Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
ጊዜያችን በአጋጉል ነገር አናቃጥል።
በጊዜ መጠየቅ አለና በአግባቡ እንጠቀምበት፣ እናብብ፣ ራሳችንን በእውቀት እንገንባ፣ በዒልም እንታጠቅ፣ ይህቺን የሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ምክር አጥብቀን እንያዛት በጣም ጠቃሚ ስለሆነች በአግባቡ እንጠቀምባት፣ እንዲህ ይላሉ:–
«ጊዜህ በማይረባ ነገር እየባከነብህ/እየጠፋብህ መሆኑን ካገኘሀው፣ ልብህን መቆጣጠር ግድ ይልሃል፣ ምክንያቱም ይህ አላህን ከማውሳት በመዘንጋት የሚከሰት ነው።
ያለፉ ታሪኮችን ብትመለከት፣ የኢስላም ሊቃውንቶች እንዴት ውጤታማ ሆነው መፅሃፎችን እንዳዘጋጁ፣ በነርሱ ምክንያት ለውጤት የበቁ ዓሊሞችን ብትመለከት በእርግጥም አንት ከኖርካት እድሜ በታች ሆነ (ትገኛለች)።
ይህ የሆነውም አላህ ልባቸውን በሞላው ዚክር (አላህን ማስታወስ) ሰበብ ነው፣ በእድሜያቸው አንድ አፍታ እንኳን ያለ አግባብ የምትጠፋ ወቅት እስከማትኖር ደርሰዋል።
አደራህን!! ለዚህ የልብ በሽታ ትኩተረት ስጥ፣ መድኃኒቱን በመፈለግ ላይ በርታ። ምክንያቱም በሽታው በልብህ ከተሰራጨ (አላህን ጤናማነትን እንጠይቀዋልን) ይሞታል፣ በሱ ላይም የታተመ/የታሸገ ይሆናል፣ ሀቅን ሀቅነቱን አይገነዘብም ባጢልንም ባጢልነቱን አይገነዘብም።» [ተፍሲሩ ሱረት አል_አህዛብ]
✍🏻ኢብን ሽፋ: ሸዋል 8/1440 ዓ.ሂ
https://telegram.me/IbnShifa