#በአዋጅ_ቁጥር_1353_2017_አንቀፅ_99_የዲሲፕሊን_እርምጃ_አወሳሰድ
1/ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት መደበኛ የዲስፕሊን ምርመራ የሚያካሂድና የውሳኔ ሀሳብ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የሚያቀርብ የዲስፕሊን ኮሚቴ ማቋቋም
አለበት፤
2/ የዲስፕሊን ቅጣት የማንኛውንም ፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ ወይም ሳይከተል ሊወሰን ይችላል፤
3/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በተቋቋመ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት ተጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበለት የመሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ የውሳኔ ሀሳቡን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመቀበል ወይም ውድቅ ለማድረግ ይችላል፤
4/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የማንኛውም መንግሥት መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 98 ንዑስ አንቀፅ (3)፤ (7)፤ (9)
ወይም (10) ላይ የተመለከተውን ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት መፈፀሙን ካመነ
በዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ሃሳብ ላይ በራሱ ከመወሰን ይልቅ ከባድ የዲስፕሊን
ጥፋት የፈጸመው ሠራተኛ ከስራ እንዲሰናበት ጉዳዩን ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ
አመራር ጉባኤ በማቅረብ ሊያስወስን ይችላል፤
5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 ድንጋጌ መሠረት በአንድ መስሪያ ቤት የሥራ አመራር ጉባኤ አማካይነት የተሰጠ ከሥራ የማሰናበት ውሳኔ በዚህ አዋጅ ወይም በሌላ ሕግ በተቋቋመ ማንኛውም አስተዳደራዊም ሆነ መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሊታይ አይችልም።
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta