የአዲሱ የትምህርት መዋቅር (6-2-4) በሚል ማሻሻያ ተደረገ
አዲሱ የትምህርት መዋቅር 6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ፣ 2 ዓመት
የመለስተኛ ትምህርት እንዲሁም 4 ዓመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት
እንዲሆን መወሰኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ18
ዓመት የሚያጠናቅቁ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/
ር ጥላዬ ጌጤ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት በግል ዘርፍ ተይዞ የቆየው የቅድመ
መደበኛ ትምህርት በግልና በመንግስት እንዲያዝ መደረጉም
ተጠቅሷል፡፡
ተማሪዎች 6ኛ ክፍል ሲያጠናቅቁ ክልላዊ ፈተናን እነደሚፈተኑና
ከዚህ በፊት ክልላዊ ፈተና የነበረው 8ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና
እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም የ10ኛ ክፍል ፈተኛ እንደማይኖርና የ12ኛ ክፍል ፈተናው
ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
#share
@ethiobravez ✍contact us
@entsuggestionbot