የአዘርባጃን አውሮፕላን በካዛኪስታን ተከሰከሰ
የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን በካዛኪስታን መከስከሱ ተገለጸ፡፡
62 መንገደኞችን እና 5 የአየር መንገዱ ሰራተኞችን የያዘው የአዘርባጃን አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው በተባለ ከተማ አቅራቢያ አደጋው እንደደረሰበት የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
የካዛኪስታን የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር፤ በህይወት የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አደጋው እንደተከሰተ የወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱት በህይወት የተረፉ ሰዎች ስለመኖራቸው ተገልጿል፡፡
የመከስከስ አደጋው የተከሰተበት ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡