Daniel Aweke(ዮዳA)


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


🔊ዳኒ ነኝ! Follow አታድርጉ Fan ብቻ ሁኑ።
🔊ምክንያት ካላችሁኝ "Only God wanna Followers not Fans! "
🔊እናም ይኸ ገጽ የኔን ስራዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። "✍️ዮዳA "
Facebook:https://www.facebook.com/daniyeuodit.lij
Tiktok:@daniel_aweke
https://vm.tiktok.com/ZMM7JCXbQ/

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#2

ስነዝምሽ በልቤ አፍ
ከአንደበቴ ቃል ስነድፍ
ላንቺ ነው ሰመመኔ
ባንቺ ነው ሰቀቀኔ
የነዘምኩት መንዙማ
የጠለፍኩልሽ ሸማ
መለየትን ነው የሚያሰማኝ
ሲቀደድ ነው የሚታየኝ
አትፍራ ትይኛለሽ
በፈገግታ እየሳቅሽ
እንባዬን ሳልኩ
ጥርሴን በተንኩ
በእንባዬ ስእል ተሳለ
በሳቄ መከፋት ከፈነ
መቼ ነው የምገላገለው
ምጤ መች ነው የሚያበቃው
ደስታንስ መች ነው የምወልደው?
መኖሬንስ እንደ ጥቅም መቼ ነው ምወደው?
5:20(12,7,15)


#_1
በበረዶው ልቧ

የመከዳት እዳ ፍርሃቱ ቆርፍዷት
አዬ ወንድ ትላለች መተማመን ከብዷት

እኔ የሷ ጸሀይ
ይህን ፍርሃቷን ሳይ
ከልቧ ለራቀው ማዶ ላለው ልቧ
በረዶ በሰራው ለደደረ ቀልቧ
በገላጣው መንገድ ወደርሷ ሄዳለው
በመላጣው መንገድ እግር በጠረገው
ልቤን ከአካሌ አራምደዋለሁ
ግና ከርሷ ራቅሁ እንጂ መቸ አደርሳለሁ?
በረዶ ነው ልቧ እኔ አውቀዋለሁ
ደርሼ ላየሁ ስል ቀልጦ አገኘዋለሁ

22-04-015
11:04



3 last posts shown.

10

subscribers
Channel statistics