አንድ ሰው በባህር ብቻውን በጀልባ እየተጓዘ በማዕበል ተመታና ጀልባው ተሰባብራ በባህሩ ውስጥ ሰጠመች። ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል።
ምግቡን ዓሳ አያጠመደ እየተመገበ
ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ለምግብ የሚሆነው አሳ ሊያጠምድ ባህሩ ዳርቻ ላይ መንጠቆውን ይዞ ለረጅም ሰአት እየጠበቀ እያለ በድንገት ጭስ ሸተተው። ዞር ብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው። እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም።
ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ፤ ፈጠሪውን ወቀሰ፤ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለኸኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለህ ብሎ አለቀሰ፤ አማረረ።
ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ፤ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ፤ ተደሰተ። የመርከቡ ሰዎች መጥተው ጭነው ወሰዱት። ከዚያም ለመርከቡ ሰዎች ጠየቃቸው! እንዴት አገኛቹኝ?
እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት አገኛቹኝ?
አላቸው። መርከበኞቹም "እኛማ በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር። ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለን መጣን፤" አንተ አገኘን አሉት።
አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃዬ ልታውጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፍርስከው፤ ወደ ትልቁ ቤት ልትውሰደኝ ነው አለ።
✍ለበጎ ነው!!
ተስፋ ማድረግን ልማድ እናድርገው፡፡
Join: @direwoch