❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
ለጀማሪዎች ሰውነት ገንቢዎች የሚሆን መረጃ
❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
🚠1. ከማሽኖች ይልቅ ባር ቤል እና ዳምፔሎች በመጠቀም dual purposed (ደባል ጥቅም) ያላቸው እንቅስቃሴዎችን መስራት እነዚህም ኮምፓውንድ ኤክሰርሳይስ ይባላሉ ይህን በሌላ ፅሁፍ እናቀርባለን
🏋♀2. ግብ ማስቀመጥ እራሳችንን ፎቶ በማንሳት ሊኖረን የምንፈልገው ሰውነት ጎን አስቀምጠን ማስተያየት
🥊3.በሳምንት ከ3 - 4 ቀን መስራት
🏋♀4. የምንፈልገውን የሰውነት ክፍል (ጡንቻ) በሳምንት 2 ጊዜ መስራት ግድ ይኖርብናል....ሁሉንም የጡንቻ ክፍል እኩል በሆነ መልኩ ማሰራት አለብን
🎭🎭5. እያንዳንድን እንቅስቃሴ ከመስራታችን በፊት ከቀደሙ ሰዎች ወይም አሰሪዎች ሰለ አሰራሩ ትምህርት መቅሰም የጂም ትንሿ ስህተት መዘዟ ብዙ ስለሆነ ማለት ነው
🏋♀🏋♀6. ቀስ እያልን እንጂ ባንዴ ከበድ ያሉ ክብደቶችን አለማንሳት አንዳንዶች ከባድ ስናነሳ ጡንቻችን በፍጥነት የሚያድግልን ይመስለናል ይህ ግን ስህተት ብቻ ሳይሆን ለወገብ እና ነርቭ የመገጣጠምያ ቁስለት ለመዳርገን ይችላል ማንሳት ያለብን በ1 ዙር ከ8 -10 ግዜ ብቻ ማንሳት የምንችለውን ብቻ ነው ሰውነታችን ሲለምድ ቀስ እያልን መጨመር
🍗🥑7. በዛ ያሉ በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች መጠቀም ማለትም ለምሳሌ ቀይ ስጋ አቮካዶ እንቁላል ወተት አሳ .......ይህንን በሌላ ፅሁፍ የበለጠ እንመለስበታለን
🍯🧀8. በቀን ውስጥ ከ 6 ግዜ መመገብ አንዴ ብዙ ከመመገብ አነስ አነስ እያረጉ በይ 3 ሰአት ልዩነት መመገብ ይህም ሰውነታችን ያልተቋረጠ ሃይል እንዲያገኝ ያደርገዋል
🍑🍒9. ከማክሮ ኒውትረት (ፕሮቲን ካርቦሀይድሬት ፋት) በተጨማሪ ማይክሮ ኒውትረንት ( ቫይታሚን እና ሚኒራሎች) መጠቀም ይህንንም ከ አትክልት እና ፍራፍሬ ማግኘት ይቻላል በተጨማሪም የቪታሚን ሰፕሊመንቶችን መጠቀም ተገቢ ነው
🏊♀🏊♀10. በቀን ውስጥ ከ 8 ሰአት በላይ ማረፍ (መተኛት) ይህም የደከሙ እና የሞቱ ሴሎቻችን እንዲያገግሙ እና እራሳቸውን እንዲተኩ ግዜ ያገኛሉ ግን መረሳት የሌለበት እንቅልፍ እና እረፍት ሲበዛ ተቃራኒ ውጤት እንዳለውም መረሳት የለበትም
🤼♂🤼♂11. ስለሰውነታችን የሚሰጡ አሉታዊ አስተያየቶች እንደ ማበረታቻ መጠቀም በሱ ተከፍተን አለማቆም አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከቅናትም ይሁን ከሌላ ከማበረታታት ይልቅ ስለሰውነታችንም ሆነ ስለ ስፖርቱ ብዙ የተሳሳተ ነገር ሊናገሩን ይችላሉ ስለዚህ ይህን ችላ ብለን ስራችን እና ግባችን ላይ ማተኮር ይኖርብናል
🙏🙏ለግሩፖች እና ጓጀኞቻቹ forward በማረግ ማጋራት እንዳትረሱ እኛን የበለጠ እንድንሰራ ያበረታታናል
💜💜💜💜JOIN👇👇👇👇👇👇👇
@bodybiuld1 @bodybiuld1