ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
===============
ትምህርት ሚኒስቴርየ2013 ዓመታዊ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አፈጻፀም እየገመገመ ነው፡፡
ትምህርት ቤቶች በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ያሉበትን ደረጃ ይበልጥ ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስፋው መኮንን አንደገለፁት መድረኩ በ2013 ዓ.ም በእቅድ አፈፃፀም ሂደት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ለቀጣይ ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አቶ አስፋው አክለውም የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ከክልል ክልል ተመጣጣኝ አለመሆኑን በመጥቀስ ለቀጣይ ክፍተቶች ያሉበትን አካባቢዎች ለይቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ መድረኩ የሚጠቅም መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ በቀረበው ሪፖርት በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ትምህርት ቤቶች በወቅቱ ያለመከፈታቸው ሥራዎች በታቀደላቸው የጊዜ ገደብ ለመከናወን፣ የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ ለማዘጋጀትና የግብዓት አቀርቦት እንደ እጥረት መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በውይይቱ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተውጣጡ የዘርፉ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡