Ayu ????


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


@Ayuhali
Born in ??living ?? nat ??
Music??
Video?
Pictures ?❤️
Promotion
About love?

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የድሀ ፍቅር

ክፍል 7

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,.
የማትሪክ ፈተና መጥቶ እኔና ሜላት ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተገናኝን
,የማትሪክ
ውጤት ቅድሚያ የኔ ወጣ ደስ የሚል ውጤት አምጥቼ አለፍኩ በጣም ደስ እለኝ
ሜላትም
ደስ አላት,የሜላትም ውጤት መጣ ሜላት ግን አላለፈችም ነበር በጣም ያሳዝናል
አዘንኩ
አብረን እንደምንቀጥል ነበር የማስበው በቃ ግን አልሆነም,
ሜላት በውጤቷ ብዙም አልተበሳጨችም ይልቅስ የኔ ማለፍ አስደስቷታል ,እኔ ግን
አዝኛለው .ውዴ አለችኝ እንደከፋኝ አውቃ ወዬ አልኳት,አየህ የእኔ መውደቅ አሪፍ ነው
ምንክያቱም ባልፍ እንኳን አንድ ዮኒቨርሲቲ ላይደርሰን ይችል ነበር እኔ እዚህ ከሆንኩ
ግን
ቢያንስ አንተጋ እየመጣሁ እጠይቅሀለው የፈረደበት የአባቴ ድርጅት አለ እዛ መቀጠር
እችላለው ለእናትህና ለወንድምህም እኔ ቅርብ ሆኜ እንከባከባቸዋለው አለችኝ,.
ከሜላት ያልጠበኩትን ነገር ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ይከፋታል ብዬ አስቤ ነበር
በተቃራኒው ግን አልከፋትም,.እሽ ብያት ተያይዘን እኛ ቤት ሄድን ለእናቴ የኔ ማለፍ
አስደሰታት ሜላት እንዳላለፈች ስታውቅ አዘነች ግን ሁሉም ለበጎ ነው ,እናቴ
እንደተለመደው ነጠላዋን አንጠልጥላ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደች እኔና ሜላትም ያበጠው
ይፈንዳ ብለን ተያይዘን ዘና ለማለት ሄድን ,ያን ጊዜ ግን ብር ስለነበረኝ እኔ ልክፍል
አልኩ
ሜላት አልፈቀደችልኝም,.
እኔና ሜላት ስንዝናና ውለን መሽ ልንለያይ ስንል የባንክ አካወንት መክፈት እንዳለብኝና
አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል መጀመር እንዳለብኝ ነገረችኝ ከተቻለ አዲስ አበባ
ዮኒቨርሲቲ እንዳይደርስህ ፀሎት አድርግ አለችኝ ,ለምን አልኳት ,ከጏደኞቼ ጋር ዘና ልንል
ነው ብዬ ያለህበት ድረስ መምጣት እችላለው አዲስ አበባ ከደርሰህ ግን አልችልም
አለችኝ እሽ እስኪ እናያለን ፈጣሪ ያውቃል አልኳት,
ሜላትን ወደ ቤቷ ሽኝቼ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ በቃ እናቴ ደስ ብሏታል እኔም ደስ አለኝ
የእናት ደስታ ከማየት በላይ ምን ያስደስታል ምን በቃ ደስተኛ ነኝ,ምን እንደሚፈጠር
ባይታወቅም ፈጣሪ ያለው እንደሚሆን ግን አምናለው,ሜላቴን ማጣት አልፈልግም በቃ
ከልቤ እወዳታለው የመጀመረያየም የመጨረሻዬም እሷ ብቻ ናት በችግር ጊዜ እንኳን
ፊቷን
አላዞረችብኝም አብራኝ ነበረች ,.ሁሌም ሳፈቅራት እኖራለው,.
ቀኑ ደርሶ የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰኝ አወኩኝ "ደብረማርቆስ"ዮኒቨርስቲ ነበር የደረሰኝ
ለሜላት ደውዬ ነገርኳት ልቀይር ወይስ ይሁን አልኳት አይ አትቀይር አሪፍ ነው አለችኝ
እሽ
አልኳት በቃ እንገናኛለን ተባባልን,. ማድረግ የነበሩብኝን ነገሮች ሳስተካክል ዋልኩ እናቴ
በአቅሟ የምትችለውን እያደረገች ነው.,
የምዝገባ ጊዜ ሳያልፍ መመዝገብ ስለነበረብኝ ልሄድ እንደሆነ ለሜላት ነገርኳት እሷም
አብሬህ እሄዳለው አለችኝ ,እሽ ብያት እሷም ለቤተስብ ምክንያት ፈጥራ አብራኝ ሄደች
ተመዝግቤ ዞር ዞር ብለን ከተማዋን ስናይ ዋልን ደብረማርቆስ ውብ ናት ,እኔና ሜላት
ደስ
የሚል ጊዜ አብረን አሳለፍን ለመጀመርያ ጊዜ አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ
አደርን
,በህይወቴ የማልረሳው ድንቅ ቀን .እኔና ሜላት ለ ሁለት ቀን ያክል ቆይተን ወደ አዲስ
አበባ
ተመለስን .ነገ ማታ እቤት እመጣለው ብላኝ ተለያየን,...
በማግስቱ ማታ ሜላት እቤት መጣች በእጆቿ ፊስታል አንጠልጥላለች ተቀብያት ገብታ
ተቀመጠች ገና ከመቀመጧ ምንም እንዳትለኝ አለችኝ በፍረሀት ምንድነው አልኳት
ፊስታሉን ፈትታ ለቢጃማ የሚሆን ቱታ የውጪ ቲሽርት ጅንስ ሱሪ ጫማ ቦርሳ ስልክ
ሳይቀራት
ገዝታ ነበር የመጣችው ምን ልበል ምንም እንዳትል ብላ አስጠንቅቃኛለች ዝም አልኩ
አመስግናለው ከማለት ውጪ,.
ሜላት ለኔ ከምንም በላይ ነች በርትተህ ተማር እኔም እየመጣሁ እጠይቅሀለው እነ
ማዘር
ከናፈቁህ አንተም በእረፍት ጊዜ መጥተህ ታያቸዋለህ ብቻ ትኩረትህ ትምህርትህ ላይ
ይሁን አለችኝ እሽ ማሬ አልኳት.እናቴም ተባረኪ ልጄ አለቻት በርታ እሽ ልጄ አለችኝ
በስስት
እያየች የእናት እንጀት ሆኖባታል,.ወንድሜም ስማ ለኛ እንዳታስብ እሽ እኔ እንዳንተ
ጎበዝ
እሆናለው አለኝ እሽ እልኳቸው ሁላችንም እንባ ተናንቆናል,.ትንሽ አምሽተን ሜላትን
ሸኘኃት
,.የተለመደውን ግንባሯን አንገቷን ከንፈሯን ስሜ ተለየኃት,.
ዝግጅቴን አጠናቅቄ የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ስለነበር ለመሄድ ወሰንኩ ሜላትም
እናቴና
ወንድሜ ሆነው ሸኙኝ እንደምወዳቸው ነገርኳቸው ሜላቴ አፈቅርሻለው አልኳት በቃ
ቻው
ብዬ ተለየኃቸው. የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ ጉዞ ጀመርኩ የብቸኝነት ህይወት አንድ
ተብሎ
ተጀመረ ,እኔና ሜላት እንደዋወላለን ሜላቴ እዛው አባቷ መስሪያ ቤት መስራት
ጀምራለች
እኔም ትምህርቴን የመጀመርያ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሆኜ ጀምርያለው........
ይቀጥላል ...

ቶሎ እንዲቀጥል..like 👍❤️👍❤️👍❤️❤️❤️❤️
@bosbitch


የድሀ ፍቅር

ክፍል 6

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ
እኔና ሜላት በስልክ ስናወራ ቆይተን ነገ ቤተስብን አስፈቅደሽ እናጠናለን ብያት ስልኩ
ተዘጋ,ስልኩን እንደዘጋሁት ሌላ ስልክ ተደወለልኝ የማላውቀው ስልክ ነበር ዝም አልኩት
,ደግሞ ተደወለልኝ ግራ ገባኝ ከሜላት ውጪ ይሄንን ስልክ ማንም አያውቀውም
በሦስተኛው አነሳሁት በር ላይ ነኝ ውጣ የሚል ጎርናና ድምፀ ማን ልበል ስለው ውጣ
ብሎኝ ስልኩን ዘጋው.,
ደነገጥኩኝ ለእናቴ ሳልነግር መጣሁ ብዬ ወደ ውጪ ወጣሁ አንድ ግብዳ ሰውዬ
በርላይ
ቆሞ አገኝሁት ,አቤት ማን ልበል አልኩት ና !አለኝ ቆጣ ብሎ ተጠጋሁት ስልክህን !አለኝ
አልሰጥም አልኩት !አምጣ !!ብሎ ጮኸ ሰጠሁት ሰማ ከዚህ በኃላ ከሜላት ጋ
እንዳላይህ
ካየሁህ ግን ከምድርገፀ ነው የማጠፋህ አለኝ ,ወዲያው ከፊት ለፊት የመኪና መብራት
በረጅሙ በራ ወደኛ ተጠጋ ,.የመኪናው መብራት አይኔን እየወጋኝም ቢሆን የግዴን
አየሁት
የሜላት ወንድም ነበር መኪናው ውስጥ የነበረው,አጠገቤ የነበረውም ግብዳ አስፈሪ
ሰውዬ ካስጠነቀቀኝ በኃላ መኪናው ውስጥ ገብተው ሄዱ,.
ሜላት የሰጠችኝ ስልክ አዲስ ሴም ነበር ግን ከስልኳ ውስጥ ነበር ስልክ ቁጥሩን
የወሰዱት
በስልክ እንደምንገናኝና ትምህርት ቤትም አብረን እንደምንውል ቤተክርስትያን
እንደምንገናኝም በደንብ ያውቃሉ ምክንያቱም በቅርብ እርቀት ይከታታሉን ስለነበር
,በጣም
አዘንኩ ትንሽ በር ላይ ከቆምኩ በኃላ ወደ ቤት ገባሁ ለእናቴ ሁሉንም ነገር ነገርኳት,በቃ
ይቺ አመት እስክትጠናቀቅ ድረስ አብራችሁ አትሁኑ አለችኝ ግን እንዴት አድርጌ ሜላቴን
እርቃታለው የማይታሰብ ነው ,.
ጠዋት ትምህርት ቤት ሄድኩኝ ሜላትን አገኝዋት ሰላም ተባባልን ,ጠዋት ደውዬ ነበር
ስልክህ ዝግ ነው አለችኝ ,ከዚያ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት በጣም ተናደደች በቃ
የራሴን
ውሳኔ መወሰን ሊኖርብኝ ነው በጣም አበዙት አለች ,ሜላቴ እንደዚህ እንዳታስቢ
ሁለታችንም ይችን አመት በሰላም ተምረን መጨረስ ይኖርብናል ከዛን በኃላ ፈጣሪ
ያውቃል
አልኳት ትንሽ ተርጋጋች ,.
እኔና ሜላት ከዛን ቀን ጀምረን ከትምህርት ቤት ውጪ በምንም አይነት ነገር አንገናኝም
ፈተና ስለደረሰ ያለችንን ሰአት አጣበን እናጠናለን ግን ተነፋፍቀን ስለምንገናኝ
ከምናጠናበት ሰአት ይልቅ የምናወራበት ሰአት ይበልጣል እኔ ከትምህርት መልስ እቤት
አጠናለው እሷ ግን አታጠናም,ፈተና ደርሶ ማትሪክ ተፈተንን! ሁለት ወር እንዴት ሊከረም
ነው ጭንቅ ሆነብኝ ገና ሳስበው.
አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ ቤተክርስቲያን ደርሼ ስመጣ የስራ ማስታወቂያ ለማንበብ ጠጋ
ብዬ ቆምኩ ድንገት አይኔ ተወርውሮ አንድ ስራ ላይ አረፈ እነ ሜላት ሰፈር ካሴት
(cd)ፊልም ማከራየት የወር ደሞዝ 150 ብር ይላል ደስ አለኝ ወዲያው ሄጄ ተነጋገርኩ
ስራ
ስላልነበረኝ እዛ ተቀጠርኩ ,.ስልክ ቤት ሄጄ ለሜላት ነገርኳት ደስ አላት ፊልም
ለመክራየት
እየመጣች እንደምንገናኝ ተነጋገርን,.
እቤት ሄጄ ለእናቴ ሁሉንም ነገርኳት ግን ክፍያው በቂ አይደለም ጫማ ብጠርግ በቀን
ከ150 ብር በላይ አገኛለው ብቻ ትንሽ ጊዜ ልየው ብዬ አሰብኩኝ,.እናቴ ደስ ያለህን
አድርግ አለችኝ.,ስራ ጀመርኩ ,ከሜላትም ጋ መገናኝት ጀመርን ስናፍቃት መጥታ አይታኝ
በአይን አውርተን እንለያያለን,እኔም ከቀጠረኝ ሰውዬጋ ተነጋግሬ በር ላይ ጫማ
መጥረግ
ጀመርኩ ታናሽ ወንድሜ ፊልም ማከራየት ጀመረ,.
እንደምንም ብለን ሁለት ወር ክረምት እየተገፋ ነው እኔም የአቅሜን እየሰራሁ ጫማ
እየጠረግሁ ጎን ለጎን የሞባይል ካርድ ማስቲካ ሌሎች ትናንሽ ነገሮችን እየሸጥሁ ነው
እናቴ
የሰው ቤት እንጅራ መጋገርና ልብስ ማጠብ ትታለች ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ
ማስተካከል ትሰራለች ባለቻት ሰአት ደግሞ ሽንኩርት ቃሪያ ድንች ትቸረችራለች
ተመስገን
አሁን ነገሮች እየተስተካከሉ ነው,.
ሁለት ወር ክረምት አለፈ የማትሪክ ውጤት ሊመጣ ነው ውጤቱ ምን እንደሚሆን
አይታወቅም ብቻ አሪፍ ውጤት አምጥቼ እንደምይልፍ እርግጠኛ ነኝ ከፈጣሪ ጋር
,.ሜላቴም እንድታልፍ ፀሎቴ ነው ብቻ መድረሱ አይቀር የማትሪክ ፈተና መጣ ሲባል
እኔም
ሜላትም ተያይዘን ውጤት ለመቀበል ሄድን ውጤትም ተቀበልን ግን .......
ይቀጥላል
እንዲቀጥል #like. #Share
👍👍👍👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍❤️👍🤣

@bosbitch


Ima Boss bith🔥🥀
@bosbitch
@itsdrakewife0


የድሀ ፍቅር

ክፍል 5
በእውነተኛ ህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ
ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ እየጠበቅን ነው ሜላት ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ
አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ አኮረፈች ሁሌም ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው
የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና ጉንጫን በእጆቼ ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት
ደስ
አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ,.
ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ ደንግጠን ዞር ስንል የሜላት አባት መኪና
ነበር
ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ,ሜላትም እሽ ብላ ቻው ብላኝ ወደ መኪናው ገባች አባቷ
እኔን
ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ.,
ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል ነበር ብዬ አሰብኩ ቀኑ አርብ
ስለነበር
ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን የለኝ ብቻ ጨነቀኝ እቤት ገብቼ
ለእናቴ
የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ አምላክ ያለው ይሆናል አለችኝ ,እሽ
አልኳት
በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ ሜላት የለችም ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ
ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም.,እሁድም አላገኝኃትም ይበልጥ ጨነቀኝ.,
ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ ሜላት ግን የለችም ተደውሎ ወደ
ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር ላይ ሲቆም ሰማሁ ዞር ስል የሜላት
ወንድም ሜላትን ይዞ መጣ ,ተንደርድሬ ሄጄ ሰላም ልላት ስል ዝም ብላኝ በቆምኩበት
ትታኝ ገባች ፈዝዜ ቀርሁ ለምን አልኩ ወንድሟ ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ እኔም
ቀስ እያልኩ ሜላት በቃ ተለየችኝ ተለያየን እያልኩ ወደ ክፍሌ አመራሁ.,
እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት እንደመጣች ሳላውቅ መጥታ
ተጠመጠመችብኝ
ከንፈሬን አንገቴን አይኔን
ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ አለችኝ ምን ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው
አልኳት ለረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ መምህር ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና
እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን.,
የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት የተፈጠረውን እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም
ጨንቆኝም ነበር ,መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ ሰአቱን መግፋት ብችል ገፍቼ አሳልፈው
ነበር
ግን አልቻልኩም ,የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ አይቀር ወጥቼ ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ
ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ አለችኝና ቁጭ አልን,.
ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ ጋር ከታየች ችግር
እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም እንዲጎዱህ ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት
ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም ብዬህ የገባሁት ከዚህ በኃላ ከ ትምህርት
ቤት
ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም ምናልባት ማታ ማታ ቤተክርስቲያን እንገናኛለን
አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት .,
ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ አውጥታ በዚህ ስልክ እንደዋወል
አለችኝ
እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ እንደምጎዳ በደንብ ገባኝ ከዝይች ቀን
ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ መገናኝት አቆምን
ሜላት
ማጥናት ትታለች በቃ ከኔጋር ለምዳ ብቻዋን ማጥናት አልቻለችም.,
የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት ተወጥሪያለው ሜላት ግን ማጥናት ትታ
እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ ላስጠናት እንደምችል ግራ ገብቶኛል ,ማታ
ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም እንዳላጠናች ነገረችኝ አጥኚ ነገ ከትምህርት
መልስ
እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ ብላኝ ቻው ተባብለን ስልኩ
ተዘጋ..በድጋሚ
ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር,........
ይቀጥላል.......
@ like 👍👍👍👍
@bosbitch ❤️


Ma crzy women🔥😍🥀❤️💕🇪🇹
Semuti ilu💕💕💕❤️❤️❤️🔥🔥🔥🥀🥀🥀🥀😍😍😍😘😘😘💯💯💯💯🌷🌷🌷🌷🤩🤩🤩🤩🤩💘💘💘💘💝💝💝💝💝💖💖💖💖💖💖💖👅👅👅👅 @bosbitch


😍View 🥀
@bosbitch 🔥


Jerrya❤️ her color killing me😣😣💕💕💕🥀🥀🥀🥀🥀🇪🇹🇪🇹🇪🇹🔥🔥🔥🔥🔥🔥🍫🍫🍫🇺🇲😍😍😍😍❤️❤️❤️❤️
@bosbitch


የድሀ ፍቅር

ክፍል 4

በእውነትኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ.
እኔና ሜላት ፈተና ስለደረሰ ሰናጠና አምሽተን ልሸኛት እንደወጣሁ ካፌ ሻይ ብና እንበል
ብላኝ ገብተን ቁጭ እንዳልን ድንገት የሜላት አባት ከፊት ለፊታችን ድቅን አሉብን .እኔ
ሰለማላውቃቸው ዝም አልኩ ሜላት ተርበተበተች ማ..ማነ አልኳት ?በጣቶቿ አፏን
ተመተመች ዝም በል ለማለት ነበር...
ሜላት ከመቀመጫዋ ተነስታ አ...አባቢ አለች እየተርበተበተች ,አባቢ ስትል ቀልቤ
ግፍፍ
አለ ..ደግነቱ ዩኒፎርሜን ከላይ ያለውን አላወለቅሁትም ነበር.የየየክፍሌ ተማሪ ነው
ስናጠና
ቆይተን ሻይ ብና እንበል ብለን ነው አለች እየተርበተበተች .,አባቷም ሰላምታ
አይቀድምም
ልጄ አሉ .,ይቅርታ አባቢ ብላ አቅፋ ሳመቻቸው .እኔም ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላም
አልኳቸው.
የሜላት አባት ሰላም ብለውን በጊዜ ግቢ ቻው ብለውን ሌላ ወንበር ወደ አለው
ጏደኛቸው
ሄዱ .,እኔና ሜላት ደንግጠናል ያዘዝነው መጥቶልን ቶሎ ቶሎ ጠጣን አባቷ ቀድመው
ሂሳብ
ከፍለውልን ስለነበር ቻው ብለናቸው ተያይዘን ወጣን.,.
ሜላት ፊቷ ላይ የፍረሀት ስሜት ይነበባል ሜላቴ ምን ሆንሽ ምን እያሰብሽ ነው
አልኳት.አባቢ አለች አባትሽ ምን አሁን እቤት ስገባ ጭቅጭቁ አይጣል ነው አለች
በፍረሀት
.አይቆጡሽም አስጠኒዬ ነው በያቸው ባይሆን ሁለተኛ አብረን እንዳያዬን እንጠነቀቃለን
አልኳት እሽ አልችኝና ግንባሯን ለመጀመርያ ጊዜ ስሜ ተለየኃት.,
ሜላትን በታክሲ ሽኝቼ እኔ ወክ እያደርግሁ ወደ ቤት ተመለስኩ ግን የሜላትዬ ፍርሀት
እኔን
አሳሰበኝ አባቷ ይቆጡ ይሆን ብዙ ነገሮችን አሰብኩ .ምክንያቱም የሜላት ቤተሰቦች
ሀብታም ስለሆኑ ልጃቸው ደግሞ ከእንደኔ አይነት መናጢ ድሀ ጋር የፍቅር ግንኝነት
እንዳላት ቢያውቁ ከባድ ነው የሚሆነው አምላኬ አደራህን ብዬ እቤቴ ገባሁ መንጋት
አይቀር ነጋ.
ጠዋት ትምህርት ቤት ቶሎ ሄድኩ በሩ ላይ ጠበቅኃት እሷም እንደምጨነቅ ስለገባት
በጠዋት መጣችልኝ ደስ አለኝ ቶሎ ብዬ ምን ተፈጠረ አልኳት .,ሰላም በልኝ እንጂ
ቅድሚያ
አለችኝ አቅፌ ሳምኳት .ምንም አልተፈጠረም አባቢ ምንም አላልኝም አለችኝ በጣም
ተደሰትኩ ለሚቀጥለው እንጠነቀቃለን አልኳትና ተያይዘን ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ
ገባን,.
እኔና ሜላቴ ፍቅራችንን በድብቅ አድርገን መዝናናትም ስንፈልግ ደበቅ ያለ ቦታ እየሄድን
እንዝናናለን .አብዛኛውን ጊዜ ግን እኛ ቤት ነው የምናሳልፈው.አመቱ አልቆ ተፈትነን
ውጤት
መጣ ሁለታችንም አልፈናል ደስ የሚል ነገር ተመስገን አልተነጣጠልንም.,
ሁለት ወር ክረምትን ያው እንደተለመደው እኔ እናቴን በማገዝ አሳለፍኩ ከሜላትም ጋ
አልፎ
አልፎ እቤት እየመጣች ካልሆንም ማታ ማታ እነሱ ሰፈር ቤተክርስቲያን ውስጥ
እንገናኛለን..በቃ ደስ በሚል መዋደድና መፈቃቀር አብረን ቀጠልን .,
አዲሱ አመት ገብቶ ትምህርት ጀመርን 12ኛ ክፍልን በጣም መጠናት እንዳለበት
ስለማምን ብዙ ጊዜያችንን በጥናት ነው የምናሳልፈው .ሜላትም ከኔ ጋር ታጠናለች
በርትተን መማር እንዳለብን ሁለታችንም እናምናለንና .,ስለዚህ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል
እናጠናለን.
እኔ ስናጠና ስለ ትምህርት ወክ ስናደርግ ስለ ነገ ተስፋ ነው የማስበው ወደፊት ምን
ማድርግ እንዳለብኝና ምን መሆን እንደምችል ብዙ ነገር ሜላትን እንደማገባት ነው
የማምነው ,.ሁሌም ስለያት ወይ ግንባሯን ወይ አንገቷ ስር ስሜ እለያታለው....
አንድ ቀን ማታ ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ሜላት ፊቷን ጥላዋለች አኩርፋለች ምነው
ሜላትዬ ምን ሆነሽ ነው አልኳት.,ሳመኝ አለችኝ አይናይኔን እያየች ,.እ!! አልኳት
ሳመኝኝኝኝ!
አልቸኝ ግንባሯን ሳምኳት ,ኡፍ ብላ ተበሳጨች ,ትዝ ሲለኝ እእእ አልኩና በእጆቼ
ጉንጭና
ጉንጫን ያዝ አድርጌ በስሱ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ አላት ምን ዋ ጋ አለው ታዲያ
ባልስማት
ይሻል ነበር አባ..,.....
ይቀጥላል
share. Like 👍👍👍👍👍
@bosbitch ❤️


የድሀ ፍቅር

ክፍል 3

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ.,
እናቴ በክረምት ወራት ሰርታ ያጠራቀመችውን ብር ሰብስባ ዩኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ
.ሜላት ቀድማ ዩኒፎርም አሰፍታ አመጣችልኝ ደነገጥሁ ለምን ገዛሽ ?እኔ እንድትረጂኝ
አልፈልግም::አልኳት ተቆጥቼ .ሜላትም ፊቷን አዙራ ከቤት ወጣች .ስቆጣ ሰምታኝ
የማታውቀው እናቴ ደነገጠች.እኔም ሜላትን ከመከተል ይልቅ ፈዝዤ ቀረሁ,....
ድንገት ታናሽ ወንድሜ ገፍትሮኝ ወደ ውጪ ሲሮጥ ብንን እንደማለት አልኩ .እንደዛው
እንደቆምኩ ብዙም ሳልቆይ ታናሼ ምን እንዳላት ባላውቅም ሜላትን ይዟት መጣ .እስኪ
ዞር
በል እንግባበት,ብሎኝ ይዟት ገብቶ ያለችው መቀመጫ የኔ የበሰበሰች ፈራሽ ላይ
ተቀመጭ
አላት,.
እኔ አሁንም ፈዝዣለው እማዬ ቡና አፍይ እስኪ አላት እናቴ እሽ ብላ ተፍ ተፍ ማለት
ጀመረች.አቦ አትቁምብና ና ተቀመጥ!!አለኝ እሽ ብዬ ሜላት ስር ቁጭ አልኩ ለማየት
ፈራኃት .እንዳቀረቀርኩ ይቅርታ አድርጊልኝ ሜላት አጥፍቻለው አልኳት ,!አይ ችግር
የለውም !!አለችኝ ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ አየኃት .እውነትሽን ነው አልኳት አዎ
አልችኝ,.እጆቿን ያዝ አድርጌ ሜላትዬ እውድሻለው አፈቅርሻለው ግን በገንዘብ
እንድትረጂኝ
ሳይሆን ንፁህ ፍቅርሽን ነው የምፈልገው አልኳት አይናይኗን እያየሁ.
እየውልህ የኔ ውብ እኔ እየረዳሁህ አይደለም ማደርግ ስለፈለግሁ እንጂ ደግሞ ካንተና
ከእናንተ ቤተሰብ የማገኘው ፍቅር ከሺ ሚልዮን ብር በላይ ደስታን ይሰጣል
.አትበሳጭብኝ
ይቅርታ እሽ አለችኝ .,ታናሽ ወንድሜ ጣልቃ በመግባት እድሜ ለኔ መለስኩልህ ፈዛዛ
ይኸኔ
እቤቷ ደርሳ ነበር አለኝ ተሳሳቅን ቡና ተፈላ ቤት ያፈራውን ቀማመስን በቃ ደስተኛ ሆነን
አመሽን በጣም ማምሽት ሰለማይፈቀድ ሜላቴንም ወደ ቤቷ ሸኘኃት.....
እኔም እሷን ሽኝቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ወደ ቤቴ ተመለስኩ..እናቴም ዩኒፎርም
ስለተገዛላት ያለው ብር ለደብተርና እስክርቢቶ ይሆናል ተመስገን አለች.ዞር ብላ አንተ
ከዚህ
በኃላ እንደዚህ ጮኸህ ስትቆጣ መስማት አልፈልግም አለችኝ.እሽ አልኳት,.
ቀናቶች ሄደው የትምህርት መሳሪያዎቼን አሟልቼ ትምህርቴን ጀመርኩ ሜላቴም እኩል
ጅመርን አንድ ክፍል መሆን ፈልገን ነበር ግን አልተሳካም መምህሮቹ አልፈቅድ አሉ
ይሁን
ብለን በክፍል ተለያየን ግን እርፍት ሲሆን እኔ ቀድሜ ቀወጣሁ እነሱ ክፍል በር ላይ
እጠብቃታለው እሷም ከቀደመች እንደዛው .ደስ የሚለው ሁላችንም ዩኒፎርም
ስለምንለብስ
የድሀ የሀብታም ልጅ ብሎ ነገር የለም .የሚበላ ስንፈልግ ሜላት ብር ሰጥታኝ እኔ
እከፍላለው .,
እኔና ሜላት ተለያይተን አናውቅም እኔም ከእሷ ውጪ እሷም ከእኔ ውጪ ትምህርት ቤት
ውስጥ ጏደኛ የለንም.ተማሪዎች ሁሉ ይቀኑብናል .እሷ ቆንጆ ነገር ስለሆነች ሌሎች
ይመኟታል እሷ ግን ከኔ ውጪ ማንንም አትፈልግም.,እኔም እንደዛው.
ከትምህርት ቤት ውጪ እኔ እናቴን ለማገዝ ስራ ስለምሰራ ብዙም አንገናኝም ጥናት
ካለብን ግን አብረን እናጠናለን ጥናት ስንጨርስ ወክ አድርገን እንለያያለን እናቴም
አብሮነታችን በጣም አስደስቷታል ደስተኛ ነች እኔም እንደዛው .አንድ ቀን ፈተና ስለደረሰ
ስናጠና ቆይተን ልሸኛት ወጥቼ ሻይ ቡና እንበል ብላኝ ካፌ ውስጥ ተቀምጠን
ያላሰብነው
ሰው ድንገት መጣብን.....
share.like👍
@bosbitch ❤️


የድሀ ፍቅር

ክፍል 2

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,
ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት ተጀመረ የማትሪክም
ውጤት
መጣ .በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ነበር ያለፍኩት .ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን
ስትስማ የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ .,ሜላትም አልፋለች በከፈተኛ
ውጤት
ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ
በልቤ!!
ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት እናቴ ጋ ሄድን
እናቴ
ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ
ጌታ
ሆይ አንተ ታውቃለህ አለች!!የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው ወረዱ እኔም
ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን ,"እናቴ ገና አኮራሻለው"አልኳት በጆሮዋ
የደስታ እንባ እየተናነቀኝ,.
ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ እንባዋ ይወርድ ነበር
,እኔና
እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን
ሰምቷል
ብላ ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች ,ናቲ
,"አይገርምህም
እኔም እንዳንተ ጅግና ነው የምሆነው"ብሎ መጥቶ ተጠመጠመብኝ .,ጎበዝ እንደዚህ
አስብ
እሽ ብዬው መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ,.
ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን አላውቅም.ወደ ኪሷ
ገብታ
20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ
አለችኝ
እሽ አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት.,
ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል አለችኝ
መሬት
መሬት እያየች .እኔ አሁን እቤት ስገባ ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን
ይሄን
ያክል ፍቅር ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች,.እኛ ቤት ንፁህ ፍቅር
እንዳለ አውቃለው የሷን ስትነግረኝ ግን ግራ ገባኝ.,ብቻ በፍረሀት ለምን?አልኳት .እ!
አለች,.እኛ ቤት ማንም ስለምይንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት
የአባቴ
ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት,.
አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ ለማንኛውም እንሂድ
አለችኝ
እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣ እሷን ታክሲ አስይዜ
ቻው
ተባብለን ተለያየን,.
ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ ፍቅር የለውም ,ለነገሩ
ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የነሱ
ቤተሰብ በሆንኩ.,!አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ ነው
::እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ .,እቤት ስደርስ እናቴ ብና አቀራርባ ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ
አለኝ ,"እናቴ እወድሻለው"ብዬ ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ.,
እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል,በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ
ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም
ሰነገጥኩ እኔ ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት,ሜላት ግን በቃ እሽ ብላ
ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች.እናቴ ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት
ፈዝዤ
ቀረሁ..........
ይቀጥላል
@share and like 👍
@bosbitch ❤️


Danawit 🤗🔥❤️🥀
@bosbitch


Ma Jb ❤️🙏😘
@bosbitch 🥀🔥
@Jbyeeeeeee




Hailu❤️
@bosbitch


It's about everything 🌍🌍🌍👀👀👀
Music's 🎶
Lifestyles
Funny pics 😄
GIFs😈
Videos 🔥
Stories 💥
Stickers 👙
Facts 😑
Challenges nd ma makeup works 🔥🔥🔥
JOIN
@Thug_life8

For more info 👇🏽
@Anacimos1991


Forward from: Hemi seyoum
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


My day maker ilusm ma kiki❤️🇪🇹💖💕


👟😍
@bosbitch

Ayu🇸🇴🇪🇹🌹


Chebera mood

@bosbitch
❤️❤️


Happy birthday too you ma lovey 🤗🎂ma kebite ❤️🎈
@bosbitch

20 last posts shown.

220

subscribers
Channel statistics