የህይወት ቃል✝


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎን ይህንን @breadoflife4all_questions_bot የቴሌግራም ቦት ይጎብኙ::

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የህይወት ቃል📖

" ደግሞ ሌላው። ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። 62፤ ኢየሱስ ግን። ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። "
ሉቃስ 9:61-62

ውስጣዊ እና ውጫዊ 🤍


"ግቡ ምንድን ነው?" የሆነ ነገር እንድታደርግ ከተጠየክ ያ ጠቃሚ መረጃ ነው። ዓላማዬ ምንድን ነው? ግቤ ምንድን ነው? የሚለውን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ምን እያሰብክ እንደሆነ የማታውቅ ከሆነ ግብህን በጭራሽ ልታሳካው አትችልም።

የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆንን በተመለከተ፣ አዳኛችን ግቡን በጣም ግልፅ ያደርጓዋል። የመጨረሻ ግባችን በሰማይ የዘላለም ሕይወት ነው፤ ያ ነው አላማችን። ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከተናገረው የበለጠ ግልጽ በሆነ መንገድ ሊናገረው አይችልም ነበር። “እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።” (3፡1-2)

በአንድ ወቅት አንድ ሰው ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ እከተልሃለሁ። ነገር ግን አስቀድሜ ተመልሼ ቤተሰቦቼን ልሰናበት” ሲል ወዲያው ኢየሱስ መለሰ፡- “ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።" የእሱ ነጥቡ ግልጽ ነበር። የእኔ ደቀመዝሙር ልትሆን ከፈለግክ፣ ዓይኖችህን ወደ ላይ ማድረግ አለብህ። እሱ በዚህ ዓለም ነገሮች እና ሰዎች በቀላሉ እንደምንዘናጋ ያውቃል። ወደ ኋላ አትመልከት እያለ እሱ ያሳስበናል። ዓይኖችህን ከግቡ ላይ አታንሳ።

ግን ኢየሱስንም ደግሞ ተረዳዉ። በህይወታችን ውስጥ ላሉ ሰዎች በተለይም ለቤተሰባችን ፍቅር እና አሳቢነት እንድናሳይ ይፈልጋል። በምንችለው መንገድ ሁሉ በየቀኑ እንድናገለግላቸው ጠርቶናል። ነገር ግን ምርጫው በእሱና በቤተሰባችን መካከል ከሆነ ወይም በሟች ዓለም ውስጥ በምንኖረው ሕይወታችንና ከእሱ ጋር በሰማይ በሚኖረው የዘላለም ሕይወት መካከል ከሆነ ምንም ዓይነት ፉክክር እንደማይኖር እንድንገነዘብ ይፈልጋል። ኢየሱስ እና ሰማያዊ ነፃነታችን የመጨረሻ ግባችን መሆን አለበት።

እና እንዴት ነው እዚያ መድረስ የምንችለው? በራሳችን ሥራ ሳይሆን በኢየሱስና በኃይለኛው ቃሉ ነው፡። ያንን የሚያድነውን ቃል ተንከባከበው ምክንያቱም ዓይኖችህ ወደ ላይ ስለሚመራ።

እንፀልይ፡-
ውድ ኢየሱስ ሆይ፣ ልቤ እና ሀሳቤ ሁል ጊዜ በአንተ ላይ እንዲያተኩር መንፈስህን ስጠኝ።
አሜን


በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከተፃፉ ታላላቅ መዝሙሮች መካከል አንዱን እስኪ ተጋበዙኝ!!


(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 23)
----------
1፤ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2፤ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3፤ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4፤ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5፤ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6፤ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

እግዚአብሔር ይባርካቹ !!!


የዕለቱ ጥቅስ📖

" ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ። 7፤ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። "
2 ጢሞቴዎስ 1:6,7

ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ🎁


እግዚአብሔር ተማሪ፣ በራሱ የመተማመን፣ የሌሎችን ግብአት ለማግኘት የሚጓጓ፣ በዋጋ የሚመራ እና ነገሮችን እና ሰዎችን ለስኬታማነት በሚያበቃ ቦታዎች ላይ የሚያስቀምጥ ሰዉ አድርጎኛል። እግዚአብሔር እንዴት ስጦታዎችን ይሰጣል? በሰዎች ፊት ስትቆም ረድቶሃል? ታታሪ አድርጎሃል? ለዝርዝሮች ትኩረት ሰጪ አድርጎሃል? ጠንቃቃ እና አሳቢ አድርጎሃል? እስኪ እራስን ተመልከት!

እግዚአብሔር አካልን፣ ነፍስንና አእምሮን ፈጥሮልካል። ያ ማለት ከግራ ክርንክ በስተጀርባ እንዳለው ልዩ የልደት ምልክት (አምሮት) አንተም ልዩ የሆኑ ባህሪያት አሉክ ማለት ነው። እነዘህን የሰጠህን ስጦታዎች “ለሚወዱት ሁሉ ለበጎ” ዓላማ በእግሮችህ ሥር ተቀምጠዋል።

የጢሞቴዎስ እውነት ይህ ነበር። ስጦታዎች ነበሩት። መንፈሳዊ አባቱ ጳውሎስም ይህን አይቶ ያበረታታው ነበር። ለጢሞቴዎስ “በእሳት አቀጣጥላቸው” አለው። እነሱን በማግኘትህ ብቻ አትርካ፣ ነገር ግን አሳድጋቸው፣ ያሳደካቸውንም ደሞ ተደገፍባቸው። "እነርሱ ለአንተ ተሰጥተዋል፤ ስለዚህ አሁን በይበልጥ ተጠቀምባቸው!

ስጦታዎቼን እንደ ነበልባል እንዴት ማራገብ እችላለሁ?” ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። ትክክለኛ ጥያቄ ነው። ምናልባት የILPF ምህጻረ ቃል ይረዳል ይሆናል (መለየት(identify)- መማር(Learn)- መለማመድ(Practice) - አስተያየት መቀበል(Feedback))። ያለክን ስጦታዎች ለይ። ምናልባት ያ ራስን በመገምገም ሊሆን ይችላል ወይም የታመነ አማካሪህን "በእኔ ውስጥ ምን ታያለህ?" በለህ ጠይቅ። ከዚያ ስለእነዚያ ስጦታዎች ተማር። ምን አይነት ናቸው? ሌላ ማን አለው? እነሱን አላግባብ መጠቀም ምን አደጋ አለው? የሚሉትን ጥያቄዎች አጥና። በመቀጠል ልምምድ አድርግ። ማለቂያ የሌላውን የመሞከር እና የመውደቅ ዑደቶች ውስጥ ካላለፍክ በምንም ነገር ላይ ጥሩ አትሆንም። ያ ልምምድ ነው። እና በመጨረሻም አስተያየቶችን ተቀበል። ለአንተ ቅርብ የሆኑትን ጠይቅ፣ “ስጦታዬን ለመጠቀም ሞክሪያለው። እንዴት የሄደ ይመስላችኋል? በሚቀጥለው ጊዜ ምን ማሰብ አለብኝ? ” ብለህ ጠይቅ። እግዚአብሔር በተሰጠህ ስጦታዎች ውስጥ ስትኖር፣ በዛ ውስጥ ጌታ ፈቃዱን ሲፈጽም አስተውል።

እንፀልይ፡-
ጌታ ሆይ፣ ስላለኝ ስጦታዎች አመሰግንሃለሁ። ካንተ እንደሆኑ አውቃለሁ። መንግሥትህን በሚገነባ መንገድ እንድጠቀምባቸው እርዳኝ።
አሜን።

#DailyDevotions #June_29_2022 #የእለቱጥቅስ #Wednesday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/wl4all


" እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ አባቶቻችሁ በወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። "
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 24:15


የእለቱ ጥቅስ📖

"ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤"
(2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:3)

መፀለየችሁን ቀጥሉ✝🛐

በአንድ ቤተሰብ አምልኮ ላይ ጸሎቶችን ለማቅረብ ተራ የልጃቸው ነበር። አንገቱን ደፍቶ፣ አይኖቹ ጨፍኖ በታላቅ ድምፅ “ውድ ኢየሱስ ሆይ፣ ክፉ ሰዎችን ሁሉ ጥሩ አድርጋቸው፣ እናም ጥሩ ሰዎችን ሁሉ አበርታቸው::” አለ።

ሰሞኑን ለማን ጸልያቸዋል? የቤተሰብ አባል? የስራ ባልደረባ? ጎረቤት? ምናልባት የእናንተ ዝርዝር ረጅም እና በየጊዜው እየሚቀያየር ሊሆን ይችላል። ወይም ደሞ የእናንተ ዝርዝር አጭር እና ሰፋፊ ሱሪዎች ፋሽን ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ያልተለወጠ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትጸልያላቹ።

የምትጸልዩት እግዚአብሔር እንድንጸልይ እንደጋበዘን ስለምታውቁ ነው። የዙፋኑ ደጅ ለአንተ ክፍት ነው። ወደ ውስጥ ስትገባ፣ የአጽናፈ ዓለምን ጉዳይ ሁሉ የሚመራው የንጉሶች ንጉስ አይኑን በአንተ ላይ ተክሎ ምን እና ማን በልብህ ውስጥ እንዳለ ለመስማት ዝግጁ ሆኖ ወደ ፊት ይጠጋል።

ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ይህን ሃይል ለተማሪው፣ ለጠባቂው እና ለጓደኛው፣ ፓስተር ጢሞቴዎስ ለመፀለይ ተጠቅሞበታል። ጳውሎስ ያለማቋረጥ ይጸልይ ነበር። ለእግዚአብሔር መንግሥት ጥቅም ሲባል ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መታገል እንደሆነ ያውቃል። ጳውሎስ የሰማይ ጌታ ጸሎትን በሚሰማበት ጊዜ የሰይጣንን ጥቃት እንደሚከለክል እና ማንኛውንም ክፉ እቅድ እንደሚያጠፋ ያውቅ ነበር። ጳውሎስ ጸሎት የእርሱን ሕልሞች እና ፍላጎቶች፤ የአምላክን ሕልሞችና ፍላጎቶችን በተሟላ ሁኔታ ለማንጸባረቅ እንዲችሉ አድርጎ እንደሚያስተካክል ያውቅ ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ጸለየ።

እንደ ጳውሎስ መጸለይን ቀጥሉ። እግዚአብሔር የምትናገሩትን ለመስማት እና ለአለም ያለውን እቅድ ለመፈጸም ይጓጓል። ያም አሁን እና ለዘለአለም የኛን መልካም ነገር ብቻ የሚያስብ እና ክፋትን የሚያደቅ እቅድ ነው።

እንፀልይ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፣ ጸሎቴን ስለሰማህ አመሰግናለሁ። እንድጸልይ ስለጋብዘኝ ብዙ ጊዜ እና በትልልቅ ጸሎቶች እንድጸልይ ድፍረትን ስጠኝ። ጸሎቶቼን ውስደና አንተ በምታቀው በመልካሙ መንገድ መልስ ስጠኝ። ክፉውን ጨፍልቀው እና መልካም ነገርህን አሳየኝ። በኢየሱስ ስም
አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #Monday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


የጌታ ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

በተለያዩ ነገሮች ተይዤ ስለነበር ለረጅም ጊዜ ፖስት ስላላደረኩ ይቅርታ!
ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ ወደ በፊቱ ቅደም ተከተል እንደምንመለስ በጌታ ፍቅር ላሳውቃችሁ ወዳለው።


የእለቱ ጥቅስ📖

"17፤ ሊቀ ካህናቱ ግን የሰዱቃውያን ወገን ሆነውም ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሡ ቅንዓትም ሞላባቸው። 18፤ በሐዋርያትም ላይ እጃቸውን ጭነው በሕዝቡ ወኅኒ ውስጥ አኖሩአቸው። 19፤ የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና። 20፤ ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ አላቸው። 21፤ በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፥ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ። 28፤ ሊቀ ካህናቱም። በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ብሎ ጠየቃቸው። 29፤ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል። "
የሐዋርያት ሥራ 5፡17-21,28,29

ሂዱ እና ስበኩ

የምንኖረው ሰዎች በመንፈሳዊ እና ዘላለማዊ ሞት በሚሞቱበት ዓለም ውስጥ ነው፣ እና ብቸኛው እውነተኛ የሞት መድሀኒት አለን። ከሞት የተነሳውን ኢየሱስን በማመን፣ እኛ ለዘላለም መኖር እንችላለን። ከሞት በተነሳውን በኢየሱስ ውስጥ፣ ለዘላለም በደስታ እንድንኖር ትእዛዝ አለን። ለሌሎች ያለን ፍቅር ደግሞ ሄደን እንድንነግራቸው ያነሳሳናል።

አዎን፣ ይህን እውነት ውድቅ የሚያደርጉ፣ ይህን አጋጣሚ የሚክዱ እና በኢየሱስና በእሱ አማካኝነት አስደሳች የዘላለም ሕይወት አግኝ የሚለው ሐሳብ ሞኝነት እንጂ ሌላ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ ሰዎች ይኖራሉ።

ነገር ግን እግዚአብሔር ሌሎችን ወደ እምነት ያመጣል፣ እናም ያንን የህይወት መድኃኒት የሆነውን የተሰቀለውን እና ከሞት የተነሳውን የክርስቶስን መልእክት ስላካፈላችሁ ያመሰግኗችኋል። ስለዚህ ያንን መልእክት ለሌሎች በማካፈል ያለውን ድንቅ እና ደስታ ተለማመዱ። አዎን ሂዱ እና ስበኩ::

እንፀልይ ፦
ውድ ጌታ ሆይ፣ ከአንተ ጋር በሰማይ ለደስታ ሕይወት ስላዳንከኝ አመሰግንሃለዉ። በአስደናቂው ፍቅርህ አነሳስተኸኝ ሄጄ ስለ አንተ ለሌሎች እንድናገር እርዳኝ!
አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #May_7_2022 #Tuesday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


የእለቱ ጥቅስ📖

" ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።"
የዮሐንስ ወንጌል 20:26

የትንሳኤው ሰላም

አንዳንድ ጊዜ ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ህይወት በጣም ቀላል እንደነበር ሊመስለን ይችላለን፤ ምክንያቱም ኢየሱስ እዚያው ከእነርሱ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ቆሞ ነበር። ይሁን እንጂ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኢየሱስ ወደ ሰማይ እንደሚያርግ እና ደቀ መዛሙርቱ የእርሱን አካላዊና የሚታይ መገኘት ማግኘት እንደማይችሉ አትርሱ። በገባው ቃል ላይ መታመን ነበረባቸው። እናም እነዚያ ተስፋዎች በዚያን ጊዜ ለደቀመዛሙርት እንደነበሩት ሁሉ ዛሬም ለእኛ የሚያጽናኑ እና አስተማማኝ ናቸው።

ኢየሱስ በእኛ ቤት ወይም በሕክምና መጠበቂያ ክፍሎች ውስጥ በድንገት አይገለጽልንም፣ ነገር ግን ይህንን ቃል ኪዳን ሰጥቷል፡- “እኔ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ” (ማቴዎስ 28:20) እና “ አልለቅህም፤ ከቶም አልጥልህም” (ዕብ 13፡5)

ህሊናችን በተነሳ ቁጥር የቆሰሉ እጆቹን ለማሳየት የልባችንን በሮች እያንኳኳ፡፡ ይልቁንም “ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ” (መዝ. 103፡12) ኃጢአታችን ከእኛ እንዲሁ እንደተወገደልን ቃል ገብቷል።


እንፀለይ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ደካማ ወይም ብቸኝነት ሲሰማኝ፣ አንተ ቅርብ እንደሆንክ አስታውሰኝ። በደለኛ ሕሊና ሲያስጨንቀኝ ለኃጢአቴ ዋጋ እንደከፈልክ አስታውሰኝ። ስጎዳ ፍቅርህን አስታውሰኝ። ያንኑ ፍቅር ለሌሎች እንዳካፍልም እርዳኝ።
አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #May_4_2022 #Tuesday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


የእለቱ ጥቅስ📖

"19፤ ያም ቀን እርሱም ከሳምንቱ ፊተኛው በመሸ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተሰብስበው በነበሩበት፥ አይሁድን ስለ ፈሩ ደጆቹ ተዘግተው ሳሉ፥ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። 20፤ ይህንም ብሎ እጆቹንም ጎኑንም አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። ... 24፤ ነገር ግን ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም። 25፤ ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ። ጌታን አይተነዋል አሉት። እርሱ ግን። የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም አላቸው። 26፤ ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። 27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው። 28፤ ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። 29፤ ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው። "
የዮሐንስ ወንጌል 20:19,20,24-29


ውድ ጓደኞቼ፤ ክርስቶስ ሞቷል። ክርስቶስ ተነስቷል። ክርስቶስ ዳግም ይመጣል። በአካል እዚያ በቀራንዮ ኮረብታ ወይም በተዘጋው ክፍል አልነበርንም፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ ያላሰለሰ ጥረት ሁሉም ነገር እንደተፈጸመ ያሳምነናል። በእውነቱ, በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ከእኛ ጋር የተካፈለው ነገር ሁሉ "ኢየሱስ መሲህ, የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ, እና አምናችሁ በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ" (ቁ. 31) ተጽፏል.

ክርስቶስ እንደሞተ እናምናለን። እንደገና ወደ ሕይወት እንደተመለሰ እናምናለን። እንደገና ከእርሱ ጋር ሊወስደን የሚመጣበትን ጊዜ በእምነት ዓይን እንድንመለከት የሚያስችለን ይህ ነው። ይህንን የመዳናችንን እውነት በመመስከር፣ ይህንን የምናውቀውንና የምናምንበትን እውነት ለሌሎች ለማካፈል በድፍረት ወደ ፊት እንጓዛለን!


እንፀልይ:-
የተወደድክ ኢየሱስ ሆይ፣ ፊት ለፊት አይተንህ ሳለ፣ በመቃብር ላይ ያለህን ድል በመጽሐፍ ምስክርነትህ ገልጠህልናል። ልባችንን እና ህይወታችንን በዚህ ዘመን በማይሽረው እውነትህ ሙላ እና አንተ በመኖርህ እኛ ደግሞ እንኖራለን የሚለውን እውነታ ለሌሎች ስናካፍል የመተማመን መንፈስን ስጠን።
አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #May_4_2022 #Tuesday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


የእለቱ ጥቅስ📖

"ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።"
የሐዋርያት ሥራ 5:29

ጴጥሮስና ሐዋርያቱ እኛ ድፍረትን በምናገኝበት ቦታ ማለትም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ አግኝተዋል! የሮማ ወታደሮች እሾህ ዘውድ አድርገው በትከሻው ላይ መስቀል ሲያነግቡበት ኢየሱስ ተረከዙ ሲቆለመም አከርካሪውም ሲደነዝዝ ማየት ትችላለህ። በቆራጥነት እና በድፍረት ኢየሱስ ፌዝን፣ መከራን፣ እና እንዲያውም የጭካኔ ስቅለትን አይቷል። በድፍረት ሞቷል። በድል ተነስቷል። እኔን እና እናንተን "ምስክሮቼ ትሆናላችሁ" ይለናል።

ይህ ደፋር ኢየሱስ ኃጢአታችንን ወደ መስቀል ተሸከመ፤ አሁን ደሞ እኛ ስሙን ለአለም እንድንሸከም ይጠይቀናል። አንዳንዶች ለዚህ ያመሰግኑናል። አንዳንዶች ዝም እንድንል ይገፋፋሉ። ከኢየሱስ ብቻ በሚሆነው ብርታትና ጉልበት፤ በጭካኔ ጥርሳችንን ነክሰን ስለ ኢየሱስ መስበካችንን እና ማስተማራችንን እንቀጥላለን።

እንፀልይ
ጌታ ሆይ፣ ስለአንተ መማር በጣም ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጋር ፍቅርህን ለመካፈል ምስክርህ እንድሆን ነግረኸኛል። በራሴ ሳይሆን በአንተ ድፍረትን ስጠኝ። ስለ አንተ የማዳን ስራ እድሎችን ባገኘው ጊዜ ለመናገር እንድችል እርዳኝ።
አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #May_3_2022 #Tuesday

ተቀላቀሉን:-
https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


Forward from: ህይወት በክርስቶስ ❤️❤️🙏🙏✝✝
ይሄን ብይዝ ያረካኛል ፤
እሱን ይዞ ሌላ ይመኛል ።
አዲስ የለም ሁሉም ከንቱ ፤
ሰው አፈር ነው እንኳን ሃብቱ።


ᴊᴏɪɴ ᴜs ፦ (https://t.me/jw255)


የእለቱ ጥቅስ📖

"5 ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ 6 መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
የዮሐንስ ራእይ 1:5-6


ዮሐንስ ካህን ነን ሲልህ፣ እያንዳንዳችን የተለየ የሕይወት ዓላማ እንዳለን እያስታወሰን ነው። የቀን ስራችን ነርስ፣ ሂሳብ ሹም፣ አስተማሪ ወይም መካኒክ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የህይወት አላማችን ሌሎች የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ቸርነት እንዲያዩ መርዳት፣ ስለሌሎች መጸለይ እና ለእግዚአብሔር መስዋዕቶችን ማቅረብ ነው። መስዋዕቶች ስንል፤ ለሌሎችን ደግ ቃላት በማሰብ፣ ለተቸገረ ሰው የሚረዳ እጅን በመዘርጋት፣ የሥራ ባልደረባችንን በመታገስ፣ በምስጋናና በእርካታ መንፈስ በመመላለስ እንዲሁም አጋጣሚውን ሲናገኝ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች ቃል ማካፈልን ማለት ነው። በእነዚህ መንገዶች ሁሉ ሌሎች የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዲያዩ እንረዳለን።

እንፀልይ:-
ጌታ ሆይ፣ ስላዳንከን እና የቤተሰብህ አባላት ስላደረግከን እናመሰግንሀለን። ለሌሎች ጥቅም እና ለአንተ ክብር በህይወታችን በምኖርበት መንገድ ሁሉ ምስጋናችንን እንድገልጽ እርዳን። አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #May_2_2022 #Tuesday


ተቀላቀሉንhttps://t.me/wl4all


የሰንበት ዜና
ቀን፡ ሚያዝያ 23, 2014 ዓ.ም

ከሞት የተነሳው የክርስቶስ ምስክሮች ለመሆን የመጨረሻው ዝግጅት የሚጀምረው በእይታ ነው። ሐዋርያት ከሞት የተነሳውን ጌታ በማየት ተባርከዋል። ጥርጣሬያቸውን በመንፈስ ኃይል በማሸነፍ ሕያው በሆነው ውስጥ ያለውን አዲስ ሕይወት በድፍረት ያውጁ ነበር። የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ራእይ በእምነት አይን በማየታችን የተባረክነውን እኛን “ክርስቶስ ሞቷ! ክርስቶስ ተነስቷል!" በሚል አይነት እምነት ልባችንን ይሞላል::

የእለቱ መዝሙር ፦
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 16 (ቢቻል በዜማ)

የብሉይ ኪዳን የንባብ ክፍሎች
ዘፍጥረት 15፡1-6

የአዲስ ኪዳን የንባብ ክፍሎች ፦
የሐዋርያት ሥራ 5፡12-32
የዮሐንስ ራዕይ 1፡4-18
2ኛ ጴጥሮስ 1፡16-21

የወንጌል የንባብ ክፍል
የዮሐንስ ወንጌል 20:19-31

የእለቱ ጥቅስ
"ሃሌሉያ። ሃሌሉያ። ክርስቶስ ተነስቷል! በእርግጥም እርሱ ተነስቷል! ሃሌሉያ። ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው። ሃሌሉያ "
(የዮሐንስ ወንጌል 20:29)

ተቀላቀሉን፦ https://t.me/wl4all


ስለሞቱ እና ትንሳኤው የሚያስታውስ መዝሙር


ተነስቷል ተነስቷል
የመቃብር ደጃፍ ተስፍቷል
ድንጋዩም በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነዉ አሰክሬኑ የታል
በእውነትም የሱስ ተነስቷል



ለቁጥር 4 ትክሩት እንድተሰጡ እንመክራለን

ተቀላቀሉን: https://t.me/wl4all


የእለቱ ጥቅስ📖

"51,52 እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን። ... 54 ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ። ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። ... 57 ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።"
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:51,52,54,57

የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው፣ ግን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት፣ ኢየሱስ የኃጢአትን እርግማን ተሸከመ። የኃጢአት ኃይል ሕግ ነው፣ ግን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት፣ ኢየሱስ የሕግ ፍላጎቶች አሟልቷል። ኢየሱስ ሲሞት የኃጢአታችንን ዋጋ ከፍሏል፣ ህግን ፈፅሟል፣ ሞትን ድል ነስቶ፣ ነፍሳችንን ብቻ ሳይሆን ሰውነታችንንም አዳነ።

ኢየሱስ ሕያው ስለሆነ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ቢሞቱም ከእርሱ ጋር ለዘላለም ይኖራሉ። ነገር ግን እነዚህ ሟች፣ የሚበላሹ፣ በኃጢአት የተነደፉ ባህሪያት ለዘለአለም ህይወት አልተፈጠሩም። ማሻሻያ ይደረግላቸዋል። የኢየሱስ ትንሣኤ እድገታችን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ያረጋግጣል። አዎን፣ ኢየሱስ መዳናችንን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ፈጽሟል፣ ግን አንድ ቀን በእኛ ውስጥ ደሞ በትንሳኤ ይፈጸማል።

ኢየሱስ በመጨረሻው ቀን ቀንደ መለከቶች ሲነፋ የኃጢአትን መርዝን በመቀልበስ ሞት የሚያስከትለውን ውጤት ያስወግዳል። መቃብርን ሁሉ ቀድዶ ሙታንን ሁሉ ያስነሣል። በጌታ ታምነው የሞቱ ሁሉ ይለወጣሉ። አሮጌው አካል አዲስ አካል ይሆናል። የእኛው አካል ሆኖ ግን የማይሞት፤ የማይበላሽ፤ ለዘለአለም ህይወት የሚቆይ ሆኖ ይለወጣል።

እንፀልይ:
የተነሣኸው አዳኜ፣ በኃጢአትና በሞት ላይ ስላሸነፍከው ድል አመሰግንሃለሁ። እኔም ለመንግስትህ እንድበቃ እንዳኝ። አሜን!

#DailyDevotion #April_29_2022 #የእለቱጥቅስ @wordoflife4all

ተቀላቀሉን: https://t.me/+ne2ccHuzI20wOGQ0


Forward from: ህይወት በክርስቶስ ❤️❤️🙏🙏✝✝
አይመስለኝም ነበር ጌታ ያለው የሚፈጸም
ኑሮዬን ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ ያለው ግን ይሆናል
እርሱ መች እንደ ሰው ተናግሮ ዝም ይላል

ᴊᴏɪɴ ᴜshttps://t.me/jw255


ከእለቱ ጥቅስ ጋር የሚሄድ መዝሙር

ከእንግዲህ ሞት የለም፤
ጌታ ትንሳኤ ነው
ከእንግዲህ ሞት የለም፤
ጌታ ትንሳኤ ነው
ህይወት ነው ዘላለም፤
ኢየሱስ ላመነው
ህይወት ነው ዘላለም፤
ኢየሱስ ላመነው


ለሁለተኛው ቁጥር ትኩረት እንድተሰጡ እንመክራለን


የእለቱ ጥቅስ📖

"6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል። 7 በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል። 8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፥ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፥ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና። "
ትንቢተ ኢሳይያስ 25:6-8

ኢየሱስ አሁንም እስከ ምጽአቱ ቀን ድረስ ይነግሣል። በዚያች የድል ቀን ደግሞ ሙታን በሕይወት ይኖራሉ። ይህ አዲስ ሕይወት ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ብቻ አይደለም። በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር ባሰበው መሠረት የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ። አእምሮአችንን በመልካም ነገሮች ሁሉ የሚያጥለቀልቅ ሕይወት ይሆናል።

ምንም የጠፋብን ነገር የለም፣ ሁሉም ነገር የጠፋ በሚመስልበት ጊዜም እንኳ፤ ሁሉ አለን ምክንያቱም ኢየሱስ በሕይወት ስለሚኖር! ትንሣኤው በጣም የሚያሠቃየውን የሰው ልጅ ክስተቶች እንኳ ለሕዝቡ ወደ በጎነት እንደሚለውጥ ዋስትናን ይሰጣል።

ስለዚህ ብርጭቋችንን አንስተህ የድሉን ዝማሬ እንበል፡- “እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።" (ኢሳይያስ 25:9)

እንፀልይ:-
ኢየሱስ ሆይ፣ ከኃጢአት፣ ከጥርጣሬ፣ ከሐዘንና ከሞት መቃብር ከአንተ ጋር ውሰደኝ። እናም ከድልህ፣ ሕይወትህ፣ ደስታህ እና ክብርህ ጋር እንድካፈል እርዳኝ። አሜን።

#DailyDevotion #April_28_2022 #የእለቱጥቅስ @wordoflife4all


የእለቱ ጥቅስ📖

"4 እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤ 5 ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። 6-7 የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ።
የሉቃስ ወንጌል 24:4-6


ኢየሱስ እዚህ የለም ምክንያቱም ተነስቷል እና ወደ እግዚአብሔር ቀኝ አርጓል። በዚያ መኖሪያ ሊያዘጋጅልን ሄዷል። ነገር ግን ለእኛ ቦታ ለማዘጋጀት ሄደ ማለት፤ ተመልሶ ይመጣል ማለት ነው ::

እስከዚያ ድረስ፣ አሁንም እንፈራለን፣ እንከፋለን፣ እንናደዳለን። ነገር ግን በችግር ጊዜአት የተከፈተልንን ቃል ኪዳን መዘንጋት የለብንም። ኢየሱስ ከዓይኖቻችን ተሰውሮ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሁልጊዜ በቃሉ ውስጥ ልናገኘው እንችላለን። በዚያም በሰላሙ፣ በደስታው፣ በእርካታው ፣ በጸጋው እና ለእኛ መልካም እንደሚሰራልን በገባው ቃል በጊዜው ይገናኘናል።

በጥርጣሬ፣ በፍርሃት፣ በህመም እና በሀዘን አንቆይም። በመቃብርም አንቆይም። በሚጠፋው ሰውነታችን ውስጥም አንቆይም። በዚህ ምድር በኃጢአት ሸክም እየቃተትን አንቆይም ነገር ግን ተመልሶ ሲመጣ ከክፉ ነገር ሁሉ በጸዳች አዲስ ምድር ከእርሱ ጋር እንድንኖር ይወስደናል።

እንፀልይ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ እንዳልከው በዚህ ባለመሆንህ እና ከሞት በመነሳትህ በጣም ደስ ብሎኛል። ይህም የገባኸውን ቃል ሁሉ እንደምትፈጽም መታመን እንድችል ያደርገኛል። ስለዚህ ለቃልህ ፍጻሜ እንድደርስ እርዳኝ:: አሜን።

#DailyDevotion #April_27_2022 #የእለቱጥቅስ @wordoflife4all


የእለቱ ጥቅስ📖

"5 ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ 6 መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
የዮሐንስ ራእይ 1:5-6


ዮሐንስ ካህን ነን ሲልህ፣ እያንዳንዳችን የተለየ የሕይወት ዓላማ እንዳለን እያስታወሰን ነው። የቀን ስራችን ነርስ፣ ሂሳብ ሹም፣ አስተማሪ ወይም መካኒክ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የህይወት አላማችን ሌሎች የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ቸርነት እንዲያዩ መርዳት፣ ስለሌሎች መጸለይ እና ለእግዚአብሔር መስዋዕቶችን ማቅረብ ነው። መስዋዕቶች ስንል፤ ለሌሎችን ደግ ቃላት በማሰብ፣ ለተቸገረ ሰው የሚረዳ እጅን በመዘርጋት፣ የሥራ ባልደረባችንን በመታገስ፣ በምስጋናና በእርካታ መንፈስ በመመላለስ እንዲሁም አጋጣሚውን ሲናገኝ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች ቃል ማካፈልን ማለት ነው። በእነዚህ መንገዶች ሁሉ ሌሎች የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዲያዩ እንረዳለን።

እንፀልይ:-
ጌታ ሆይ፣ ስላዳንከን እና የቤተሰብህ አባላት ስላደረግከን እናመሰግንሀለን። ለሌሎች ጥቅም እና ለአንተ ክብር በህይወታችን በምኖርበት መንገድ ሁሉ ምስጋናችንን እንድገልጽ እርዳን። አሜን።

#DailyDevotions #የእለቱጥቅስ #April_26_2022 #Tuesday @wordoflife4all

20 last posts shown.

75

subscribers
Channel statistics