🔎 ሲም ካርድን ይተካል የተባለው #ኢ_ሲም ምንድን ነው…?
እንደ ኦ.ኢ.ኤም፣ አፕል እና ጎግል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች ደግሞ በአዳዲስ ምርቶቻቸው ላይ ኢ ሲም ማካተት መጀመራቸው ተሰምቷል። “ኢ ሲም ምንድን ነው”..? ካላችሁ ኢ ሲም ልክ እንደ መደበኛው ሲም ካርድ በስማርት ስልካችን ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው። ነገር ግን ኢ ሲም በቀጥታ በስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ የሚገጠም እንጂ እንደ ከዚህ በፊቱ አይነት ማስገቢያ የሚፈልግ እንዳልሆነ ተነግሯል። ኢ ሲምን አጠቃቀም አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ሲም ካርድ ጋር ሲነጻጸር ቀላል እንደሆነም ነው የተነገረው። እንዲሁም ኢ ሲም አንድ ጊዜ የስማርት ስልኩ ሰርኪዩት ቦርድ ላይ ከተገጠመ በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ እንደሚሆንም ነው የተጠቆመው። ከዚህ በተጨማሪም ኢ ሲም የስማርት ስልክ አምራቾች በጣም ጠፍጣፋ ስልክ ለማምረት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነም ነው የተገለፀው። በአሁኑ ወቅትም አንድ አንድ የስማርት ስልክ አምራቾች በስልኮቻቸው ላይ ከመደበኛው ሲም ካርድ በተጨማሪ ኢ ሲምን እንደ አማራጭ እያቀረቡ እንደሆነም ተነግሯል። አሁን በገበያ ላይ የዋሉ እና ኢ ሲምን የሚቀበሉ ስማርት ስልኮችም ጎግል ፒክስል 2፣ ጎግል ፒክስል 2 XL፣ ጎግል ፒክስል 3፣ ጎግል ፒክስል 3 XL፣ ጎግል ፒክስል 3a፣ ጎግል ፒክስል 3a XL፣ አይፎን XS፣ አይፎን XS Max፣ አይፎን XR፣ አይፓድ ፕሮ እና ኳልኮም ስናፕድራጎን 850 ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ዊንዶውስ 10 ኮምፒውተሮች ይገኙበታል
@droneethiopia