Forward from: Home of love
😍 እወድህ ነበረ 😍
ከዋክብት በፍቅር ~ እንደሰገዱላት
እንደ ውብ ጨረቃ፣
ሰማይ ዙፋን ሆኗት ~ እንዳሸበረቀች
እንደ ድንቡል ዶቃ፣
ምግብ የራባት ነፍስ ~ ማቆያ እንደሚያሻት
እንደመጥገቢያዋ፣
እንደጉብል ወጣት ~ እንደመሽቀርቀሪያ
እንደመዋቢያዋ፣
እንደ እናት ጡት ወተት~ ለልጅ እንደሚያሻው፣
እወድህ ነበረ ~ አንተን የልቤን ሠው።
አብዝቼ እልፍ ጊዜ ~ እወድህ ነበረ፣
ከዐይኔ ስትሰወር ~ ፍለጋ እየዞረ፣
አካላቴ ሁሉ ~ ዝሎ እየሰከረ፣
አማትራለሁኝ ~ አንተኑ ጥበቃ፣
ገዝፎ ይጮህ ነበር ~ የፍቅሬ እውነት ሲቃ።
ነበር እኮ ድሮ ~ አሁን ጠፍቶብኛል፣
ወድጄህ ስትርበኝ ~ ፍቅር አስጨንቆኛል፣
ህመሜን ላታክም ~ ቆስዬ ስትሸሸኝ፣
አመርቅዞ ደምቶ ~ ስቀር ለብቻዬን፣
ሆነብኝ ጠባሳ ~ እዡ ፈሰሰልኝ፣
ደርሶ ባይድን እንኳ ~ አገግሜያለሁኝ፣
እናልህ ዓለሜ ~ እወድህ የነበረው
ላንተ የሆነው አልቆ፣
ቃልኪዳኔን ሽሬ ~ ፍቅሬን ቀብሬያለሁ
ከጥልቁ ሸለቆ፣
የእናቴን ከራማ ~ የአባቴን አውሊያ
አጫጭሼ ካደምኩ፣
መስጂድ ቤተስኪያንም እንባዬን አፈሰስኩ፣
በወደድኩህ ልኬት ~ አንቅሬ ልተፋህ
የጠየኩት ፀሎት፣
ሰምሮልኝ ምኞቴ ~ አከፋፍያለሁ
የደረሰ ስለት፣
ስነግርህ እወቀው ~ የእኔም አፍ በተራው
ብሶት ተናገረ፣
ዛሬ እንዲህ ልጠላህ ~ እወድህ የነበረው
አምና ድሮ ቀረ።
(ወጣህልኛ )
✍ኤዲ ያና
@loveurhome
🌹❣🌹❣🌹❣🌹
❥❥________⚘_______❥❥
ከዋክብት በፍቅር ~ እንደሰገዱላት
እንደ ውብ ጨረቃ፣
ሰማይ ዙፋን ሆኗት ~ እንዳሸበረቀች
እንደ ድንቡል ዶቃ፣
ምግብ የራባት ነፍስ ~ ማቆያ እንደሚያሻት
እንደመጥገቢያዋ፣
እንደጉብል ወጣት ~ እንደመሽቀርቀሪያ
እንደመዋቢያዋ፣
እንደ እናት ጡት ወተት~ ለልጅ እንደሚያሻው፣
እወድህ ነበረ ~ አንተን የልቤን ሠው።
አብዝቼ እልፍ ጊዜ ~ እወድህ ነበረ፣
ከዐይኔ ስትሰወር ~ ፍለጋ እየዞረ፣
አካላቴ ሁሉ ~ ዝሎ እየሰከረ፣
አማትራለሁኝ ~ አንተኑ ጥበቃ፣
ገዝፎ ይጮህ ነበር ~ የፍቅሬ እውነት ሲቃ።
ነበር እኮ ድሮ ~ አሁን ጠፍቶብኛል፣
ወድጄህ ስትርበኝ ~ ፍቅር አስጨንቆኛል፣
ህመሜን ላታክም ~ ቆስዬ ስትሸሸኝ፣
አመርቅዞ ደምቶ ~ ስቀር ለብቻዬን፣
ሆነብኝ ጠባሳ ~ እዡ ፈሰሰልኝ፣
ደርሶ ባይድን እንኳ ~ አገግሜያለሁኝ፣
እናልህ ዓለሜ ~ እወድህ የነበረው
ላንተ የሆነው አልቆ፣
ቃልኪዳኔን ሽሬ ~ ፍቅሬን ቀብሬያለሁ
ከጥልቁ ሸለቆ፣
የእናቴን ከራማ ~ የአባቴን አውሊያ
አጫጭሼ ካደምኩ፣
መስጂድ ቤተስኪያንም እንባዬን አፈሰስኩ፣
በወደድኩህ ልኬት ~ አንቅሬ ልተፋህ
የጠየኩት ፀሎት፣
ሰምሮልኝ ምኞቴ ~ አከፋፍያለሁ
የደረሰ ስለት፣
ስነግርህ እወቀው ~ የእኔም አፍ በተራው
ብሶት ተናገረ፣
ዛሬ እንዲህ ልጠላህ ~ እወድህ የነበረው
አምና ድሮ ቀረ።
(ወጣህልኛ )
✍ኤዲ ያና
@loveurhome
🌹❣🌹❣🌹❣🌹
❥❥________⚘_______❥❥