Forward from: Dhiiroo Garbii
ከትግራይ መንግስት ማእከላይ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ
ከነሓሴ 18/2014 ዓ/ም በፋሽሽት አብይ አህመድ ቡድን ሰራዊት እና ሸሪኮቹ እንዲሁም የአምባገነን ኢሳያስ አፈወርቂ ትግራይ ሙሉ በሙሉ በእጁ ለማስገባት ያልተጠናቀቀው ህዝብ ለማጥፋት ፕሮጀክታቸው በሁለት ሳምንት ውስጥ ውስጥ ለማጠናቀቅ ያለመ ጥቃት በበርካታ ግንባሮች ጀግናው ሰራዊታችን ባካሄደው ውጤታማ የመከላከል እና የፀረ ማጥቃት እርምጃዎች አንደኛው የህዝብ የማጥፋት ምዕራፍ እንደተቀለበሰ ይታወቃል።
ከነሓሴ 24/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢሳያስ አፈወርቅ መንግስት ያለ የሌለ ሓይሉ በማዝመት የተሳተፈባቸው ወረራዎች በሚፈለገው መንገድ እናዳልሄደለት እና በአስር ሺዎች የሚቆተሩ የጠላት ሃይል ከጥቅም ውጭ ሆኖ ሰራዊታችን የአብይ አህመድ እና የአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ የጋራ የጥፋት ፕሮጀክት በሚፈልጉት መንገድ ሊሳካ እንደማይሳካ በግልፅ ታይቷል።
ሰራዊታችን ከተደቀነበት የጥፋት አደጋ ለማዳን ያደረገውን አስገራሚ ጀግንነት እና ፅናት የተሞላበት ተአምራዊ ስራ በጠላቶች ካምፕ ሽብር እና መደናገጥ ፈጥሯል።
ለዚህም ነው ጠላቶች የተረፈውን ሃይላቸው አቀናጅተው የትግራይ ሰራዊት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለማንበርከክ የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ያስችለናል ያሉትን መጠነ ሰፊ የጥቃት እና ወረራ ለማካሄድ ከሁሉም የኢ/ያ አከባቢዎች ያሰባሳቧቸውን ሁሉም መደበኛ አሃደች ፣የአማራ ል ሃይል እና ፋኖ ሙሉ የኤርትራ ሰራዊት እንዲሁም ተጠባባቂ የአማራ ሃይል እና ሚሊሻ በማዝመት ዛሬ ጥዋት ከተከዘ እስከ ዓዲ ኢሮብ በሚገኝ ምሽጎችን ሰፊ ጥቃት ጀምሯል።
በተለይም ባለፉት ጥቂት ቀናት በፀለምቲ እና ኩሕሊ ግንባሮች የገጠመውን ከባድ ኪሳራ ደነገጠው ጠላት ዛሬ ንጋት ላይ የፋሽስቱ ቡድን ምስራቅ እዝ ስሜናዊ እዝ አብዛኛው ከፍሉ፣ሶስት ኮማንዶ ክፍለጦሮች በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ልየ ሃይል እና ፋኖ ሲያሰማራ፣አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ሙሉ የኤርትራ ሰራዊት እና የኤርትራ ሙሉ ተጠባባቂ ሃይል እና ሚሊሻ በማሰማራት በዛላምበሳ፣ጾሮና እና ራማ በኩል፣እንዲሁም በዓዲ አውዓላ፣ሕረት፣ማይኩሕሊ፣ማይ ሑጻ እና ዝባን ገደና ሰፊ ጥቃት ጀምሯል።
የዚህ ጥቃት ዋነኛ ትኩረቴ ወደ አድያቦ ያደረገ ሲሆን በሁሉም ግንባሮች በተቀናጀ መንገድ እየተደረገ ያለ ሲሆን ጀግናው ሰራዊታችን አሁንም እንደ ከዚህ ቀደም በተለመደው ጀግንነት እና ጽናት እየመከተው ይገኛል።
የትግራይ ህዝብ እና መንግስት የትግራይ እና ኢ/ያ ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በኩል የቀረበው ጥሪ ተቀብለው ምላሽ በሚጠብቁበት ጊዜ እየተደረገ ያለው ጥቃት ጠላቶቻችን እኛን የማጥፋት ጉዳይ የሞት እና ሽረት ጉዳይ አድርገው እንደወሰዱት በማያወላዳ መንገድ ያረጋገጠ መሆኑን የትግራይ መንግስት ማእከላይ ኮማንድ ያምናል።
የተከበርከው የትግራይ ህዝብ
በላይህ ላይ የታወጀው ዘር የማጥፋት ወረራ ለመመከት ልጆችህን አሰልፈህ በፍጹም ጀግንነት እና ጽናት ትግልህን እያጠናከርክ መጥተሃል።አሁንም ቢሆን ከጸና አቋምህ ለአፍታ እንኳን ሳትዘናጋ እያደረግከው ያለሀው እጅግ የሚያኮራ ተግባር የትግራይ መንግስት ማእከላዊ ኮማንድ ያለውን አድናቆት ለመግለጽ ይወዳል።
ይሁን እንጂ አሁን ያጋጠመን ፈተና ከማነኛውም ጊዜ በላይ የእያንዳንዱ ትግራዋይ ተሳትፎ የሚጠይቅ የህለውና ጉዳይ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት እያደረግነው ባለነው ሁለንተናዊ ምከታ ሙሉ በሙሉ እንድትከት እና የጠላቶቻችን ህልም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለማምከን እያደረግነው ባለነው ርብርብ ጥረትህ እንድታጠናክርየትግራይ መንገስት ማእከላዊ ኮማንድ ጥሪውን ያቀርባል።
የኢትዮጵያ ህዝቦች
የልማትም ይሁን ሌላ መደበኛ አጀንዳ የሌለው የሌለው የጥፋት ሀይል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችህን ወደ ጦርነት በመማገድ የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት ያደረገው እና እያደረገው ያለው የጥፋት ዘመቻ ተጨማሪ መቶ ሺዎችን ሊቀቅል ላይ ታች እያለ በሚገኘው የጥፋት ሀይል ላይ ተቃውሞህን እንድታሰማ ጥሪ ያቀርባል። በተለይም የአማራ እና የአፋር ህዝብ እስከአሁን ያሳያችሁት አወንታዊ ምልክቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም በማይጠቅም አላማ ልጆቻችሁን የእሳት እራት የሚያደርጉ ሰራዎችን እየተበተበ ካለው ከፍሽስቱ ስርአት እና አምሳያዎቹ ወጥመድ ለመውጣት የጀመራችሁት ጥረት አጠናክራችሁ ቀጥሉ።
ለኤርትራ ህዝብ እና ሰራዊት
የአምባገነኑ ፍላጎት ለሟሟላት እስከአሁን ድረስ የከፈልከው ከፍተኛ ዋጋ ይበቀሃል።ልጆችህ ወንድማቸውን ለማጥፋት የሚደክሙበት የኤርትራ ህልውና ከማይቀበሉ ወገኖች ጋር ተሰልፈው የእሳት እራት የሚሆኑበትን ሂደት እየተቃወምክ መጥተሀል።አሁንም አጠናክረህ ቀጥል። የትግራይ ህዝብ የራሱን አይሰጥም የሌሎችንም አይፈልግም፤ ፍላጎታችን ምኞታችን ሰላም እና ልማት እንጂ ውደመት ሆኖ አያውቅም ፤ አይሆንንም።
ጀግናው የትግራይ ሰራዊት እስከአሁን ያሳየሀው ለመግለፅ የሚከብድ ጀግንነት እና ፅናት ከህዝብህ የወረሰከው መሆኑን እና እንደምትቀጥልበትም የትግራይ መንግስት ማእከላይ ኮማንድ በሚገባ ይገነዘባል። ለመግለፁ የሚያስቸግር ፈተናዎችን አልፈህ አንፀባራቂ ድሎችን አስመዝግበሀል፤ አሁንም ከህዝብህ ጋር ድሉ ያንተ መሆኑ አያጠራጥርም።
የትግራይ መንግስት ማእከላይ ኮማንድ
መስከረም 10/2015 ዓ.ም
ህልውናችን እና ደህንነታችን በክንዳችን!
ትግራይ ትስዕር!