ይነበብ ቁ2
ለጮሆ ሁሉ ጆሮ አልሰጥም ብለህ በሱና ላይ የፀናሃው ወንድሜ ናማ?! ከኔጋር ፈገግ በል!!
አዎ እማናግረው በአቋምህ የፀናሃውን የጫሂ ጩሆት ከያዝከው የሰለፊያ አቋም የማያነቃንቅህን ነው እንጅ
ከፍ ባለ ድምፅ የጮሆ ሁሉ ሃቅ የያዘ እየመሰለው ንፋስ እንደሚያራግበው ባንዲራ የሚርገበገውን አቋም የለሽ ወላዋይ አይደለም! ምክኒያቱም እንዲህ ያለው ዛሬ ቢሄድም ነገ ደግሞ ከፍ ያለ ድምፅ በሰማ ሰአት አድሱን አቋሙን መቀየሩ አይቀርም!!
•
ከሶስት ወር በፊት የመን በተደረገ አንድ ደውራ ላይ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ በስልክ ተጋርተዋል።
የደውራው ሐላፊዎች(ቋሚዎች)የመዕበርና የፊዊሽ መርከዝ መሻይኾች ነበሩ።
መዕበር ማለት የሸይኽ ሙሐመድ አል–ኢማም መርከዝ ነው።
•
በዚህ ደውራ በአካል ከተሳተፉት መሻይኾች ባሻገር በስልክ
1, አል ዐላመቱ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ
2, አል ዐላመቱ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላህ አል ኢማም
3, ሙሐዲሥ ሸይኽ ዐሊይ አር–ራዚሂይ
4, ዳዒ ሸይኽ ወህባን ኢብኑ ሙርሺድ አል መውደዒይ
ተጋርተዋል
•
👉 ሸይኽ ዐሊይ አር–ራዚሒይ እና ሸይኽ ወህባን ኢብኑ ሙርሽድ ማን ናቸው?!
1, ሸይኽ ዐልይ አር–ራዚሂይ (ሐፊዞሁሏህ) የሸይኽ ሙሐመድ አል ኢማም ተማሪ በመዕበር መርከዝ ግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት አስተማሪዎች መካከል ሲሆኑ ሸይኽ ሙሐመድ አል–ኢማምን በደርስ ጊዜ በማስተማርና በፈታዋ በመስጠት የሚያግዟቸው ዐሊም ናቸው።
((በነገራችን ላይ ኹጥባቸውን እና ደርሶቻቸውን በተለይ ሙጠወል የሙስጦለህ ደርስ የምትፈልጉ ቻናላቸውን በዚህ መቀላቀል ትችላላችሁ {
https://t.me/AliAlrazihi } ))
2, ዳዒ ሸይኽ ወህባን ኢብኑ ሙርሺድ አል መውደዒይ የሸይኽ ሙሐመድ አልኢማም ተማሪ እና አማች(የልጃቸው ባል) ሲሆነ ዘማር የሚባለው ሀገር ውስጥ የራሳቸው መርከዝ አላቸው። ከሸይኽ መሐመድ አል ኢማም ላይ በመከላከልም በቅርቡ አንድት ሪሳላ አዘጋጅተዋል። ያዘጋጇትን ሪሳላ በዚህ ሊንክ ያገኟታል።
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/711_
👉 ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ ደግሞ በዚህ ደውራ ላይ አብረዋቸው የተጋሯቸውን መሻይኾች ከንግግሮዎ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ በደንብ ያደንቃሉ
👉 በደውራው ላይ የሚሰጡትን ኩቱቦችና ት/ቶች ካደነቁ በሗላ በደውራው ላይ እንደርሰዎ በርቀርት በስልክ
የተጋሩትን መሻይኾች እንዲህ በማለት አድንቀዋል።
👌 «በየመን ያሉ የሰለፊይ ወንድሞቻችን ሱንይ መሻይኾች ከርቀት ተውጅሀት በመስጠት ይጋራሉ በማለት የሰማነውም ወደዚህ ይጠጋል በዚች ደውራ በርቀት ይጋራሉ ። ከ01:37–01:54 ባለው ደቂቃ ከሸይኽ ሙ/ድ ኢብኑ ሃዲ ንግግር ያዳምጡት
ከተወሰነ ደቂቃ በሗላ ደግሞ
«እንደዚሁም የክብር ባልተቤት የሆኑ መሻይኾችንም አላህ እንዲመነዳቸው እለምናለሁ ወንድሞቻችን አህሉሱና የሱና መሻይኾች በየመን ሀገር አህሉል ሐዲይሥ ወልአሠር የሆኑ … » ከ8ኛው ደቂቃ በሗላ
ያዳምጡት
በመቀጠልም ለኡማው የሚያስተምሩትን ት/ት
ሐቅን ሳይደበቁ ግልፅ የሚያደርጉትን አሏህ እንዲባርክላቸው ዱዓ አደረጉላቸው።
👂ከዚያም በሪፍቅ አደራ በማለት መክረዋቸዋል!!
_
ልብ በል ወንድም ዐሊ በቻናሉ ላይ በቅርቡ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲን ስለ ተመዩዕ የተናገሩበትን እንዲህ በማለት ልኮ ነበር!!👇
«ما معنى المميع؟
✅من هم المميعون؟
አደራ በጢሞና አዳምጡት ሙመይዓ ማለት ምን ማለት ?ነው ኢና ማን ናቸው?👆»
ከዚያም ቀጠለና ሸይኹን እንዲህ በማለት ገለፃቸው።
👇
«أسد السنة شيخ الوالد العالم العلامة وفقيه الزمان أبو أنس محمد بن هادي المدخلي السلفي حفظه الله تعالى»
ጥያቄ ለወንድም ዐሊ:-
ስለ ሙመየዐና ስለሙመይዖች ያስተምራሉ ብለህ የላካቸው ሸይኽ ሙ/ድ ኢብኑ ሃዲ የሸይኽ ሙ/ድ አል ኢማም ተመዩዕነት ተሰውሩባቸው ነው አብረዋቸው በተማሪዎቻቸው የተዘጋጀ ደውራ ላይ የተጋሩትን?? ከዚያም አልፈው እንደዚያ ያደነቋቸው??
ወይንስ እርሰዎም የአቋም መነሸራተት የምትሏት ዜማ ተጋብታበዎት ይሆን??
👂 ከዚህም አልፎ ሲመክሯቸው ሙተሳሂል አትሁኑ ሽዳ ይኖራችሁ እያሉ አይደለም የመከሯቸው አንተ ካሰብከው በተቃራኒ ነው በሪፍቅ እና ጉንን በማለስለስ አደራ እላችሗለሁ እያሉ ነው የመከሯቸው።
👉 ምክኒያቱም የየመን ሰለፊያ ዑለሞች በሽዳ እንጅ በተሳሁል አይታወቁም።
👉 በአህለል ቢደዕ ላይ ያላቸው ሽዳ እና በራእ ግልፅ ነው።
👂 ዱዐም ሲያደርጉላቸው ለህዝብ ሳይደብቁ ግልፅ የሚያደርጉትን ሐቅ አሏህ እንዲባርክላቸው ነው። እንጅ ተምዩዕነታቸውን አላህ እንዲያላቃቸው አይደለም ዱዐ ያደረጉላቸው??
👉 ለማንኛውም በአንድ ራስ ሁለት ምላስ አትሁን ወይ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ "ሙመይዕ ብለህ" የወነጀልካቸው ዓሊም ጋር ደውራ በመጋራታቸው እራሳቸውንም "ሙመይዕ" "ከአቋማቸው የተንሸራተቱ" "የመንሀጅ ክፍተት ያለባቸው" ብለህ ፍረድ እና የጀርህ ወተዕዲል ደረጃህን ከፍ አድርገህ አሳየን
👉 ወይንም ሸይኽ ሙሐመድ አል ኢማምን እንዲህ ታላቅ ዓሊም እና ታላላቆች ዘንዳ አንቱታን የተረፉ እንቁ የሰለፊይ ዓሊም መሆናቸውን አላውቃቸውም ነበር እና ነው ስለዚህ ካለኝ አቋም ተመልሻለሁ ብለህ በግልፅ እንደቀጠፍክባቸው በግልፅ ተመለስ
👍 ለማንኛውም ወንድም ሙእሚን ከአንድ ጉድጓድ ሁለት ጊዜ አይነደፍም እና ንቃ እንዳትሸወድ ሁለተኛውን ምረጥ
በሀሰት ላይ ከምዘወተር ወደእውነት ብትመለስ ይሻላሀል
•
በርግጥ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲን ሌሎች ሰለፊያ ዑለሞችን እንደምንወድ እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን እንጅ እርሱዎ ፍፁም ናቸው ብለን አናምንም እንዲሁም የሚጀርሁትንም ሆነ የሚያደንቁትን ከመረጃ ጋር እንጅ በጭፍን እንከተላለንም ለማለት አይደለም
•
ግን በሰሞኑ ጉዳይ ብዙ ጊዜ የማጣቅሳቸው እነ ወንድም ዐሊ ጀርህ ወተዕዲል የጂቲሃድ መስኣላ አይደለም ብለው ስለሚያምኑ እንደዚያ ከሆነ እርሰዎንስ ምን ትላላችሁ? እሄው በናንተ ቤት ተጀርኸዋል ያላቸሗቸውን ዓሊም ሰለፊይ ናቸው እያሉ በአደባባይ እያደነቁ ነው። መርሃችሁ የሚሰራው እየመረጣችሁ ጭሆት አይነሳብንም ብላችሁ የምታስቡበት ላይ ነው ወይንስ ወጥ ሙስና የሌለበት መርህ ነው ለማለት ነው።
__
በደውራው ላይ በስልክ ያደረጉትን የዑለሞችና መሻይኾች ግግር ከዚህ በታች ባሉት ሊንኩች ታገኟቸዋላችሁ
① የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ አል መድኸሊይን ንግግር
በዚህ {
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/732 }
② የሸይኽ ሙሐመድ አል ኢማምን ንግግር
በዚህ {
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/727 }
③ የሸይኽ ዐሊይ አር–ራዚሂይ ንግግርን
በዚህ {
https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/728 }