ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ የሕግ ምክሮች
✅ ቅጂውን ሳታገኙ ወይም ሙሉውን ሳታነቡ ምንም ነገር ላይ አትፈርሙ
ብዙ ጊዜ ሰዎች ለራሳቸው ቀሪ ቅጂ ሳይኖራቸው ወይም የተፃፈውን ሳይረዱ የተለያዩ ስምምነቶችን ይፈርማሉ። በዚህም የተነሳ ወዳልተገባ ክርክርና ጥል ውስጥ ይገባሉ። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የፈረሙበትን የስምምነት ቅጂ በወረቀት ኮፒ መያዝ ይመረጣል። ይህ የማይመች ከሆነ ደግሞ የፈረሙትን እያንዳንዱን ሰነድ በፍጥነት ፎቶ አንስቶ መያዝ ይገባል።
✅ ቤተሰብዎንና ንግድዎን ከሕግ ስጋት ይጠብቁ!
የንግድ ስራ ሲሰሩ ድንገት የገንዘብ ዕዳ ቢከሰት እራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ ተጠያቂነት ማዳን የሚችሉት ኃ/የ/የግ/ማ ወይም አ/ማ ኩባንያ መስርተው ሲሰሩ መሆኑን ተረድተው ሀብትዎን የንግድ ድርጅት በማቋቋም ያንቀሳቅሱ!
✅ የሕግ ባለሙያ እስኪያማክሩ ድረስ_ሃላፊነትን ወይም ተጠያቂነትን አምነው አይቀበሉ
በጭንቀት ወይም በፍርሃት ስሜት ዉስጥ ሆነን የምንናገራቸው ነገሮች እኛኑ መልሰዉ ሊጎዱን ይችላሉ ስለሆነም በፍርድ ቤት በፖሊስ ጣቢያ ወይም በሌላ መሰል ስልጣን ባላቸው አካላት ፊት የምንሰጣቸውን ቃላት ማስተዋል ያስፈልጋል። ከተቻለ የሕግ ባለሙያ ወይም ጠበቃ እስኪያማክሩ ድረስ ዝምታ ጥሩ መፍትሄ ነው።
✅ የሕግ ጉዳዮችን በተመለከተ የሕግ ባለሙያ ያማክሩ
ከሕግ ባለሙያ ጋር መማከር በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙ ጠበቆች በነፃ ወይም በክፍያ ወሳኝና አስፈላጊ ምክር ይሰጣሉ። የመንግስት አቃቤ ሕግም አቅም ለሌላቸው ወገኖች የሕግ ድጋፍ ያደርጋል። ስለሆነም የሰለጠነ ባለሙያ ጉዳይዎን እንዲመለከተው በማድረግ የሕግ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፦ ውል ከመፈረምዎ በፊት ውሉ ልዩ የሕግ ቋንቋ የሚያካትት ከሆነ እነዚያ ድንጋጌዎች ብዙ ጊዜ ከባድ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ውሉን ከመፈረምዎ በፊት የሕግ ባለሙያ ቢያማክሩ ይመረጣል።
✅ ማናቸውንም ስምምነቶች በጽሁፍ_ያድርጉ! ሰነዱንም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡ!
ሰዎች ያለማቋረጥ ስምምነቶችን ያደርጋሉ። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እነኚህን ስምምነቶች በፅሁፍ አድርገው በጥንቃቄ ሲዋዋሉ አይስተዋልም።
ለምሳሌ እንደ ቤት ሽያጭ፣ የመኪና ሽያጭ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ወዘተ ስምምነቶች ሕጋዊ ለመሆን ግዴታ በጽሁፍ መሆን አለባቸው። ስለሆነም ሁልጊዜ ስምምነቶችዎን በጽሁፍ የመፃፍ፣ ሁሉም ተዋዋይ ወገኖችና እማኞች መፈረማቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ሰነዱን በጥቅቃቄ ማስቀመጥ ስምምነቱ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይረዳዎታል::
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta