🍁ውለታ🍂
🌵ክፍል ሁለት🌵
♓♓♓♓♓♓
ብሩክ ለጓደኞቹ ሁሉ ጥሩ ስሜት ቢኖረውም ለኤልያስ ግን ለየት ያለ ቦታ ነው የሚሰጠው ኤልያስ የጥቁር ቆንጆ የሚባል እረዘም ያለ የሃያ አመት ወጣት ነው እረዥም እራስታ ፀጉሩ ፊቱን ከሲታ አድርጎታል በፀባዩ ግን ሁሌም እንዳስደነቃቸው ነው በጣም ተጨንቀው ቁጡ ሆነው አይበርድም ያሉትን ፀብ ድንገት መጥቶ ሲያቀዘቅዘው ጓደኞቹ እሱ ባይኖር አብሮ ነታቸው ያበቃለት እንደነበር ያስባሉ በብሩክ ኩራት በቸርነት አለው አለው ማለት በአቤል አይለኝነት ድሮ ገና በተለያዩ ነበር..... ብሩክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወደዳት ሴት እንኳን ስሜቱን መግለፅ ቸግሮት ኤልያስ ነበር ያቀራረበው ይኽው እስካሁንም ዕድላዊት ፀሐዬ አብራው ናት ጓደኞቹ በዕድላዊት ሁሌም እንደ ተደነቁ ነው ውብና መልካም ስነመግባር ያላት ልጅ ናት በዛላይ ግልፅ ብዙ የተሻሉ አማራጮች ቢኖራትም እንኳ ስለብሩክ ሁሌም ትቸገራለች ትደክማለች ስለሱ የማትሆነው የለም.... አንዳንዴ የስሜቷን መጠን አልፎ ሲያዩ እናም ብሩክ በራሱ ዓለም ተውጦ ትኩረቱን ሁሉ ሙዚቃው ላይ ብቻ ሲያደርግ ጓደኞቹ ስሜቷ እንዳይጎዳ ይፈሩላታል.... አጠገቧ ሆኖ ምክንያት እየደረደረ ስለ ብሩክ ጥሩ እንዲሰማትና እንዳታዝንበት እየነገረ የሚያፅናናት ኤልያስ ነው ብዙም አታስቸግርም ከብሩክ ቸልተኝነት ይልቅ ለሱ ያላት ፍቅር አያልነት ሚዛን ይደፋባታል ብሩክን ትታገሳለች.... ከዚ በፊት ያልተሳካለትን ነጠላ ዜማ ለማሰራት ከገንዘብ ጀምሮ መስዋት ከፍላለች ቤተሰብ እያስቸገረች........
, አንዳንዴ ብሩክ ከዝና ጥማቱ ወደራሱ ሲመለስ ጓደኞቼ እናንተ ባትኖሩ ምን እሆን ነበር በተለይ ዕድልዬ የወደፊት ሚስቴ የኔ ፍቅር የኔ አልቃሻ ስወድሽ እኮ ሲላት ጓደኞቹ ፈገግ ፈገግ ሲሉ ዕድላዊት ንግግሩ ለልቧ ሞቅታን ሲፈጥርላት ጓደኞቹ መኖራቸው እንኳ ሳያሳስባት ተነስታ ጥምጥም ብላ ትስመዋለች እናም "የኔ አስቸጋሪ ብሩክዬ እኔም በጣም እወድሃለው ሁሉም ጥሩ ይሆናል ተስፋ አትቁረጥ "ትለዋለች
"እሺ ውዴ አንቺ እያለሽ ጓደኞቼ እያሉ ተስፋ መቁረጥ የለም "ይላታል የስሜቷ ኀይል እየገረመው
,,,,ብሩክ ዛሬ ላይ የስኬቱ መጀመሪያ ላይ ደርሷል ፈገግታውና ኩራቱ ጨምሯል አዳዲስ ሰዎች ወደሱ እየቀረቡ ነው ጊዜ የለውም ጓደኞቹን እንደቀድሞ በየቀኑ አያገኛቸውም ነገርግን በተገኘው አጋጣሚ አብሮነታቸውን እያሳዩት ነው ደስተኛ እንዲሆን ትልቅ ቦታ እንዲደርስ የሁሌም ምኞታቸው ነው
ዝግጅት ሲኖረው ዕድላዊት ትገኛለች ጓደኞቹም ጭምር ከመድረኩ ፊትለፊት ዕድላዊት ዛሬም እሱ ሲዘፍን በደስታ እንደ ተዋጠች ዕንባ ባቀረሩ አይኖቿ ታየዋለች .... ብሩክ መድረኩላይ ከወዲ ወዲያ ሲንጎራደድ አድናቂዎቹ ሲጮሁ ሴቶቹ ስሙን አቆላምጠው ሲጠሩት ለራሷ ፈገግ ብላ 'የኔ መሆኑን ማን በነገራቹ 'ትላለች......ኤልያስ ብሩክ የሚገርም ድምፅ አውጥቶ ሲዘል "ብሮ ዋውውው እኮራብሃለው.. "ብሎ ሲጮህለት... ዕድላዊት "የስስስ" ብላ አብራው ጮኽች ቸርነትም አቤልም አብረው ስለ ጓደኛቸው ስኬት ጮሁ ዘለሉ ዘፈኑ ተውረገረጉ ብሩክ እየዘፈነ ከመድረክ እጁን እያውለበለበ መለሰላቸው .... ዕድላዊት መድረኩ ላይ ወጥተሽ ሳሚው የሚል ድንገተኛ ስሜት ተሰማት ከዚ በፊት አድርጋው ባታውቅም ይሄ የተለየ ስሜት ተሰማት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ትልቅ መድረክ ላይ የተጫወተው ይሄ ምኞቱ ነበር ሁሉም ይህን ያውቃሉ በተለይ እሷ በዛላይ ሰሞኑን ስላላገኘችው ናፍቆቷ ጨመረ ..... ድንገት ያበጠው ይፈንዳ ብላ ወደ መድረኩ ሮጠች አንዱን ጋርድ አምልጣ ብሩክ ጋር ደረሰች ተመልካቹ ጮኽ እነ ኤልያስ አጨበጨቡ ብሩክ ዕድላዊት ወደሱ ስትመጣ አይቶ ስቅቅ አለ ወደሷም ከመምጣት ይልቅ ወደ ቤዝ ጊታሪስቱ ተጠጋ ሴቶች አድናቂዎች ጮሁ "ብሩኬ ፍቅር ሁሁሁሁ"አሉ
ዕድላዊት አጠገቡ ሄዳ በደስታ እና በፍርሃት እንደተጥለቀለቀች "ኮርቼብሃለው የኔ ጌታ አፈቅርሃለው "ብላ አቀፈችው.....ብሩክ እጁን ለማቀፍ አላነሳም ይልቁኑ ያፈረ መሰለ " ዕድላዊት ምን እያረግሽ ነው? እባክሽ ተይ እንዲ አታድርጊ አለ ማይኩን እያራቀ ከእቅፋ ለመውጣት እየሞከረ ... ዕድላዊት ያልጠበቀችው ምላሽ የሰማችውን ለማመን ከበዳት ለቃው ቀና ብላ አየችው ደነገጠች ይሄን አስተያየት አታውቀውም እግሮቿ ሊከዷት ሞከሩ ......
⚡ይቀጥላል⚡
VOTE