የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል::
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡
ኤጀንሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነት የ2013 ፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።
ከ617 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው ዝግጁ እንደሆኑ የገለጹት የኤጀንሲው የቀድሞ ዋ/ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፤ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በእጥፍ መጨምሩን ገልጸዋል።
ፈተናው የጸጥታ ችግር ባለባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎችም እንደ ወላጆችና ተማሪዎች ፈቃድ እንዲሁም እንደ አካባቢው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ሊከናወን እንደሚችልም ተናግረዋል።
ፈተናው በ10 የትምህርት አይነቶች መዘጋጅቱንና የኢኮኖሚክስ ፈተና በዘንድሮው መርሃ ግብር አለመካተቱን ገልጸዋል፡፡
አስፈላጊ ቁሳቁሶች ባለመድረሳቸው ምክንያት የዘንድሮው ፈተና ቀደም ሲል እንደነበረው በወረቀት እንደሚከናወን ተገልጿል። #ኢፕድ
@tikvahuniversity @Tikvahethiopia