❤️ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናገሩ...
" አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር
ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል። ከቀብር ሥነስርአቱም በኃላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ መላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት
ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጓደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላችሁ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው አልሄድም"። ከዚያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ
አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም" ፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ
አልጋ ያዘጋጅለታል።
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ የሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
#ታዲያ ለኛ ከነብይያትም ከ መላኢኮችም የበለጠ የሚከራከርልን ቁርአን ከሆነ።
#እኛ_ከቁርአን_ጋር_ያለን_ግንኙነት_እንዴት_ነው???
#ቁርአንን_በቀን_ምን_ያህል_እንቀራለን_ወይም_ቁርአንን_በቀን_ምን_ያህል_እናነባለን???
ለሁላችንም የምተወው ጥያቄ ነው።
#ሼር_ሼር_በማድረግ_ከማይቋረጠው_አጅር_ተካፋ_ይሁኑ!!!
#አደራ ለሌሎች ሰዎች በማድርስ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!!!
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን።
👇👇👇👇👇👇👇👇
Share & Join join join
👇👇👇
@Quran_Becha@Quran_Becha 👆👆👆