High school students
አንዳንድ ሰዎች የሚጠይቋቸው አድክም ጥያቄዎች እና መመለስ ያለብን መልሶች
1, ከአሜሪካ ያለ ዘመድ ከሌሊቱ ሰባት ሰአት ደውሎ ተኝተሀል እንዴ?
: አይ ምስር እየለቀምኩ ነበር
2, ከፍቅረኛህ ጋር አልጋ ላይ ስትሳሳም ቆይተህ ልብስህን ማወላለቅ ስትጀምር: እንዴ ምን ልታረግ ነው?
: ፎቶ ልነሳ!
3:ሲኒማ ለመግባት ተሰልፈህ እያለ ውይ እዚ ደሞ ምን ታረጋለህ?
: የትምርት ቤት ክፍያ ልከፍል መጥቼ ነው ።
4, ለፍቅረኛህ እቅፍ ፅጌረዳ ልትሰጣት ሄደህ በርላይ ተቀብላህ ወይኔ አበባ ነው? ለኔ?
: አየ ድፎ ዳቦ ነው ወስደሽ ላባትሽ ስጫቸው ይባርኩት ።
4, ለበአል በግ ገዝተህ ወደ ቤት እየሄድክ, ለበአል ሊታረድ ነው?
: አይ በማደጎ ልናሳድገው ነው ። ተዋወቀው ወጋየሁ ይባላል ።
5:ከሻወር ገላህን ታጥበህ እንደወጣህ አግኝቶህ, ገላህን ታጥበህ ነው?
አይ ጎርፍ ውስጥ ወድቄ ነው።
6, ወደ ቢሮ ፎቅ ለመውጣት ሊፍት እየጠበቅህ, ወደላይ ነው ?
: አይ ሊፍቱ ቢሮዬን ሊያመጣልኝ ሄዶ እየጠበቅሁት ነው።
7: ሆቴል ገብተህ ጠረፔዛ በአይንህ እየፈለክ እያለ አስተናባሪው መቶ መቀመጫ ፈልገህ ነው?
አይ የእትዬ እልፍነሽ ውሻ ከሰፈር ጠፍቶ እያፈላለግነው ነው ።
😂😂😂😂😂😂
Join and share
@Cruiseinsiders