በክልሉ በበጀት ዓመቱ ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ሊቆጠሩ የሚችሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የዕቅድ የትውውቅ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ በበጀት ዓመቱ ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢንተርፕራይዞች በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በክልሉ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ የሥራ እድል ፈጠራ መሆኑን ጠቅሰው ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በሚቀጥለው በጀት ዓመትም የተሳለጠና ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን የስራ አጥ ቁጥርን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ በልዩ ትኩረትና በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ መዝረዲን ሁሴን፣ የየቢሮው ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳን ጨምሮ የቢሮው፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መዋቅር የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከቢሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡