TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Telwin Creative Space

8 Apr 2025, 11:48

Open in Telegram Share Report

የዛሬ 3ዓመት አከባቢ ስለ ሎጎ እና ዓይነቶቹ የጻፍኩትን አጭር ፅሁፍ ላጋራችሁ በደንብ አንብቡት እና እጠይቃቸኋለው።

===============
💡 #ስለሎጎ_Logo ምን ያህል ያውቃሉ?
ሎጎ (አርማ) ማለት በአጭሩ አንድን ድርጅት ወይም ተቋም ወይም ምርት ወይም አገልግሎት የሚገልጽ እና የሚወክል #ምልክት ነው።ይህ ምልክት ጽሁፍ ወይም ምስል ወይም ቅርጽ ሊሆን ይችላል።አሊያም እነዚህን ይዘቶች በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ መለያ ሊሆን ይችላል።ለተለያዩ ድርጅቶች እና ተቋማት መለያነት ተነድፈው ጥቅም ላይ የዋሉ የተለያዩ የሎጎ ዓይነቶች አሉ።ዝርዝራቸውን እንሆ :-

1️⃣.Word mark (Logo type)
ይህ የሎጎ ዓይነት የድርጅቱን ስያሜ በጽሁፍ በማስቀመጥ ብቻ የሚነደፍ ሲሆን ፤ የፊደላቱ ቅርጽ በእጅ ጽሁፍ አጻጻፍ ወይም ለዚሁ ተብሎ በተነደፈ Font (የፊደላት ቅርጽ/ስታይል) አሊያም በሌላ ለየት ባለ የአጻጻፍ ስልት የተጻፈ ሊሆን ይችላል።ለዚህ ምሳሌ ከሚሆኑ ዝነኛ ሎጎዎች መካከል የ ኮካ ኮላ (Coca Cola) ፣ የሶኒ (SONY) ፣ የካነን (Canon) እንዲሁም የጉግል (Google) ሎጎዎች ተጠቃሽ ናቸው።

2️⃣.Letter mark
ይህ የሎጎ ዓይነት የድርጅቱን ስያሜ የመጀመሪያ ፊደላት ብቻ በመጠቀም የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን ፤ ከመጀመሪያው Word mark ሎጎ የሚለየው ሎጎው የሚያካትተው ሙሉ የድርጅቱን ስያሜ ሳይሆን የስያሜውን የመጀመሪያ ፊደላት ብቻ መሆኑ ነው።ለዚህ ታዋቂ ምሳሌ መሆን ከሚችሉ ሎጎዎች መካከል የ ናሽናል ኤሮናቲክስ ኤንድ ስፔስ አድሚኒስትሬሽን /ናሳ/ - እ.ኤ.አ 1975 - 1992 ጥቅም ላይ የዋለው ሎጎ (The National Aeronautics and Space Administration /NASA/ from 1975 until 1992) ፣ እና የ ኬብል ኒውስ ኔትዎርክ /ሲኤንኤን/ (Cable News Network /CNN/) ሎጎ ተጠቃሽ ናቸው።ይህ ዓይነቱ ሎጎ ስማቸውን መጥራት (ምላስ ላይ) ለሚከብዱ አሊያም ስያሜያቸው ረዥም ለሆኑ ድርጅቶች ዓይነተኛ ምርጫ ነው።

3️⃣.Pictorial mark (Brand mark)
ይህ የሎጎ ዓይነት ድርጅቱን በሚገልጹ ምስሎች ወይም ምልክቶች የሚነደፍ ሲሆን ምንም ዓይነት ጽሁፋዊ ይዘት የለውም።ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑ ሎጎዎች መካከል የ አፕል (Apple) ፣ የትዊተር (twitter) እና የ ኢንስታግራም (Instagram) ሎጎዎች ተጠቃሽ ናቸው።

4️⃣.Abstract logo mark
ይህ የሎጎ ዓይነት የ Pictorial mark (ከዚህ በፊት ሶስተኛ ላይ የጠቀስነው የሎጎ ዓይነት) አንድ አካል ሲሆን ከ Pictorial mark የሚለየው ይህኛው የሎጎ ዓይነት የሚነደፈው እንደ Pictorial mark በግልጽ ምንነታቸው በታወቁ ምስሎች እና ምልክቶች ሳይሆን በአንጻሩ ረቂቅ በሆኑ የጂኦሜትሪክ ቅርጾች ነው።ለዚህ እንደ ምሳሌ የ ፔፕሲን (pepsi) ሎጎ መጥቀስ ይቻላል።

5️⃣.Mascots
ይህ ዓይነቱ ሎጎ ስዕላዊ ገጸ ባህሪያትን በመጠቀም የሚነደፍ ሲሆን ለዚህ ሚስተር ፒናትን (Mr. Peanut) እንደምሳሌ መውሰድ እንችላለን።

6️⃣.Combination mark
ይህ የሎጎ ዓይነት ከላይ የጠቀስናቸውን የሎጎ ዓይነቶች ( ስያሜ እና ምልክትን ወይም ስያሜ እና ቅርጽን ወይም ስያሜ እና ምስልን) በማጣመር የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን በርከት ያሉ ሎጎዎችን በዚህ መልኩ እናገኛለን ለምሳሌ ያህል የአዶቤ (Adobe.inc) የ አዲዳስ (adidas) ፣ የማይክሮ ሶፍት (Micro soft) እና የህዋዌ (HUAWEI) ሎጎዎችን መጥቀስ ይቻላል።

7️⃣.Emblem
ይህ የሎጎ ዓይነት ልክ እንደ Combination mark (ከዚህ በፊት ስድስተኛ ላይ የጠቀስነው የሎጎ ዓይነት) ስያሜ እና ቅርጽን ወይም ምስልን ... በማጣመር የሚነደፍ የሎጎ ዓይነት ሲሆን ከ Combination mark የሚለየው የድርጅቱ ስያሜ እና የተነደፈው ቅርጽ ወይም ምስል ለየብቻ የሚቀመጡ ሳይሆኑ ስያሜው በሎጎው ቅርጽ ውስጥ ታቅፎ የሚቀመጥ መሆኑ ነው ።ለዚህ እንደምሳሌ የ ናሳ (NASA) ፣ የ ቢኤም ደብልዩ (BMW) እና የ ፎርድ (Ford) ሎጎዎችን መጥቀስ ይቻላል።

By Esmael Kemal
Jul 24 2022

@TelwinCreative

623 0 5 7
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot