ምን እነግርሃለው ?
እንደምታየው ነው።
............................
የተለኮሰ ህንፃ እሳት ሲንበለበል
የሚጨፍር መንጋ ዜማ ሲቀባበል
የተዘረፈ እቃ አደባባይ ሲሸጥ
የገበርከው ገንዘብ ለጠላትህ ሲሰጥ
እንደምታየው ነው።
............................
ከሰል የመሰለ የመስጅድ ምሶሶ
ሆድ የባሰው አባት ያደባባይ ለቅሶ
የመአት ሰልፈኛ ድምፁ የተናቀ
በሌባ አሰተዳደር ጩኸት የተቀማ እምባ የተነጠቀ
እንደምታየው ነው ...
................................
ጠላት ሲጠራራ ደርሶ ሲደጋገፍ
ሊሸፍን ሲቋምጥ አንደኛው ያንዱን ግፍ
ያኡመተል ኢስላም
አንተው ምትቀማ አንተው ምትከሰስ
አንተው ምትበደል አንተው ምትወቀስ
አንተው ምትቃጠል ንብረትህ የሚነድ
አንተው ተጠርጥረህ ባንተው ላይ ሚፈረድ
እንደምታየው ነው ።
.......................................
አማራጭ የለህም ከመዋደድ ሌላ
ከዘርም ከጎጥም ይበልጥብህ ሆኗል ኡኹወቱን ፊላ
አዎ ተጠራራ እንደተጠራሩት
ሂዱ ለአፋሩ ለሶማሌው ጀግና በደሉን ንገሩት
ኦሮሞው አማራው ከተሜው ገጠሬው
አስረዱት ይወቀው የነገረው ወሬው
ከሚናራው ግርጌ ከቁባው ጥላስር
ሙስሊሙ ይመካከር ቃል ኪዳን ይታሰር
#ወአኢዱ_ለሁም_መስተጣእቱም_ሚን_ቁዋ"
ይደራጅ ወጣቱ ለዲኑ እንዲሰዋ
© Salahadin Alli
T.me/Kennaapost
እንደምታየው ነው።
............................
የተለኮሰ ህንፃ እሳት ሲንበለበል
የሚጨፍር መንጋ ዜማ ሲቀባበል
የተዘረፈ እቃ አደባባይ ሲሸጥ
የገበርከው ገንዘብ ለጠላትህ ሲሰጥ
እንደምታየው ነው።
............................
ከሰል የመሰለ የመስጅድ ምሶሶ
ሆድ የባሰው አባት ያደባባይ ለቅሶ
የመአት ሰልፈኛ ድምፁ የተናቀ
በሌባ አሰተዳደር ጩኸት የተቀማ እምባ የተነጠቀ
እንደምታየው ነው ...
................................
ጠላት ሲጠራራ ደርሶ ሲደጋገፍ
ሊሸፍን ሲቋምጥ አንደኛው ያንዱን ግፍ
ያኡመተል ኢስላም
አንተው ምትቀማ አንተው ምትከሰስ
አንተው ምትበደል አንተው ምትወቀስ
አንተው ምትቃጠል ንብረትህ የሚነድ
አንተው ተጠርጥረህ ባንተው ላይ ሚፈረድ
እንደምታየው ነው ።
.......................................
አማራጭ የለህም ከመዋደድ ሌላ
ከዘርም ከጎጥም ይበልጥብህ ሆኗል ኡኹወቱን ፊላ
አዎ ተጠራራ እንደተጠራሩት
ሂዱ ለአፋሩ ለሶማሌው ጀግና በደሉን ንገሩት
ኦሮሞው አማራው ከተሜው ገጠሬው
አስረዱት ይወቀው የነገረው ወሬው
ከሚናራው ግርጌ ከቁባው ጥላስር
ሙስሊሙ ይመካከር ቃል ኪዳን ይታሰር
#ወአኢዱ_ለሁም_መስተጣእቱም_ሚን_ቁዋ"
ይደራጅ ወጣቱ ለዲኑ እንዲሰዋ
© Salahadin Alli
T.me/Kennaapost