ቀረብ ሲላቸው ይሰማቸዋል።"እንደዚያ በለኛ እኔ የምን ሽፍታ አገኘህ እኮ ብዬ ነው እሺ!" አሉና ወደ ውስጥ ዘለቁ። የሳሎኑ ግርማ አስደነቃቸው እጅግ የተንጣለለ ቤት ሲያዩ ተመሰጡ።ዙሪያ ገቡ መቃኘት ጀመሩ።ምራቃቸውን ሲውጡ ከጉሮሮአቸው ሲያልፍ ይሰማል።ጋሽ አክመል መቀመጫ ፈለጉ ውስጥ ያሉ ኻዲሞች ቦታ ሰጡዋቸው።ከአረብያኑ ተቀመጡ።የሚጠጣ መጣላቸው፤ ሻልም አለበሷቸው፤ ጫማቸውንም አውልቀው ከዳር አስቀመጡላቸው።አደብ የተሞላ ሙሉ እንክብካቤ በዚህ ጊዜ አህመድ ከጓዳ መጣ። ኢስላማዊ ሰላምታ አቅርቦላቸው ራቅ ብሎ ቁጭ አለ። የት እንደመጡ፣ ማን እንደሆኑ ለመጠየቅ አልደፈረም።ብቻ ፈገግ ብሎ ያስተውላቸዋል። ጋሽ አክመል ጉሮሮአቸውን ጠራርገው ንግግራቸው ጀመሩ።"እጅግ ያማረ እና የተዋበ ህይወት ነው ያለህ አላህ ባለው ላይ ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ" አሉት።አህመድ በአሚን ተቀበላቸው። "ግና የምትንጎራደድ ወይዘሮ አትታየኝም" አሉት።አህመድም " እ ትዳር ማለቶት ነው" ብሎ ጠየቃቸው። ጋሽ አክመል " የምን አዳር እኔ ለአዳር አልመጣሁም እሄዳለሁ" አሉት።አህመድ ድምፁን ከፍ አድርጎ "እ ሚስት ማለቶት ነው ያልኩት" አላቸው።ጋሽ አክመልም"አዎ ሚስት ቢጤ ማለቴ ነው"አሉት። አህመድም መልሶ " እ አይ አላገባሁም" አለ ድምፁን ቀንሶ እየተሽኮረመመ።
" አልገባሁም ይሄ ሰው ያመዋል እንዴ ዛሬ ውስጥ እኮ ነው ያለኸው እስኪ ጥራቸው " አሉ። አህመድ ወደ እሳቸው እየቀረበ "አይደለም አይ ሚስት አላገባሁም ነው ያልኮት" አላቸው። እሳቸውም ሰሙት "እንደዛ ነው እንዴ እንግዲ ይቅርታ አድርግልኝ እማዳመጫዬ ላይ ችግር ስላለ ድምፅ መለየት ይሳነኛል። እወታደር ቤት መድፍ ጮሆብኝ ነው።እዛ ነው እንዲ የሆንኩት" አሉት።አህመድም " እ ችግር የለውም ጠጋ ልበሎት ስለማይሰማ" አላቸው። "ጥጋቦት ስለማይስማማኝ ጆሮዬን እኮ ነው ያልኩህ ሌላ አላልኩም"አሉት። አህመድም በደንብ እየተጠጋቸው " አይደለም ጠጋ ልበል ነው ያልኩት እ ይቅርታ" አለና ከአጠገባቸው ተቀመጠ።ጋሽ አክመል " እንግዲህ ራሴን ላስተዋውቅህ እኔ አክመል እባላለሁ። የአባትህ የወታደር ቤት ጓደኛ ነኝ" ብለው ገና ሳይጨርሱ አህመድ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ። ነግረውት ነበርና አባቱ በውትድርና አለም ላይ ሳለሁ አንድ ጓደኛ ነበረኝ ግራ እጁን ለኔ ሲል ፈንጅ ላይ አስቀምጦ የኔን ህይወት ለመታደግ እጁ የተቆረጠ የምወደው። በህይወቴ እሱን ባገኘው ሌላ ምመኘው የለም አንድ ነገር ቃል ገብቼለታለሁ ያን ቃሌን ሳልሞላ ሞት እንዳይቀድመኝ እሰጋለሁ ይሉ ነበረ የአህመድ አባት ታድያ ጎንበስ ብሎ የጋሽ አክመልን እጅ ሲመለከት እውነትም ግራ እጃቸው በቦታው የለም አባቱ ረጅም ግዜ ሲያፈላልጓቸው የነበሩትን ያን ውዱ ጓደኛቸውን አጠገቡ ስላያቸው በደስታ ባባቱ ደግሞ በትኩስ ሀዘን እንባ አይኑን ጋረደው ድንገት ሳያስበው ተነስቶ ግንባራቸውን ሳማቸው
ክፍል-3
ይቀጥላል....
@Halal_islamic_lovers_story