Abdil halim shayk abdil hamid


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ሐቅ እንጂ ሰው አትከተል
የባጢል ዘመድ የለም የሐቅ ባዳ የለም
ሐቅን የትም ካገኘሃት ተከተላት
ጉድ ኡኮ ነው
የተለያዩ እውቀቶችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማለት ይቀላቀሉ ↘↘↘↘↘↘↘↘↘↘↘↘
https://t.me/joinchat/

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


عبد الفتح:
// ኢስላማዊ ግጥም //

// ርዕስ //
\\መውሊድ\\

/\ክፍል ➊/\
_________________
💭ሙብተዲዕ ጠማማ ቢድዓውን ፈጥሮ
💭ሊያጠምህ ሲመጣ አትስማው ዘንድሮ
💎ስለመውሊድ ጉዳይ ግጥሜን ገጥሜ
💎ይዤ መጥቻለው☞አንብባት ወንድሜ
🌹መውሊዱ አይደለም ለረሱል ውዴታ
🌹የመብያ ነው እንጂ አይቤ በገበታ
🌹ከየት አለ ውዴታ ሲጥሱ ትዕዛዝ
🌹የመብያ ነው እንጂ ድንችና ሩዝ
🌹ሳያከብሩ ቃል ከየት መጣ ውዴታ
🌹ፈልጎ ነው እንጂ የጫቱን ጀባታ
🌹የት አለ ውዴታ ሀራም እየሰሩ
💎ለጂኒ እያረዱ ሙታን እየጠሩ
💎ወደድኩ እያሉ ቢቀበጣጥሩ
💎ውጤቱ ባዶ ነው ዜሮ ነው ድምሩ
💎ለረሱል ውዴታ መውሊድ ቢያስፈልግ
💎ነቢዩን በመውደድ •°•°•የደረሱት ጥግ
💎ያከብሩት ነበረ•°•°•°•° ሰሀቦች በወግ
መውሊድ ምታከብረው የሸርኩን ክምር
// አረ አላህን ፍራ ሰው አታጭበርብር
💎የናፈቀህ ማነው ☞ እውነቱን ንገር
💎ረሱል ናቸው ወይስ ☞የጀባታው ብር
💎የቅቤው ቡናና ☞ ☜ የጫቱ ክምር
💎ስጋው እና አይቤው__ በሰው መዘየር
💎የቱ ነው ናፍቆትህ ሳትዋሽ ተናገር?
💎ወንድም አትፎገር •°•°•ለአህባሽ ብዥታ
💎የሚያስፈልገው °•°•° ለረሱል ውዴታ
💎ሱና መከተል ነው ሳይለቁ አንድ አፍታ
💎የሽርክ መናሀሪያ የዝሙት አውድማ
💎በመውሊድ ነው ያለው ወንድሜ ሆይ ስማ
💎ዝሙትን ፈልጎ መውሊድን ሚናፍቅ
💎አብዘኃኛው ወጣት መሆኑን እወቅ
💎ጫቱን ወታትፎ ቢጮህ ቢቅለሰለስ
💎መንዙማውን ከፍቶ ቢያድር ሲደንስ
💎በምርቃናው ብዛት እንባ ቢያፈስ
💎ጋልቦ ነው እንጂ ☞ የሸይጧን ፈረስ
💎ነቢዩን መች ወዶ ☞ አረ ይቀንጠስ
💎እሄን አይነት ወዳጅ ደጄን እንዳይደርስ
💎መሀባ መች አለ ትዕዛዝ ሳይከበር
💎ይገለፅ የለም ወይ ውዴታ በተግባር
💎ሴት ወንዱን ቀላቅሎ ዲቢ ሲያስመታ
💎ንገሩኝ ውዶቼ•°•°•°•° የት አለ ውዴታ
✔እራሱንም ቢስት ቢያጉረመርም
✔ወደድኩኝ እያለ-አዳሩን ቢጮህም
✔ጎሮሮውን አልፎ ልቡ ጋ አይደርስም
✔የረሱል መሀባ በውስጡ የለም
ነቢዩን በመውደድ የሚበልጡት ከእኛ
አቡ በክር ዑመር ....ታማኙ እውነተኛ
ኡስማን እና አልይ ... የረሱል ጓደኛ
መች ሰርተው አሳዩን እንድንሰራው እኛ
~~አባቷን ወዳጇ ~ ከሁሉ አስቀድማ~•
~~መች አከበረችው ልጃቸው ፋጢማ~•
✔መሀመድስﷺጭራሽ መች አከበሩት
✔የተወለዱበትን ቀን ፁሙት ነው ያሉት
✔እሱ አሁን መጥቶ ከሺ አመት በኋላ
✔መውሊዱን ሊያከብር ጫቱን እየበላ
✔ሽርክን ሲያጨማልቅ በመሀባ ጥላ
✔ውዴታው በልጦ ነው ከሰሃቦች ሁላ¿?
✔ከአባቱ በላይ አውቃለው ማለቱ
✔ቡዳነት ነው አሉ ሰዎች ሲተርት
✔ያ ሁሉ ሰሃባ __ ያ ሁሉ ታቢዕይ
✔አትባዑ ታእቢዮች ኢማሙ ሻፊዒይ
✔አቡ ዳውድ መስሊም ቡኻሪ ነሳኢይ
✔ኢብኑ ማጀህ አህመድ ታላቁ ቱርሚዝይ
✔አከበሩት የሚል ማስረጃ አለወይ??
✔ማስረጃው የት አለ - አዩሀል አህባሺይ
✔ማስረጃው የት አለ --ያ መዕሸረ ሱፊይ
✔በኖርማል አዕምሮ አምጡት እንዲታይ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0
~~~~~


// ክፍል ➋ //
#ይቀጥላል

አቡ ያሲር _አብዱል ፈታህ


بسم الله اارحمن الرحيم

ይህን ቢያዩ ምን ይሉ ነበር?!

እስኪ ለአንድ አፍታ አስቡት።
በዘመናች ያሉ ዘርፈ ብዙ መጤ አመለካከቶችን እና መሪዎቻቸውን ቢያዩ እነዛ የኢስላም ጀግኖች ምን ይሉ ነበር?!
በዲናችን ቢደዓ ሁሉ ጥመት መሆኑን ከመልዕክተኛው
(عليه الصلاة وسلام)
የተረዱ የአሏህ ተማኝ ባሮች ለምሳሌ:

👉 1, አብደላህ ኢብኑ መስዑድ

አላህን በመዘከር የተለየ አደራረግ ብቻ የፈጠሩ ሰዎችን አጥብቆ ያወገዘ።ጠፋችሁ ያላቸው።ዛሬ ላይ የሚደለቁትን የሽርክ መንዙማዎችን ጉድ ቢሰማ ምን ይል ነበር?! ጨፋሪዎቹንስ ?!

👉2 አብደላህ ኢብኑ አባስ

የነብዩን (عليه الصلاة وسلام) ንግግር ትተው የአቡበከርና ዑመርን ሀሳብ ለያዙ ሰዎች
《የድንጋይ ናዳ እንዳይወርድባችሁ እፈራለሁ》ብሎ በጥፋት ያስፋራራቸው። ዛሬ ላይ በአደባባይ ቁርኣንና ሀዲስን ለተፃረሩ የጥመት መሪዎች ጭፍን ተከታይ የሆኑ እምቢተኞችን ቢያይ ምን ይላቸው ነበር ! ?

👉3 አብደላህ ኢብኑ ዑመር

በቀድር ኢማን ላይ ቢደዓ ያመጡ ሰዎች እንደተነሱ ሲነገረው《 እኔ ከነሱ የፀዳሁ እነሱም ከእኔ የፀዱ ናቸው።…) ብሎ ከቢደዓ ሰዎች ጋ ያለውን አቋም ያፀናው ጀግና ሰሃቢይ።
በዘመናችን በሁሉም የኢማን አርካኖች በቢደዓ የታጨቀ መዝሃብ ካነገቱ ጠማማ ጭፍራዎች ጋ በአደባባይ《 አንድ ነን በርቱ》ባዮችን ጉዳጉድ ቢሰማ ምንኛ ይቆጭ ነበር ?!

👌4:ሌሎች ሰሃቦች፣ታብእዮች፣አትባኡታቢዒን፣አኢማዎች (አህመድ፣ማሊክ፣አቡሀኒፋ፣አሸፊዕይ፣በርበሃሪ፣ሸይኩል ኢስላም ወዘተ) ያሉ የሱና ተቆርቋሪ አንበሶች።
ቢደዓን ባንድ ድመፅ አውግዘዋል የቢደዓ መሪዎችን በግልፅ አስጠንቅቀዋል።
በማያሻው ወጥ አቋማቸው ሰበብ አሏህ ባለድል አድርጓቸዋል።

ዛሬ ላይ ያሉ ሙብተዲኦችን ድፍረት የተሞላበት ጥመት እና ከነሱ ጋ የሚተሻሹ አወዛጋቢዎችን በዘመናቸው ቢገናኙ ምላሻቸው ምን ይሆን ነበር !?
የሚያውቀው ያውቀዋል።


አሏሁ ተዓላ ሱራህ ሁድ ውስጥ
ነብዩን (علي الصلاة وسلام) እና ተከታዮችን በታዘዙት መሰረት እንዲፀኑ ካዘዘ በኋላ አንዲህ አለ
【وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ】 (113)

ያ አህሉሱና ተከታዮቻችሁን ግራ አታጋቡ።እወቁ ወደ ቢዳዓ ሰዎች መዘንበል ውድቀትን እንጂ ድልን አያስገኝም። አጥማሚ መሪዎችን በተለይ አጋዥ አድርጎ መያዝ እንደሌለብን ሲጠቁመን አሏህ ሱራህ አልከህፍ ውስጥ አንዲህ ይላህ
【وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ الْمُضِلِّينَ عَضُدًا】(51)

ባለንበት ግዜ እነዚህና ሌሎች አንቀፆችን እናስተንትን።ሙፈሲሮች ያሉትን ልብ እንበል።በሂደታችን ሁሉ በዘመናችን ለሚከሰቱ አዳዲስ ጉዳዮች ታማኝ ኡለማዎችን እንጠይቅ።

አልሀምዱሊላህ ትክክለኛው መንሃጅ ላይ ያሉ ጀግኖች በየዘመኑ አሉ አይወገዱም።ከተለያዪ የጥመት አንጃዎች ጋ እንዴት እንደተኗኗሩ በጥልቀት ማየት ግድ ይላል።

አሏህ እውነተኛ ሰለፊይ ያድርገን!

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0

👒_____🍃🌹🍃______


ibnu shayk
*🖐 كلام اعجبني ................../ካስገረሙኝ ንግግሮች/ 🖐*

🔲 عندما تولد لا تعلم
من الذي أخرجك من بطن أمك
🔲 ስትወለድ ከእናትህ ሆድ ያወጣህን ፈፅሞ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لا تعلم
من الذي أدخلك إلى قبرك
🔳 ስትሞት ማን ወደ ቀብርህ እንዳስገባህ ፈፅሞ አታውቅም።

*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔳 عندما ولدت تغسل وتنظف
🔳 ስትወለድ ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።

🔲 وعندما تموت تغسل وتنظف
🔲 ስትሞት ትታጠባለህ፣ ትፀዳለህ።
*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ።*

🔲 عندما تولد لاتعلم من فرح واستبشر بك
🔲 ስትወለድ ማን በልደትህ እንደተደሰተ አታውቅም።

🔳 وعندما تموت لاتعلم من بكى عليك وحزن
🔳 ስትሞት ማን እንዳዘነና እንዳለቀሰ አታውቅም።

*🔲 عجبا لك ياابن آدم*
*🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔳 في بطن أمك كنت في مكان ضيق ومظلم
🔳 በእናትህ ሆድ ውስጥ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ነበርክ።

🔲 وعندما تموت تكون في مكان ضيق ومظلم
🔲 ስትሞት ጊዜ በጠባብ ቦታና በጨለማ ውስጥ ትሆናለህ።

*🔳 عجبا لك ياابن آدم*
*🔳 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ*

🔲 عندما ولدت تغطى بالقماش ليستروك
🔲 ስትወለድ በጨርቅ ትጠቀለላህ ሊሸፍኑህ!

🔳 وعندما تموت تكفن بالقماش ليستروك
🔳 ስትሞት በከፈን ይጠቀልሉሃል ሊሸፍኑህ!

🔲 عجبا لك ياابن آدم
🔲 የአደም ልጅ ሆይ! ትገርማለህ

🔳 عندما ولدت وكبرت يسألك الناس
عن شهادتك وخبراتك
🔳 በተወለድክና በአደግክ ጊዜ ሰዎች ምስክር ወረቀት ስለሙያህ ይጠይቁሃል።

🔲 وعندما تموت تسألك الملائكة عن عملك الصالح
🔲 በሞትክም ጊዜ መልዐኮች ስለመልካም ስራህ ይጠይቁሃል።

*🔳 فماذا أعددت لآخرتك ؟*
*🔳 ለመጨረሻው ሃገርህ ምን አዘጋጀህ?*

🔲 جرب تقولها من قلب :
آشهد آن لآ آله آلآ آلله
واشهد آن محمد رسول آلله
🔲 ከልብህ ይህችን (ቃል) ለመናገር ሞክር! ከአላህ ሌላ በፍፁም የሚመለክ አምላክ እንደሌለ መስክር። እንዲሁም ሙሃመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መስክር።

🔳 مستحيل تقرآها بدون ما ترسلها
🔳 ይህችን መልእክት ፍፁም ሳታነባት እንዳትልካት!

& & &
‏ بسم الله الرحمن الرحیم
*{ قل هو الله أحد * الله الصمد * لم يلد ولم يولد * ولم يكن له كفواً أحد }*

*ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ*
*{ በል! እርሱ አላህ አንድ ነው። አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱ አንድም ብጤ የለውም።

መልዕክቱን ላክ! ሰአትህን አስተውል🕗

كم شخص يقرأ ثلث القرآن 📘 بسببك لاتحرم نفسك مٍن الاجر
በአንተ ሰበብ የቁርዓን አንድ ሶስተኛን ይቀራሉ (ያነባሉ) 📘

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


🌿መውሊድ🌿

💥የረሱልም ሆነ - የመሲሁ ኢሳ
ልደት ሚባል የለም - ከሸሪዓ ማሳ።💥

💥ኡለሞች በማስተማር - ቢዚ የሆኑበት
ኩቱቦች በመፃፍ - ያስጠንቀቁበት።💥

💥የኢርቢሉ ንጉስ - በቅርብ የጀመረው
ጉድፍ የተመላ - መውሊድ ቢድዓ ነው።💥

💥ቢድዓ እንደሆነ - ሁሉም ተስማምተዋል
ሀሰና ሰይዓ - ብለው መድበዋል።💥

💥ሙስሊሙ ኡማ ሆይ - ስማኝማ ወገን
ማጣመምህ ለምን - ነብዩ ያሉትን።💥

💥ቢድዓ ሁሉ ጥመት - ጥመት ወደ እሳት
ገልፀዋል ረሱል - በሀዲሱ መልክት።💥

💥ሀሰና የለውም - ቢድዓ ጥመት ነው
ዛሬ ካልባነንን - መች ነው ምንነቃው።💥

💥ነብዩ አላሉም - ሰይዓ ሀሰና
ቢድዓን ትታቹ - ግቡ ወደ ሱና
ግድ የለሽ አንሁን - ቁንጣሪ መና
ህይወትን እንምራ - በሰለፎች ፋና።💥

💥መውሊድ ይከበራል - ኢድ ነው ብለህ ካልከኝ
መረጃህን አምጣ - በከንቱ አታድክመኝ።💥

💥የታል ያከባበሩ ዝርዝር - ከመረጃ ሰነድ
ዶሮ ወይስ በሬ - ሚሰዋው ለመውሊድ
የታል የኢድ ሰላት - ለመውሊድ ሚሰገድ
በል ንገረኝ አሁን - ሁሉን አንድ በአንድ
በጉንጭ አልፋ ሙግት - ሰዓታችን አይሒድ።💥

💥መረጃ ካጠረህ - መውሊድ ለምትለው
አንቺ ወሃብያ ን - ታዲያ ምን አመጣው።💥

💥መውሊድ ካላወጣሽ - ነብዩን አትወጂም
እያልክ አትወርፈኝ - ፈራጅ አይደለህም
ፈጠራ ሰርቼ - ሙብተዲዕ አልሆንም።💥

💥ከልብ ለመውደዴ - ማስረዳት አያሻኝ
በዲን ላይ ቢድዓ - ሳልጨምር እንዳሻኝ
ደሊል ተደግፌ - ኢባዳ ሰራሁኝ
ያለማንገራገር - ሱናን ተከተልኩኝ
ነቢን ለመውደዴ - ምላሽ እንዲሆነኝ።💥

💥እንዲያውም ልንገርህ - መውሊድ ብሎ ማለት
በመሰደቅ ሽፍን - ሚስኪን ሚልጡበት
የፍየሏ ቅጠል - ለጉድ ሚበላበት
ሰለዋት ተብሎ - የሚጨፈርበት
እንዘክር እያሉ - ድቤ ሚመቱበት
ወንድ ከሴት የማይለይ - ኢኽቲላጥ ያለበት
ስሜት በመከተል - ዘና የሚሉበት
መውሊድ ብሎ ማለት - ፈሳድ የሞላበት
የቢድዓ አውራ - ሚሸነግሉበት።💥

💥ለተራበ ሚስኪን - ሰደቃ ለማውጣት
ዚክር ለመዘከር - ለማውረድ ሰለዋት
ምን የሚሉት ፈሊጥ - መከፋፈል ቀናት
ያልተሰራ ኢባዳ - ካመት እስከአመት
ቀዳ ነው ሚወጣው❓በመውሊዱ ዕለት❓።💥

💥በዲን በሸሪዓ - በማይታወቅ ውል
ጥፋትን በላይህ - ከምታግተለትል
በምላስህ ብቻ - ወደድኩኝ ከምትል
ሱሪህን አሳጥር - አሳድግ ፂምህን
ፀጉር አታበላልጥ - ተወው መንዙማህን
የነብዩ ሱና - መገለጫህ ይሁን።💥

💥አንቺም የነቢ ወዳጅ - ተናፋቂ እንስቷ
ከመዝለልሽ በፊት - በነሺዳ እሩምታ።💥

💥ከወንዶች ራቂ - ቅልቅሉን ትተሽ
እንኳን ልታዜሚ - አይሰማ ድምፅሽ
በኒቃብ ተዋቢ - ሜካፑ ይቅርብሽ።💥

💥ባጢል ከነገሰበት - ከፈሳዱ መድረክ
ሰተር በይ እቤትሽ - ክብርሽ አይፍረክረክ።💥

💥ሒጃቡን ልበሺ - ይሸፈን ውበትሽ
ከቀልብ በሽተኛ - ይሁን መጠበቂያሽ።💥

💥ረሱልን እንደወደዱ - እንደ ሰሀብያት
ቤትሽ ይስፋሽ ላንቺ - ደጅ ላይ ከመውጣት።💥

💥ከሰለፉነ ሷሊህ - ተቀድቶ አቂዳቹ
ከሰለፍዮች ጋር - ከተደመራቹ
ከአህባሹ መንጋ - ከጥመት ወታቹ
ሱናውን ስትሰሩ - ቢድዓ ትታቹ
ወደድን ስትሉ - አሁን አመናቹ።💥

💥በጣም ያስደንቃል - መጣረሱ ወቅቱ
ቋሚ ጊዜ - የለው በየሀገራቱ
ቅጥ አምባር የጠፋው - የቃጥባር አብሬቱ
የሚወጣው መውሊድ - አይነቱ ብዛቱ።💥

💥ኧረ ምኑ ቅጡ - አያልቅም ቢወራ
ክፍተቱ ማየሉ - የመውሊድ ፈጠራ።💥

💥ፊታቸው ገርጥቶ - አይናቸው እስኪያብጥ
ነብዩን ያስቆጣ - ሚንበሩ እስኪናጥ።💥

💥በእርሳቸው ዘመን - ባልተከሰተበት
ዑማው እንዲርቀው - ቆመው ያስተማሩት
ለቢድዓ እኮ ነው - የተንዘፈዘፉት።💥

💥አዲስ ምናመጣው - ምኑ ተያዘና
ስሩ የተባለውን - መቼ ጨረስንና።💥

💥ሰው ሰራሽ የሆነ - አዳዲስ ፈጠራ
አንድ አያደርገንም - ማንም ቢያወራ።💥

💥ቢድዓ እስከሆነ - የ'ውነት ይለየናል
ሱናውን እንያዝ - አንድነት ይመጣል።💥

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ

ያጀመኣ።

አጭር መልእክት ይዥ መጥቻለሁ።

↓↓↓↓↓

→→→→ ምኞቴ ←←←←

↑↑↑↑↑


ዛሬ ነገ ሳልል ከወንጀል ታርሜ፣
አላህን በመፍራት እስቲግፋር አድርጌ፣
በእስልምና ድባብ ሰምሮልኝ ህይወቴ፣
አቂዳዬ ሰምሮ በተውሂድ አብቤ፣
አድስን ከመፍጠር ሁሌ ተቆጥቤ፣
ጀርባዬን ካላዞር በሱና ላይቆሜ፣
ሳልገለባበጥ በድኔ ፀንቼ፣
መቆየት ብቻ ነው እስከለተ ሞቴ፣
ዱኒያን እስክላቀቅ ወዳሄራ ቤቴ፣
ከሸይጧን ውስወሳ በአላህ ተጠብቄ፣
ከታማኝ የዲን ሰው የድን ሀቅ ፈልጌ፣
እሷን በመጨምደድ ከባጢል እርቄ፣
አላህ ዘንድ መጓዝ ነው ይሄው ነው ምኞቴ፣
ጀነትን መውረስ ነው ከእሳት አምልጬ፣
በአራህማን እዝነት ሰበቡን አድርሼ፣
ከጀነት መግባት ነው ይሄው ነው ምኞቴ
ከአርሽጥላ ስር መዋል ነው ምኞቴ።

ያአላህን ውዴታ ማገኘት ነው ሁሌ፣
ስንቄን ሰናንቄ ለወዳኛው ቤቴ፣
ዛሬ ነገ ሳልል ጀነት ነው ምኞቴ።3

ሌሎች ግጥሞች ይቀጥላሉ።
ከቻሉ ሼር ያድርጉት። እርሰዎም ጆይን ያድርጉን

በቴሌግራም↓
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


"አነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፡፡

ሐዲስን እነግራችኋለሁ ከኔ ውጭ ሌላ ማንም ሊነግራችሁ የማይችለውን ሐዲስ፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- ‹‹የትንሳኤ (የቂያማ) ቀን መድረስ ምልክቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

1) የዕውቀት ማነስ፤
2) መሃይምነት መስፋፋት፤
3) ዝሙት በግልጽና በስፋት መፈጸም፡፡
4) የሴቶች አሀዝ መብዛትና የወንዶች ቁጥር ማነስ አንድ ወንድ ሀምሳ ሴትን ማስተዳደር እስኪኖርበት ድረስ፡፡

~ ቡኻሪ ዘግበውታል

--------------------
abdil halim ibnu shayk
-----------------------------
🍀🍀🍀
በቴሌግራም ይ🀄️ላ🀄️ሉን!
➢👇👇👇
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


እስስቶች

መልኳን ምትቀያይር የሆኘች እስስት፣
ያዙኝም ትላለችበመስለሀ ሰበብ ኑ ወደአንድነት፣
ልታስገባ እሳት፣
ተደምራ ከጥመት፡፡
ከኢኽዋኖች ጋር ስር ስር ትሄዳለች፣
ምንድነው ስትባል በመስለሀ ሰበብአንድነት ትላለች፡፡

የሷ አንድነት ቢሆንማ፣
መደመር ነው ከጠማማ፡፡

ተውሂድን ሳትይዝ፣
ሽርክን ሳታወግዝ፣
ሱናን የምታቀጭጭ፣
ቢድዐቸወንም ምታሰራጭ፡፡

ውሎዋ ከኢኽዋን፣
ፖለቲካ ስትጭር፣
በሱፍ ተወጥራ፣
እንደው ምትኩራራ፡፡

አሉ ልክ ነው ሱናን የሚያቀልጡ፣
በሰለፍዮች መሀል የሚያበጣብጡ፣
የሱና ሰዎችን የሚያቀላልጡ፣
ሰለፍይነት ያልገባቸው እንዲው ቅጥ ያጡ፣
ኸረረ ሰለፍዮች ከነሱም ራቁ፣ አብራቹ ሆናቹእንዳትቀላልጡ።
✍UMU RESLAN

T.me/UmuReslan_Aselefiya


#ጁለይቢብ

ፊደሉ ያልተሟላ የጎደለ ስም፣
አጭር ወይም ትንሽ ሚሰጠን ትርጉም፣

ድንክዬ መሆኑ ነው ሚያመለክተን፣

የሚሰኝ ሲሆን ስሙ ጁለይቢብ፣
አይቀላቀልም ካለው ህብረሰብ፣

መልከ ጥፉ ነበር በዛ ላይ ቁመቱ፣
ሚያስጠጋው የለም በሱ ማንነቱ፣
አይታወቅም ነበር ጎሳው ሆነ አባቱ፣
ከሱ ሚታወቀው አረብ መሆኑ ነው በአንሷርነቱ፣

በሰብአዊነቱ ተከብሮ የሚያየው፣
በችግሩ ጊዜ አብሮ የሚሆነው፣
በደስታውም ጊዜ አብሮ ሚቋደሰው፣
ታይቶ አይታወቅም ኑሮን ሚካፈለው፣

ዘር እና ቀለምን የማይለየው እምነት ፣
ሚያስተምረውን ሁሉን በእኩልነት፣
ቀይሮት ተገኝቷል የእሱን ማንነት፣
ኢስላምን ሲቀበል የረሱልን እምነት፣

ቦታ ማይሰጡት ሰው በአትኩሮት በልብ ፣
ነብዩ አልረሱትም አላረጉት ገይብ፣

መልክተኛው ሄደው ከ1አንሷር ቤት፣
ልጅህን ለትዳር ፈልጌያለው አሉት፣

አንሷሩም በፍሰሀ በደስታ ተሞልቶ፣
እያለ ይሄን እድል ማን ያገኛል ከቶ፣
አስደሳች ዜና ነው አለ ፊቱ ፈክቶ፣

ነቢም ፈጥነው አሉት ለኔ እንዳይመስልህ፣
በቀዘቀዘ ድምጽ ታድያ ለማን ይሁን ንገረኝ እባክህ፣

ሰውዬው ቸኩሎ የልጁን ማንነት፣
ለጁለይቢብ ነው ብለው መለሱለት፣

በድንጋጤ ብዛት የፈዘዘው አንሷር፣
በማለት መለሰ ቆይ ሚስቴን ላማክር፣

ለሚስቱም ሲነግራት ረሱል እንደመጡ፣
ልጃቸውን ፈልገው ለትዳር እንዲሰጡ፣

በደስታዋ ብዛት ማሻአላህ አለች፣
ስሜቷን ለመግለጽ እየተቻኮለች፣

ባሏ ግን መለሳት ለርሳቸው አይደለም፣
ለጁለይቢብ ነውለማይታወቀው ሰው፣
ፊቷ እየጠቆረ በንዴት ብዛትም
በአላህ ይሁንብኝ ለሱ አልድራትም፣

አባት ሊናገር ሲል አቋማቸውን፣
ልጅ ጭምጭምታ ሰምታ ሚናገሩትን፣

ለማን ልዳር ነበር? በማለት ጠየቀች ከመቀመጫ ላይ ፈጥና እየተነሳች

ነብዩ ለጁለይቢብ እንደጠየቋቸው፣
አጋር እንድትሆኚ በሂይወት ለሣቸው፣

አዘነች ልጂቱ በጣም ተረቀሸች ፣
ወደሳቸው ላኪኝ አታክስሪኝ አለች፣

የነብዩን ጥያቄ ውድቅ ብታደርጊ፣
ይቅር አልልሽም ምንም ብታደርጊ፣

አለቻት ልጂቱ ኢማን የገባት፣
በደንብ የተረዳች የኢስላምን መልእክት፣

የታጨችውም ልጅ አድርጋ በግልጽ፣
አነበበችው የቁርአን አንቀጽ፣

የአላህ መልእክተኛ ይበጅሻል ካሉኝ፣
አልቀበላቹም ይቅርብሽ ብትሉኝ፣

ሁሉንም በደስታ እቀበለዋለው፣
በተግባርም ጭምር እሰራበታለው፣
አለች የአንሷሩ ልጅ ተስማምቼአለው፣
ረሱልም ከሷ አፍ ይህንን ሲሰሙ፣

ጌታዬ ሆይ ጥሩውን ለርሷ አድርግላት፣
ችግርና መከራን ከሂወቷ አርቅላት፣
በማለት አላህን ዱአ ለመኑላት፣
እንደርሷ በትዳር ተስማሚና ብቁ ከአንሷር ሴቶች ውስጥ አልነበረም እንቁ፣
እስኪለያት ድረስ ጁለይቢብ በሞት፣
ይኖሩ ነበረ አብረው በሀሴት፣

በአንድ ወቅት ጁለይቢብ ከነብዩ ጋር፣
ከሙሽሪኮች ጋራ ሊገጥሙ በጦር፣

ጦርነቱ አልቆ በድል ተወጥተውት፣
ረሱልም ጠየቁ የጠፉት በማለት፣

ሁሉም እገሌ ይላል ዘመድ ጓደኛውን፣
ይቆጠር ጀመረ የሌለ ያለውን፣
ነብዩ እየዞሩ ቢጠይቁ ሁሉን፣
የሚመልስ የለም ካልሆነ ወዳጁን፣

ረሱል በመጨረሻ እንዲ ብለው አዘዙ፣
ጁለይቢብ ጠፍቶኛል ማን ያምጣ ጎበዙ፣

ከ7ከሀዲያን ጎን ወድቆ አገኙት፣
በጁለይቢብ አስክሬን ቆመው ከፊትለፊት፣
ሰባት ገድሎ ተገደለ እሱ ከኔነው እኔም ከሱ ነኝ አለ፣
እቺን ወርቃማ ቃል 3ጊዜ ደገሟት፣
በጃቸው አቅፈው ከመሬት አነሱት፣

ሸሂድ ነውና በመስዋትነቱ፣
ሳይታጠብ ቀበሩት አካል ሰውነቱ፣
የጀነት ሰው ሆኗል በአኼራ ህይወቱ፣
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


ሱመያ:
የጁምዓ ቀን ትሩፋቶች
فضلُ يوم الجمعةِ
""""""""""""""""""""""
1⃣ قال رسول الله ﷺ :
(أفضلُ الأَيَّامِ عندَ اللهِ يومُ الجمعةِ)
አቡ ሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አላህ ዘንድ በላጩ ቀን የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع - رقم: (1098)

2⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( أفضلُ الصلواتِ عند اللهِ صلاةُ الصبحِ يومَ الجمعةِ في جماعةٍ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አላህ ዘንድ ከሰላቶች መካከል በላጭ የሆነው ሰላት የጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብሂ ሰላት ነው።» ብለዋል።
📚السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566

3⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ ، فمَن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى اللهُ عليهِ عَشرًا ))
አነስ ኢብኑ ማሊክ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ምሽት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ያወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።» ብለዋል።
📚صحيح الجامع
الألباني حسن - رقم: 1209

4⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( ما مِن مسلمٍ يموتُ يومَ الجمعةِ أو ليلةَ الجمعةِ إلَّا وقاهُ اللَّهُ فِتنةَ القبرِ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ከሙስሊሞች መካከል ማንኛውም ሰው በጁምዓ ቀን ወይም በጁምዓ ምሽት ከሞተ … አላህ ከቀብር ፊትና ሳይጠብቀው አይቀርም።» ብለዋል።
📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره

5⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( الصَّلاةُ الخمسُ والجمعةُ إلى الجمعةِ كفَّارةٌ لما بينَهنَّ ما لم تُغشَ الْكبائرُ ))
አቡ ሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አምስቱ የግዴታ ሰላቶችና ከጁምዓ እስከ ጁምዓ … ከባባድ ወንጀሎች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር በመካከላቸው የተፈፀሙትን ሌሎች ኃጢኣቶች ያብሳሉ።» ብለዋል።
📚صحيح مسلم - رقم: (233)

6⃣ وفي رواية اخرى :
(( الجمُعةُ إلى الجمُعةِ كفَّارةُ ما بينهما ما لم تُغْشَ الكبائرُ ))
አባሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ከጁምዓ እስከ ጁምዓ … ከባባድ ወንጀሎች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር በመካከላቸው ያሉትን ሌሎች ኃጢኣቶች ያብሳሉ።» ብለዋል።
📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)

7⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( لا يُقيمَنَّ أحدُكم أخاه يومَ الجُمُعةِ . ثم لِيخالفَ إلى مقعدِه فيقعدُ فيه . ولكن يقولُ : أَفسِحُوا ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] ባስተላለፉልን መሰረትም
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አንዳችሁም የጁምዓ እለት (መስጂድ ውስጥ) ወንድሙን ከተቀመጠበት አያስነሳው፤ ከዚያም ወንድሙ ከተነሳበት ቦታ እሱ ሊቀመጥ አይገባውምነ። ነገር ግን (ክፍተት ካለ) ሰፋሰፋ አድርጉ (ተጠጋግታችሁ ክፍት መቀመጫ ስጡን) ይበል።» ብለዋል።
📚صحيح مسلم - رقم: (2178)

8⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( إذا راح أحدُكم إلى الجمعةِ فليغتسلْ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ብለዋል።
📚صحيح البخاري - رقم: (882)

9⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( مَن قرأَ سورةَ الكَهفِ في يومِ الجمعةِ ؛ أضاءَ لهُ منَ النُّورِ ما بينَ الجُمعتَينِ ))
አቢ ሠዒድ አልኹድሪይ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «የጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል (ያለውን ርቀት ያህል) ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)

🔟 وفي رواية اخرى :
(( من قرأ سورةَ الكهفِ ليلةَ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بينه وبين البيتِ العتيقِ ))
አቢ ሠዒድ አልኹድሪይ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «የጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ መካከል ያለውን ርቀት ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)

የኢስላም ምሁራን እንዳሉት… ብርሃን ማለት በዱንያ ላይ ሳለ ከወንጀሎች የሚጠበቅበት፣ መልካም ስራዎች ላይ የሚተጋበት እውቀት፣ ኢማን ይጨምርለታል። ወይም ነገ የቂያም ቀን ከእግሩ ስር ብርሃን ይሆንለታል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0
•════•••🌺🍃•••════•


🌹"በጁመኣ ቀን አንድ ሰአት አለች አንድ ሙስሊም አላህን ኸይር እየጠየቀ አይገጥማትም አላህ የጠየቀውን የሰጠው ቢሆን እንጂ።" ረሱል (ሰአወ)

☞ይቺን ሰአት አስመልክቶ አቡ ሁረይራ ፣ ጠውስ ፣ ኢብን አባስ ፣ አጣህ ኢብኑ ረባህ ረዲየላሁ አንሁ ወአርዷ ጁመኣ ከአስር ቡሀላ ፀሀይ ከመጥለቋ ከሰአታት በፊት መሆኑን ተስማምተዋል።

አላህ ይወፍቀን!

https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


አቡዱል ሐሊም:
🖊የሐራም እይታ

እይታ ሆነና የነገር ጅማሬ
ቃጠሎ መነሻው የሳት ፍንጣሬ
እንደተወጋ አካል በተመረዘ ቀስት
ልብም ተበላሽ በእይታ ልቀት

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ
ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ( አል ኑር :30)
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0






አቡዱል ሐሊም:
🥀✦የዘመኑ አራዳ✦🥀

➛አማርኛ አይሉት አነጋገራቸው
የዘመኑ አራዶች ምንድነው ጉዳቸው
ከእውቀት የጠሩ የተጥራሩ ናቸው
ለዲኑም ትምህርት ቦታ የሌላቸው
ነጠር ነጠር ነው አረማመዳቸው
የስታይሉ ብዛት የፀጉር ቁርጣቸው
መንገድን ያፀዳል ሲጎተት ሱሪያቸው
ሲወጡ ሲገቡ ሴት መልከፍ ስራቸው
ገርመው ይገርማሉ ሲመለከቷቸው
አላህ ዐዘወጀል ሂዳያ ይስጣቸው
እኔን የገረመኝ የሚያደንቃቸው ሰው
ምርጥ የአራዳ ልጅ ብለው ሲጠሯቸው
ዋው ዋው አሉ ይመቻል ሙዳቸው
አይ ሞኝነታቸው❗️
አሏህን አምፆ የት አለ እርድና
ይልቅ ኑ ተጓዙ በኢስላም ጎዳና
ምርጡ ነብያችን ባስተማሩት ሱና
በተውሂድ መታነፅ ይሄ ነው እርድና።‼️


https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


ሂጃብ ላለመልበስ የተለያዩ ምክንያቶች ከሚያቀርቡ ሴቶች ጋር የተደረገ ውይይት

እርሷ:- እኔ ሂጃብ ባለብስም አሏህን እወዳለሁ ስለዚህ አላህን መውደዴ በቂየ ነው።

መልስ:-
" ﻗُﻞْ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﺤِﺒُّﻮﻥَ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻓَﭑﺗَّﺒِﻌُﻮﻧِﻰ ﻳُﺤْﺒِﺒْﻜُﻢُ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ ﺫُﻧُﻮﺑَﻜُﻢْۗ ﻭَﭐﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ "
"በላቸው አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ኀጢኣቶቻችሁን ይምርላችኋልና።
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" 【ዒምራን 31】
አላህንማ ብትክክል የምትዎጅ ከሆነ መልእክተኛውን ባግባቡ ትከተይ ነበር

እርሷ:- በሙቀትና በፀሃይ ሰአት ሂጃብ ስለሚያስቸግረኝ መልበስ አልፈልግም

መልስ:-
"ِّۗ ﻗُﻞْ ﻧَﺎﺭُ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﺃَﺷَﺪُّ ﺣَﺮًّﺍۚ ﻟَّﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻳَﻔْﻘَﻬُﻮﻥ "
"የጀሃነም እሳት ተኳሳነቱ የበረታ ነው በላቸው የሚያውቁ ቢኾኑ" 【አት–ተውባህ 81】
በመገላለጥሽ ምክኒያት ነገ በአኼራ በእሳት ከመቀጣት ዛሬ በአዱኒያ ያለውን ሙቀት ተቋቁመሽ ጀነት መገባት አይሻልሽምን?

አርሷ:- አሁን ገና ልጅ ነኝ ትልቅ ስሆን ሂጃብ እለብሳለሁ

መልስ:- ሞት ልጅና ትልቅን አይመርጥም ትልቅም ትንሽም ይሞታል
ትልቅ ሳትሆኒ ብትሞችስ?

እርሷ:- እባክህ የኛ ማሃበረሰብ ሴቶች ሁሉም ተገላልጠው ነው የሚሄዱት እኔ ብቻየን ሂጃብ ስለብስ ይደብረኛል

መልስ:- ወላሂ አሁን ያልሽው በጣም የከፋ የጀሃነም ሰዎች ንግግር ነው። እነርሱ በርግጥ እንዲህ ይላሉ
" ﺑَﻞْ ﻗَﺎﻟُﻮٓﺍ ﺇِﻧَّﺎ ﻭَﺟَﺪْﻧَﺎٓ ﺀَﺍﺑَﺎٓﺀَﻧَﺎ ﻋَﻠَﻰٰٓ ﺃُﻣَّﺔٍ ﻭَﺇِﻧَّﺎ ﻋَﻠَﻰٰٓ ﺀَﺍﺛَٰﺮِﻫِﻢ ﻣُّﻬْﺘَﺪُﻭﻥَ "
"ከቶውንም እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘናቸው እኛም በፈለጎቻቸው ተመሪዎች ነን አሉ።" 【አዝ–ዙኽሩፍ 22】
አርአያሽን የሰፈርሽን ሴቶች ሳይሆን እነዚያን ብርቄየ ሱሃቦች አድርጌ!

እርሷ:- በቃ ካገባሁ በሗላ እሸፈናለሁ

መልስ:- ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ "አንድ ባሪያ በሚሰራት ወንጀል ሪዝቅን ይከለከላል" 【አህመድ ዘግበውታል】 ጥሩ ባል ከአላህ የሆነ ሪዝቅ ነው በወንጀልሽ ምክኒያት እንዳይከለክልሽ ተጠንቀቂ
ግን እመትሸፈኒው ለአላህ ነው ወይንስ ለባል? በዚህ አባባልሽ መሰረት ካገባሽ በሗላ ባልሽ መሸፈንሽን ባይፈልግ እርሱን ላለማጣት ስትይ አትሸፈኒም ማለት ነው?
ስለዚህ አንች ጌታሽን አምላኪ ሳትሆኒ ባል አምላኪ ነሽ ማለት ነው!

እርሷ:- እባክህ ዋናው የልብ ንፅህናነው ልቤ ንፁህ ከሆነ ከመሸፈኑ ምን አለኝ

መልስ:- ወስጥሽማ በተስተካከለ አካልሽም ይስተካከል ነበር ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:- "ንቁ በሰውነት ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች እርሷ ከተስተካከለች አካል ሁሉ ይስተካከላል እርሷ ከተበላሸች አካል ሁሉ ይበላሻል ንቁ እርሷ ቀልብ ነች"
በነቢዩ ምስክርነት የውጫውይ ገፅታሽ እንዲህ መበላሽቱ የውስጥሽን መበላሸት ይጠቁማል!
ደግሞም ውስጥሽ ቢስተካከል ኑሮ እንዲህ ባልተገላለጥሽ ነበር እንዲህ የተገላለጥሽው ውስጥሽ ስለተበላሸ ነው።


አለህ ሁላችንንም ያስተካክለን !


ከአረቢኛ የተተሮገመ


||••••••••||••••••||••••••||•••••||

ሼር 〰〰〰 ይደረግ



https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


Join!!👆👆👆👆👆


ሸይኸ ዐብዱልሃሚድን
የሚጠሉ አካሎች አንድም የእዉቀት ጥልቀታቸዉን
የሚያዉቁ ከዚያም እንደኛ ተልቢሰ ካለደረጉ ተብሎ ወይም

እሳቸዉን የማያቃቸዉ ጃሂል እንጅ ሰለሳቸዉ መጠየቅም አያሰፈልግህም ያፈሩትን ፍሬ ተመልከት ከመፃፍ ሳትወጣ
በብዕርህ አትዉጋቸዉ።

አላህ እረዘም ያለ ዕድሜ
ይሰጣቸዉ።

እሳቸዉን ለመግዛት፣ከሰር ለማድረግ ያልተሞከረ የለም
እናዉቃለን እዚያ ሰፈር አብሺር
ለአላህ ሰንል የምወዳቸዉ ሸይኸ ናቸዉ።ለምን ብላችሁ የምትጠይቁ
ጥሬዎች በኢልም ጥልቀት ሰላላቸዉ ነዉ።

✍አቡ አዩብ
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


አቡዱል ሐሊም:
⭐️🌸⭐️ የዛሬ ሐዲስ⭐️🌸🔴

"“ሰባት (ፈታኝ ሁኔታዎች ሳይገጥማችሁ በፊት) ለመልካም ተግባራት ተሽቀዳደሙ። ወደፊት የሚመጠብቃችሁ አዘናጊ የሆነ ድህነት፣
ወይ ለአመጽና ወንጀለኝነት የሚዳርግ ሀብት፣ በካይ የሆነ በሽታ ወይም የሚያጃጃ እርጅና፣ አጣዳፊ ሞት፣ ክፉው ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ደጃል ወይም ወሰን የለሽ መከራና አስከፊ ቅጣት የሚከሠትበት ዕለተምፅዓት (ቂያማ) ነው።
” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቲርሙዚይ/📚
አቡዱል ሐሊም:
⭐️🌸⭐️ የዛሬ ሐዲስ⭐️🌸🔴

"“ሰባት (ፈታኝ ሁኔታዎች ሳይገጥማችሁ በፊት) ለመልካም ተግባራት ተሽቀዳደሙ። ወደፊት የሚመጠብቃችሁ አዘናጊ የሆነ ድህነት፣
ወይ ለአመጽና ወንጀለኝነት የሚዳርግ ሀብት፣ በካይ የሆነ በሽታ ወይም የሚያጃጃ እርጅና፣ አጣዳፊ ሞት፣ ክፉው ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ደጃል ወይም ወሰን የለሽ መከራና አስከፊ ቅጣት የሚከሠትበት ዕለተምፅዓት (ቂያማ) ነው።
” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቲርሙዚይ/📚https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0


🦋💌 ግጥሜን ተጋበዙልኝ 🦋💌

♨️📿 የእሳቶች አለቃ (ጀሃነም) ♨️📿

አላህ የፈጠራት ለካፊሮች መቅጫ
አንዴ ከገቡባት የሌላት ማምለጫ
የተቀጣጠለች ለ3ሺ አመታት
የተጎራበተች ከታላቋ ጀነት
ዲኑን ያጎደለ ፍሟን ይቀምሳታል
አቃጣይነቷ ልብን ይሠማታል
የጀሃነም ጓዶች ዋይታቸው ይሰማል
ማን ነው የሚያድነን ያኔ ሁሉም ይላል
ማንም አዳኝ የለም ከጀሊሉ በቀር
ተመላኪው ሁሉ ነበረ እኮ ፍጡር
ከግብፁ ከፊርአውን ከኢሳ እስከ ጣኦት
ተይዘው ነበረ ልክ እንደ አማልክት
ፍጡራን ተመልከዋል አላህ ተዘንግቶ
ጣኦት አምላክ ሆኗል በእጃቸው ተሰርቶ
ጣኦትን አምላኪ ብዙ ቻይናውያን
ለወንዝ ሰጋጆች እልፍ ህንዳውያን
ወደአላህ መመለስ መቶበት ካልቻሉ
ጀሀነምን ቀማሽ ባሮች ይሆናሉ
ከኛም ከሙስሊሞች ካልተጠነቀቅን
የተውሂድን ችቦ አጥብቀን ካልያዝን
ኺታማ ደፍርሶ ከሳሪ እንሆናለን
ጀሃነምን ቀማሽ ልንሆን እንችላለን!!
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0
Join በማለት ይቀላቀሉ


✨ጠቃሚ ምክሮች✨

❄️ ያላችሁ ሃብት ህይወታችሁ ነውና በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ አታባክኑት።

❄️ ጓደኛ የምታደርጉትን ሰው ማንነት እወቁ። ከመጥፎ ሰው ጋር አትጎዳኙ።

❄️ ሶላቶቻችሁን ተጠባበቁ ውዱ ማድረግ የሚከብዳችሁ ጊዜ እንኳ ቢሆን ቀድማችሁ ውዱ ከማድረግ አታመንቱ፤ የጀመአ ሶላት ላይ ተበራቱ።

❄️ የሱና ፆሞችን ፁሙ! በወጣትነት ጊዜያችሁ ከመጥፎ ነገሮች መጠበቂያችሁ ናቸውና።

❄️ ቀን በቀን ከቁርአን የተወሰነ ምዕራፍ እንብቡ አሏህን አብዝታችሁ ለምኑት አውሱትም ምክኒያቱም አሏህ የሚያወሳውንና የሚለምነውን ይወዳልና።

❄️ የነብያቶችንና የሰሃቦችን ታሪክ አጥኑ
እወቀትን መሻት በኢስላም ግዴታ ነውና ለእውቀት ልዩ ትኩረት ይኑራችሁ።

❄️ ለሰዎች ትሁት ሁኑ ወላጆቻችሁን በቅንነት አገልግሉ።
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0

19 last posts shown.

95

subscribers
Channel statistics