ውሃ
ከሰማይ የመጣ ነው፡፡ ሲዘንብ ያለምክንያት አይደለም፡፡ በረሃውን አረስርሷል፡፡ ምድር ታፈራ ዘንድ አድርጓል፡፡ ረሃብ በጥጋብ እንዲለወጥ ከመሬት ማህፀን ፍሬን አውጥቷል፡፡
መልክና ጣእም የለውም ይሉታል፡፡ ዳሩ ግን በጥም የተነሳ ሊሞቱ ያሉትን ጥም ይቆርጣል፡፡ ያረካቸዋልም፡፡ ቅርፅ አልባ ቢባልም ከትንሽ እስከ ትልቁ ድረስ በሁሉም ውስጥ ያለመገደብ ይገባል፡፡
ያነፃል፡፡ የቆሸሸ ቢኖር ሊያነፃው ዘንድ ጉልበት አለው፡፡ ማንም በእድፋምነቱ የተጨነቀ በመቆሸሹ ያፈረ ቢኖር ውሃው ያነፃል፡፡
ይሸከማል፡፡ ግዙፉ መርከብ ከነግሳንግሱ በላዩ ቢሆን ከበደኝ ሳይል እስከወደቡ ድረስ ይወስደዋል፡፡ መርከቡን ከነምናምኑ ሚሸከም ሃይል!
ደግሞም ጠራርጎ ሚወስድ ጉልበታም ነው፡፡ ደራሽ ሆኖ ሲመጣ ማንም አያስቆመውም፡፡ ሁሉንም ጠራርጎ ይወስድ ዘንድ ጉልበቱ አለው፡፡
ይህ ውሃ ደመናም ይሆናል፡፡ የብርቱ ፀሃይን ጉልበት ሚያሸንፍ ደመና! ሃሩርን መሸሽ ሚፈልጉ በአቅማቸው ምንም ማድረግ ማይችሉ እንኳን በደመናው የተነሳ ከፀሐዩ ንዳድ ይድናሉ፡፡
ውሃው ፍሬን ሊሰጥ ዝናብን ሊያበቅል ከሰማይ ቢመጣም ከምድር ወደ ሰማይም ተመልሷል፡፡ ውሃ ነውና መዝነብን ብቻ ሳይሆን በትነት ወደ ላይ መውጣትንም ያውቅበታል፡፡
(በነፃ የሆነው ውሃ እጅግ ውድ ነው)
ሰማዩን እያየሁት ነው፡፡ ሰማዩ ላይ ዳግመኛ እንደሚዘንብ ምልክትን እየሰጠ ነው፡፡
ዳግመኛ ይዘንባል!!
(ተስፋአብ ተሾመ)
@Tfanos
@tfanos