#የወንድማማቾችን_ፀብ_ለመገላገል_የገቡትን_የገዛ_እናቱን_በእንጨት_በመምታት_የገደለው_ግለሰብ_በእስራት_ተቀጣ
✔️በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሙሉ ገብረ ኪዳን የአራት ወንድ ልጆች እና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ሲሆኑ ባለቤታቸው ባለመኖሩ ከልጆቻቸው መካከል እንዳለው አበራ የተባለው የመጀመሪያ ልጅ ቤተሰብ አስተዳድራለሁኝ በማለት ሃላፊነት ወስዶ እንደነበር ተገልጿል ።
ይሁን እንጂ እህት እና ወንድሞቹ ይህንን ኃላፊነቱን ሳይቀበሉ በመቅረታቸው አለመግባባት ተፈጥሮ የነበረ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ታናናሾቹ አንቺ ለእሱ ታዳያለሽ በማለት እናታቸውን ይወቅሱ የነበረ መሆኑ እና እሱም እህት እና ወንድሞቹ ከእናታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይከታተላቸው እንደነበር ተነግሯል ።
ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ጫላ አበራ ፣ ደማ አበራ ፣ አታለሉ አበራ ፣ አራርሳ አበራ እናታቸው ቤት ተገናኝተው እያወሩ እያለ ወንድማቸው እንዳለው አንድ ላይ መሰባሰባቸው በሰላም ላይሆን ይችላል በማለት በንዴት እናቱ ቤት በመሄድ አንድ ላይ ሆናችሁ እየዶለታችሁብኝ ነው በማለት ጸብ ለማንሳት መሞከሩ ተጠቁሟል። ይህንኑ ተከትሎ ጫላ አበራ እና ዳማ አበራ ከቤት ይወጣሉ። እንዳለው ለእናቴ ያልሆነ ነገር እየነገራችሁ እኔን እንድትጠራጠር የምታደርጉት እናንተ ናችሁ በማለት ወንድሞቹን ተከትሎ ከቤት ወጥቷል።።
እናትም ጸብ እንዳይፈጠር ሲለምኑ በተፈጠረ አለመግባባት እንዳለ እንጨት በመያዝ ለጸብ ይጋበዛል። እናትን ጡታቸውን አውጥታ ባጠባችኋቸው ጡቴ እያሉ በመሃል ገብተው ሲለምኑ የመጀመሪያ ልጃቸው ለወንድሞቹ የሰነዘረው የአጥር ፍልጥ እንጨት እናቱን ጭንቅላት ላይ በማረፍ ከባድ ጉዳይ ይከሰታል። ወንድማማቾች እናታቸውን ወደ ጤናጣቢያ ቢወስዷቸውም የደረሰባቸው ምት ከፍተኛ ነበር እና ህክምና ሲደረግላቸው ቢቆይም ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስተኛው ቀን ህይወታቸው አልፏል። ፖሊስ ጉዳዩን በተመለከተ እንዳለውን እና ወንድሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩን ሲያጣራ ጫላ እና ደማ አበራ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ቢኖሩም በግድያ ውስጥ ባለመኖራቸው በዓቃቢ ህግ ክስ ሳይመሰረትባቸው በነጻ ሊለቀቁ ችለዋል።
ዓቃቢ ህግ በእንዳለ ላይ በቂ ማስረጃ በማግኘቱ ክስ በመመስረት መዝገቡን ለፍርድ ቤት አቅርቧል። የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ክሱን ሲከታተል ቆይቶ ለማገላገል የገቡትን እናቱ በአጥር እንጨት በመግደል ጥፋተኛ በመሆኑ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ11 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta