ኢክቲስ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified



Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በነገራችን ላይ ዕቅበተ እምነት ማለት እምነትን ማቀብ መጠበቅ ማለት ሲሆን እምነት ማለት ደግሞ ሃይማኖት ማለት ነው ስለዛ በዚህ ዘርፍ እምነትህን ትጠብቃለህ እንጂ እይታዎችን ሁሉ ለመጠበቅ አትደክምም ገድላትን ተአምራትን ጨምሮ ማለት ነው

ከሆነም ዕቅበተ ገድል ተብሎ እንጅ ዕቅበተ እምነት ተብሎ አይሰራም

@christo_kentrikos


አኬ የለቀቀውን አይቼ ነበር

የቤተ ክርስቲያን የሆኑ ገድላት ድርሣናት ተአምራንት ሁሉን የግድ መቀበል አለባችሁ ለሚሉ ሰዎች ጥያቄ ላቅርብና ከታች መረዳታችሁን አይቼ እቀጥላለሁ

ጥያቄ:

- “ተአምረ ኢየሱስ” ተብሎ የሚጠራ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ(በውጩ አለም ተመሳሳይ ታሪኮችን የያዘው መጽሐፍ የመናፍቃን ነው): እናም በዚህ መጽሐፍ ላይ ጌታችን በሕጻንነቱ ተአምር እንዳደረገ ተዘግቧል..

- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜው ላይ ጌታ በሕጻንነቱ ተአምራትን እየሰራ አልኖረም የመጀመሪያ ተአምር የሰራው ከጥምቀቱ በኋላ ነው ይላል

የቱን ተቀብላችሁ የቱን ትተዉታላችሁ? ያው ተቃራኒ ስለሆነ ማለት ነው እና ደግሞ በምንስ መዝናችሁ? በዚህ አስተሳሰባችሁን ተረድቼ እጽፋለሁ.. ጥያቄው ላይ የኔንም ምልከታ ከፈለጋችሁት አጋራችኋለሁ

@christo_kentrikos

2.8k 0 24 231 190

ፕሮቴስታንቲዝም ከጌታ ውጪ መሆናቸውን ከአባቶች አንጻር በጣም በቀላሉ ለማየት የጳጳሳትን ነገር ማየት ነው..

ማለትም ፕሮቴስታንቶች ከጳጳሳት ውጪ ናቸው.. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ደግሞ ያለ ጳጳስ ቤተ ክርስቲያን ትኖራለች ብሎ ያስተማረ ማግኘት ከባድ ነው.. በተቃራኒው እንደውም ጄሮም እንዲህ ይላል:-

“ያለ ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያን የሚባል ዓይነት ነገር የለም”
(Dialogue with the Luciferians, 21)

የዮሐንስ ወንጌላዊው ተማሪ ቅዱስ አግናጥዮስም እንዲህ ይላል፡-

“ከቤተ ክርስቲያን ጋር በተገናኘ ማንም ሰው ያለ ጳጳስ(ወይም እርሱ ከሾማቸው በቀር) ምንም አያድርግ... ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ያለ ጳጳስ በራሱ ማጥመቅ ሕጋዊ አይደለም።”
To the smyrneans: chap 8

ስለዛ በየመንደሩ የሚደረጉ የፕሮቴስታንትም ሆነ የማናቸውም ጥምቀቶች ያኔ የhighschool ተማሪ እያለን water day ብለን ከተራጨነው ውኃ የተለየ ነገር አይኖረውም ማለት ነው። ጥምቀት ያድናል የሚሉ ሉተራንንም ይመለከታል ይሄ።

ቆጵርያኖስም ለዛ ነው በነገራችን ላይ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድኅነት የለም.. ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለው ጥምቀት አያድንም ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት የሚያድነው ጥምቀት ያላት እያለ የሚናገረው(epistle 75: 2-3)

ያለጳጳሳት ምስጢራት አይፈጸሙም.. ሌሎች አገልጋዮችም አይሾሙም..
የጵጵስና ሹመት እንዴት እንደሆነ ደግሞ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን

@christo_kentrikos


እንኳን ደህና መጣችሁ፥ ከመጣችሁ አይቀር ደግሞ ትንሽ ላስተዋውቅ

- “christo_kentrikos” የሚለው የቻናሉ username ትርጉሙ በአጭሩ christo-centric ማለት ነው ይህም ማእከሉ ክርስቶስ እንደማለት ነው

- “ኢክቲስ” የሚለው ስም (ichthys) ትርጉሙ አሳ ነው እና ጥንት ላይ ክርስቲያኖች በኮድ እምነታቸውን የሚገልጹበት መለያ ነው እና ደግሞ ፊደላቱ ሲተነተኑ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መድኃኒት” የሚል ነው

- በጣም ለብዙ ጊዜ ሚዲያው ላይ ያለውን ነገር ለማየት ሞክሪያለሁ በየአቅጣጫው በተለይ የአኬን መንገድ እወደዋለሁ፥ ብዙ ነገርም ከሱ ተጋብቶብኛል ይኸው ቤት ውስጥ “ኧረ በቅዱስ ሚካኤል” እላለሁ🤭🤭 ከዛ ውጪ ግን ካለው ሁኔታ አንጻር ጥሩ ለመማማር እንሞክራለን

- የጥንት አባቶች ትምህርት ላይ አተኩርና በዛ በኩል እስልምና እና ፕሮቴስታንቲዝም ላይ የተወሰነ አካፍላችኋለሁ ብያለሁ እና ከዚህ ቀደም አኬ ኤቲዝም ላይም ቢሰራ ሲል ስለሰማሁት የተወሰነ እናያለን እሱንም

- በቅርቡ ደግሞ ቲክቶክ ላይ መጣለሁ

በተረፈ ሙዳችን ከገጠመ እንጫወታለን😁😁


ጌታ ሆይ አንተ ለራስህ አድርገኸናል፤
በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ልባችን እረፍት የለውም

የአውግስጢኖስ ኑዛዜ 1፡1

@christo_kentrikos
@christo_kentrikos

5 last posts shown.