የጥቅም ትስስር እስከ ምን ድረስ?
———————
የጥቅም ትስስር ብዙ ሰዎችን እያወራቸው በተጨባጭ በዐይናችን እየተመለከትን ነው። የጥቅማጥቅም ትስስር ሰዎችን ሀቁን እያወቁት ዝም እንዲሉ እያደረጋቸው ነው። ሀቁን እያወቁትም ለባጢል እንዲሞግቱ እያደረጋቸው ነው።
የሚሞግቱት ግን ትላን ሲያስተምሩት የነበረውን ሀቅ ነው!፣ ዛሬ ላይ ደርሰው ያለ ማስረጃ እውነት ነው ብለው እውቅና የሚሰጡት ትላን በማስረጃ ሲያወግዙት የነበረውን ባጢል ነው። ይህ ደግሞ በዲን ላይ መቀያየር ነው!።
ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” አል-ኢባነቱል ኩብራ 571
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! የጥቅማጥቅም ትስስር ከሀቅ መንገድ ዘወር እንዳያደርጋችሁ ተጠንቀቁ!! ዛሬ ላይ ኡስታዝ ነው ስለ ሚንሃጅ ጠንቅቆ ያስተምራል ይባልለት የነበረን አካል ጥቅማጥቅም ምን ያህል እያወረው እንደሆነ እየተመለከትን ነው። በሀቅ ላይ ታገሱ! ፅኑ! ይህቺ የቅርቢቷ አለም እንዲህ እንዲህ እያለች የተሰጠችን አጭር ጊዜ አልቃ ወደ ቀጣዩና ዘላለማዊ አለም እየተሸጋገርን ነውና ለዘላለማዊ አለም የሚሆነን ስንቅ ይዘን እንጓዝ!!
የጥቅም ትስስር ትላንት የሚያውቁትና የሚያስተምሩት የነበረን ሀቅ እንደ አዲስ ሊደብቁት የሚታገሉ ኡስታዞችን እየተመለከትን ነው። ስለ ትላንቱ አቋማቸው ሲጠየቁ ማስረጃ ማቅረብ ስላቀታቸውና የትላንቱን እውነት መደበቅ ስላልቻሉ "አልበሰልንም ነበር" የምትል አስቂኝም አሳዛኝና አሳፋሪ መልስ መስጠቱን ከተያያዙት ቆየት ብሏል።
መብሰል አለመብሰል ከመች ጀምሮ ነው ማስረጃ መሆን የጀመረው? ሀቅ እስኪበስሉ ነው እንዴ የሚያዘው? ምንድነው ያበሰላቸው? በእድሜ ከነሱ በላይ የሆኑና በሳል የሆኑ ሰዎች እዚያው ሀቅ ላይ ፀንተው ነው ያሉት!፣ ወይስ ጥቅማጥቅምና ጎጠኝነት ነው ያበሰላቸው?
እንዲህ ያሉ ሰዎች ተማሪዎቻቸውንም ለማሳት እየታገሉ ይገኛሉ፣ ይሁን እንጂ ከማንም በፊት ትላንት ሀቅ ያስተማሯቸው ያራሳቸው ተማሪዎች "ዛሬ አቋም መቀየሩና መላላቱ ለምን አስፈለገ? ትላንት የተማርነውስ?" እያሉ በማፋጠጥ ሌላ ፈተና ሆነውባቸዋል!። ግራ ሲገባቸውም "አልበሰልንም ነበር" የሚል መልስ ከመደጋገም የዘለለ ማስረጃም ሆነ ሌላ መልስ ሊያገኙ አልቻሉም።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለራሳቸው ጠመው የሚያጠሙ መሪዎችን ፈርተውልናልና እንጠንቀቅ!፣ ኡስታዜ ስለሆነ ሸይኼ ስለሆነ ብለህ ወገንተኝነት አይያዝህ! ከሀቅ መንገድ ዘወር ካለ ሳታቅማማ ተጠንቀቀው!!።
መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ከምፈራው ነገር በጣም በህዝቦቼ ላይ የምፈራላቸው ነገር አጥማሚ መሪዎችን ነው።” ኢብን ሂባን የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሂሁል ጃሚዕ 1551 ላይ ሶሂህ ብለውታል።
ዘንግተውት እንጂ ከዱኒያ ጥቅማጥቅምና ብልጭልጭ አኺራ እንደሚሻል አምላካችን አላህ እንዲህ በማለት ተናግሯል:-
بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا۞ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ
«ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትሆን፡፡» አል አዕላ 16-17
እውነትን እንጂ የማይናገሩት፣ የተናገሩት ሁሉ የሚከሰተው ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰዎች ለዱኒያዊ ጥቅማጥቅም ብለው ዲናቸውን የሚሸጡበት ጊዜ እንደሚመጣ ተናግረዋል፣ አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:-
“በመልካም ስራ ተሽቀዳደሙ፣ (ከፊታችሁ) የጨለመ ሌሊት ቁራጭ አይነት ፈተና አለ፣ አንድ ሰው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሃዲ ሆኖ ያመሻል፣ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሃዲ ሆኖ ያነጋል፣ ዲኑን በዱኒያ ጥቅማ ጥቅም ይሸጣል።” ሙስሊም 198 ዘግበውታል
ከነቢያት በኋላ የነቢያት ወራሽ የሆኑ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች ዲኑ ለዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከነቢያት በኋላ ሰበብ የሆኑት የተለያየ ችግር ሳይደርስባቸው አይደለም፣ ነፍሲያቸውን ለዱኒያ ጥቅማጥቅም ብለው ዲናቸውን ከመሸጥ ተስፋ አስቆርጠዋት ነው።
ታላቁ የየመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
“አፈር እንኳ ቢሆን ልንበላ ዝግጁ ነን፣ (ለጥቅማጥቅም ብለን) ዲናችን እና ሀገራችን አናታልልም፣ አንቀያየርም! መቀያየር ከአህሉሱንናዎች ባህሪ አይደለም!”
[አልባዒስ ዐላ ሸርህ አል-ሀዋዲስ 57]
↪️ ልብ በሉ! የጥቅማጥቅም ትስስር ሲባል አይነቱ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት አያስፈልግም፣ ከፊሉ በደሞዝ፣ በንግድ ትስስር፣ ከሌላ ቦታ የተሻለ ደሞዝ በማግኘትና… ወዘተ በጥቅማጥቅም በመተሳሰር የሚያውቁትን ሀቅ ማምታት አለ።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ጁማዱል አወል 24/1442 ዓ. ሂ
#Join ⤵️
https://telegram.me/IbnShifa