✍✍✍✍መልካም ዜና✍✍
የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ተጠባባቂ ለነበሩ 5106 ስራ ፈላጊዎች ቅጥር ሊፈጽም ነው!
የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ቢሮ ባለፈው በ0 ዓመት የስራ ልምድ በተጠባባቂ ተይዘው ከነበሩት ውስጥ ለ5106 ተወዳዳሪዎች ቅጥር እንደሚፈፅም ዛሬ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
የቢሮ ኃላፊው አቶ ኃይሉ ሉሌ እንዳሉት ቢሮው በህዳር ወር 2012 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ካገኙት በየካቲት ወር ላይ ለ8094 ያህሉ በውጤታቸው መሰረት ቅጥር መፈፀሙን አስታውሰው በተጠባባቂ ተይዘው ከነበሩት መካከልም ለ5106 ተወዳዳሪዎች ቅጥር እንደሚፈፀም ገልጸዋል፡፡
የቅጥር ሂደቱም ተወዳዳሪዎች እንደከዚህ ቀደም በwww.addis.gov.et የዌብሳይት አድራሻ ላይ የተመደቡበትን ተቋም ወይም ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም በማየት ከሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምረው በየተመደቡበት ቦታ ተገኝተው የኮቪድ-19 ቅድመ መከላከልን መሰረት ባደረገ ሂደት ሪፖርት እንዲያደርጉና የቅጥር ፎርማሊቲ እንዲያሟሉ አሳስቧል፡፡
መረጃው የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ልማት ቢሮ የፌስቡክ ገጽ ነው።