የተማሩ መሃይማን
~~~~
ሰዎችን በጣም አከብራለሁ:: በተለይም በገሃዱ ዓለም ህይወቴ ቦንብ ቢወረውሩብኝም "ድምጼ አይሰማም":: ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ግን አልፎ አልፎ ሰይጣን ያሳስተኛል:: ዛሬም ሰይጣን ስለተፈታተነኝ ሊያመልጠኝ ነውና ይቅርታ::
አንድ ወቅት ላይ " #የተማሩ_መሃይማን" የሚል ቃል እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲደጋገም ነበር:: ነገሩ ስድብ ቢመስልም በትክክል የሚገልጻቸው #በሽ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ደጋግሜ በተግባር አረጋግጫለሁ:: ብዙ #ባለካባና #ባለዳባ መሃይማን እንዳጥለቀለቁን ዋቢ እጠቅሳለሁ::
ሴት ትሁን ወንድ እርግጠኛ ባልሆንም Mekoya Kebede ተብዬ አካውንት ብዙዎቹን ይወክላል። አካውንቱ ውስጥ ስትገቡ #Notcoin የሰበሰብነውን "ገንዘብ ያስገኛል ከተባላችሁ እንኳን ስልክ ሰውም ትደበድባላችሁ" ዓይነት ዘለፋ ታገኛላችሁ። ዝቅ ስትሉ የአገራችንን ታላላቅ ደራሲዎች የሚተችበት ጽሁፍ አለ:: "ብልፅግና ያዘጋጀው የሆነ የንባብ ቀን አለ መሰለኝ" ብሎ ነው የሚጀምረው:: አስቡት ታላላቅ ደራሲያንን ለመተች የንባብ ባህልን ከብልጽግና ጋር አያይዞ ይሳለቃል:: ደራሲያኑ የመረጧቸውን የልብወለድ መጻህፍት ያጥላላል:: የአርገራችን #ክላሲክ ስነ ጽሁፍ የሆነውን ፍቅር እስከ መቃብርን ጨምሮ "ትውልዱ ማወቅ ያለበት #የታንጉትን_ሚስጥርን ሳይሆን የተፈጥሮን ሚስጥር ነው" ይለናል:: የተፈጥሮ ሚስጥር ይቅርና ለአቅመ የድረ ገጾች ሚስጥር መረዳት ያልደረሰ ጨቅላ በዚህ ደረጃ ደፋር መሆኑ ያበሳጫል። መነሻውን ያላወቀ መድረሻውን እንደማያውቅ ሁሉ እነዚህን የአገራችን ዘመናዊ ስነ ጽሁፍ ወርቃማ ዘመን ዋቢ፣ ያዘመመው ስነጽሁፋችን ማነጻጸሪያ . . . የሆኑትን የአንጋፋ ደራስያን ትሩፋቶች ያበሸቃቅጣል:: የተማረ መሃይም ማለት ነው:: (በእርግጥ ስለዚህ ሰው መማር አላውቅም:: ፕሮፋይሉ ላይ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስለሚል ቢያንስ ፊደል ቆጥሮ ይሆናል ብዬ ነው)
~~~~
የሆነስ ሆነና የደራሲዎቻችንን የመፃህፍት ምርጫ አጥላልቶ ሲያበቃም #የነLeonard_Peikoff, #የነHenry_Hazlitt እና #የነLudwig_Von የፍልስፍና የታሪክ፣ የንድፈ ሀሳብ፣ የኢኮኖሚክስ፣ የሳይንስ፣ የስነ ልቦናና የምርምር መጻህፍቶችና መጣጥፎች እንድናነብ ይጋብዛናል። ሲጀምር እሱ የጠቀሳቸውን አይነት ዓለም ያጨበጨበላቸው መጻህፍት ያነበበ ሰው የአገሩን ታላላቅ ደራሲያንና የንባብ ባህል ጅማሬን አያጥላላም:: ሲቀጥል የኢኮኖሚክስ ግንዛቤ ስለሚኖረው ገንዘብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለሚያውቅ #Notcoin ከመተቸቱ በፊት ድረገጾች ላይ ዞር ዞር ለማለት 10 ደቂቃ አያጣም ነበር። ኢኮኖሚስቶች "ነጻ ምሳ የሚባል የለም" የሚሉት ተጋባዡ ቢያንስ ጊዜውን ሰውቶ ጋባዥ አብሮት በማሳለፉና ደስታ እንዲሰማ በማድረጉ" እንጂ ተጋባዥ ያዋጣል ወይም ሌላ ቀን ውለታ ይመልሳል ማለት እንዳልሆነ ይገባው ነበር።
#Notcoin ለመሰብሰብም የሚወጣው ጊዜ፣ ቴሌግራም ከNotcoin ሽልማት ጋር የሚያጋራቸውን ማስታወቂያዎች Subscribe, like, follow, join . . . ማድረግ . . . ገንዘብ እንጂ ነጻ እንዳልሆነም ይገነዘብ ነበር። (መገንዘቢያ አእምሮ የለውም እንጂ)
ቢኖረውማ ኖሮ ቢያንስ #የNotcoin ከማጥላላቱ፣ ከማሽሟጠጡና ከመተቸቱ በፊት ምን እንደሆነ፣ በትኞቹ ዲጂታል ገበያዎች የቅድመ ግብይት ሽያጭ እየተከናወነ እንደሆነ፣ ምን ያህል እየተሸጠ እንደሆነ . . . ለማወቅ ጥረት ያደርግ ነበር:: ሆኖም የተማረ መሃይም ደፋር ነውና በጨቅላ አእምሮው የመጣለትን #ቮሚት አይስደርግብንም ነበር:: በእውነት ቤተሰብ ካለው ሊያፍሩበት ይገባል::
በጣም የሚያሳስበውና የሚያሳዝነው ደግሞ ቅንጣት መረጃ ሳይኖራቸው #Notcoin ዋጋ እንደሌለው የሚያንቧርቁት የተማሩ መሃይማን ብዛት ሲታይ ነው:: እንደመቆያ የመጣላቸውን በድፍረት የሚያመነዥኩ፣ ኮሜንት እና የሚያጋሩት ላይ እኔን Tag የሚያደርጉ፣ ራሳቸው #የለውም ብለው ብዙ ሰው በመክሰሩ ሀሴት የሚያደርጉ ደናቁርት ብዙ ናቸው። ለስሙ ህግ ተምረናል፣ ማስተርስ አለን፣ ፒኤችዲ እየሰራን ነው . . . የሚሉ መሆናቸው ደግሞ የዚህች አገር እጣ ፋንታ አሳሳቢ ያደርገዋል። ተምረው መሃይማን ከመሆን አልፈው ሰው ባለማግኘቱ ራሳቸውን #ማስተርቤት እያደረጉ የሚረኩ ምቀኞች መሆናቸው ደግሞ የተቀመጠን ሳይቀር ያደክማል::
በነገራችን ላይ ቢትኮንም ቢሆን የሚገኘው #Mine በማድረግ ነው። የቻይናና የሩሲያ ከሃያ በላይ ተቋማት #BTC #Mine ለማድረግ እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍቃድ ወስደው ወደስራ መግባታቸው የሚታወቅ ነው። ሲጠቃለል #Notcoin ይሸጣል ብዬ ምንም አላገኝም:: የማገኘው እንደሌሎቻችሁ ራሴ #Tap በማድረግ በሰበሰብኩት መጠን። እንደሚሸጥ በእርግጠኝነት የምናገረውም ራሴ ሸጬ ነው:: #Getgum ላይን ጨምሮ በአራት የዲጂታል ብይን መሸጫ ድረገጾች ላይ የ10 ሚሊየን #Notcoin ስንት እንደሚሸጥ ማንም ሰው ማረጋገጥ ይችላል። (በተረፈ ከዚህ በኋላ እነዚህን መሰል ደናቁርት ጽሁፍ ላይ #Tag የምታደርጉኝ እቦልካለሁ)።
የምታረጋግጡበት ማስፈንጠሪያ 👇
https://getgems.io/collection/EQDmkj65Ab_m0aZaW8IpKw4kYqIgITw_HRstYEkVQ6NIYCyW/EQCaMfK3CV244OTSlTYApa1La5M0KUamCViCUAjq2j3BuFAc