#_ፍቅር_አቅመ_ሲያጣ
#_part_1
ምናልባትም እኔ ይህንን ታሪክ መስማት አልነበረብኝም ። እንኳን የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ትምህርት ጨርሼም ታሪኩ ለእኔ አዕምሮ በጣም ከባድ ነው ፡፡ ባለታሪኳ ህይወቷን ስትነግረኝ ከመስማት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር ፡፡ ለካስ ፍቅርም አቅም ያጣል ።
፣
መሰረት ትባላለች ። መሲ ማንም አይቷት የሚወዳት አይነት ልጅ ናት ። 9ኛ ክፍል ስትማር ነበር የፍቅር ጥይቄ መቀበል የጀመረችው ። በጣም ብዙ ደብዳቤ ቢደርሷትም አንዱም ግን ለእሷ power አልነበረውም ። ሁሌም ከፊቷ ፈገግታ አይጠፋም ። መልካምነት ለእሷ ብቻ የተሰጠ ይመስላል ። ማንንም አታስከፋም ።
፣
የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ልብ ውሰጥ መሲ አለች ። አስራ አንደኛ ክላስ ነው ባዮሎጂ መምህር ሁለት ሰአት እንደሆነ ማስተማር ይጀምራል ። 4 ተማሪዎች ማስተማር ከጀመረ በኋላ ይመጣሉ ። መምህሩም አስገባቸውና ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ አርፍዶ የመጣን ተማሪ ለአንድ ሳምንት በእኔ ክፍለ ጊዜ አይገባም የሚል አዲስ ህግ ነገራቸው ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መሲ አልነበረችም ።
፣
አርፍዳ ነበርና ህጉ ከወጣ በኋላ ክላስ ደረሰች ። ክላሱን ላለመረበሽ አስባ ሳታንኳኳ ልትገባ ስትል መምህሩ አስቆማትና አርፍደው የመጡ ተማሪዎችን እያባረርኩ ነው ። አንቺ ግን አላወቅሽምና ተማሪዎች ከፈቀዱ ትገቢያለሽ እንዳላት ። ተማሪዎች ባንድ ድምፅ ትግባ አሉ ። በመሀል ግን አንድ የተቃውሞ ድምፅ ተሰማ አቤል ነበር ።
፣
በፍፁም መግባት የለባትም አርፍዳለችና ትቀጣ ከእሷ ቀድመው የመጡትስ ለምን ተቀጡ ? ዛሬ እሷ ከገባች እኔም ከዛሬ ጀምሮ አረፍዳለሁ አለ ፡፡ የመሲ እና አቤል አይኖች ተገጣጠሙ ። ከዚህ በፊት ሰላም ብሏትም አያውቅም ። እየሮጠች ከክላስ ወጥታ ፣
@Ekutiiiii@Ekutiiiii@Ekutiiiiiክፍል-2
,,,,የመሲ እና የአቤል አይኖች ተገጣጠሙ፡ ከዚህ በፊት ሰላም ብሏትም አያውቅም ፡ እየሮጠች ከክላስ ወጥታ ወደ ቤቷ ሄደች፡ መምህሩ በአቤል ንግግር ተናዶ "ለዛሬ እዚህ ላይ ይበቃናል " የመሲ መሄድ መምህሩንም ጭምር አስከፍቷል፡ መሲ ቤት እንደደረሰች ሳጥኗን ከፍታ እስካሁን የተላኩላትን የፍቅር ደብዳቤዎች ማየት ጀመረች ፡ ነገር ግን ከደብዳቤዎቹ አንዱም አቤል የሚል የለም፡፡ እሱ ማን ነው? አለች መሲ፡ በነጋታው ወደ ትምህርት ቤት ስትመጣ አቤል ከክላሳቸው ፊት ለፊት ባለው ዛፍ ስር ተቀምጦ አገኘቺው፡ በነገራችን ላይ አለች መሲ ልክ እንደደረሰች እኔ ተማርኩም አልተማርኩ ፈተና መስራቴ አይቀርም ሌሎቹን ግን ጎዳሀቸው፡ አቤል ቅጣቷን ሳትጨርስ መምጣቷ ገርሞታል ፡ ሁለት የተቀጡት ተማሪዎች አንቺንም ጨምሮ ልትጎዱትችላላችሁ የተቀረው 50 ተማሪ ግን ይጠቀማል ምክንያቱም እናንተን እያየ አያረፍድም አላት፡ መሲ " እኔ በመቀጣቴ ምን ተጠቀምክ ? ስትለው አበል "ምንም, ምንም አልተጠቀምኩም ማለት ምንም አልተጎዳሁምም ጭምር ነው፡ አላት ፡ መሲ ጥላው ሄደች ፡ ያየኛል አያየኝም ብላ ዞር ስትል አቤል እንኳን ሊያያት ከቦታውም የለም፡ መሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናደደች እሱን በፍቅር ማሸነፍ አለብኝ አለች፡ ቀናቶች ነጎዱ መሲ አቤልን ለማሸነፍ በጣም ብዙ ነገር አደረገች እሱ ግን አልሰማማ፡ አቤል ክላስ ሁሌም ከሁለት የወንድ ጓደኞቹ ጋር ነው የሚቀመጠው ፡ አንድ ቀን ታዲያ ቦታው ላይ ተቀምጦ ጓደኞቹን እየጠበቀ መሲ መጥታ ቦታቸው ላይ ተቀመጠች፡ አቤል "ይቅርታ ጓደኛዬ ይመጣል " አላት መሲ ዝም ሰው አለው እያልኩሽ እኮ ነው መሲ "እኔ ሰው አይደለሁ?" አለች አቤል ምንም ሳይናገር ሌላ ቦታ ቀየረ ፡ ከዚህ ሰአት ጀምሮ መሲ ሌላ ሰው ሆነች፡ ተማሪዎች ፍቅር ይዟታል እያሉ ማውራት ጀምረዋል፡ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች አቤልን የህንድ አክተር ይሉታል አንዳንዶቹ ግሩም ኤርሚያስ ፡ መሲ ይሄንን መቋቋም አልቻለችም፡ በሆዷ ክፋትን አሰበች ፡ አቤልን መክሰስ፡ ከተፃፉላት የፍቅር ደብዳቤዎች አንዱን አቤል እንደፃፈው አስመስላ እያስቸገራትና እያስፈራራት እንደሆነ ተናግራ ከሰሰቺው፡ የግቢው ወሬ ይሄ ብቻ ሆነ ፡ አቤል ግቢው አስጠላው፡ የመሸኚያ ጥያቄ አቀረበ፡ ዳይሬክተሩ መሲን አስጠርቶ "ከዚህ በኋላ የሚረብሽሽ ተማሪ የለም አቤል ከዚህ ለቋል" አላት ፡፡መሲ ባነንዴ ተለዋወጠች፡ ለምን? ሳታስበው እንባዋ ይወርዳል፡ ማን አባሩት አላችሁ ?? ንግግሯ ከቢሮ አልፎ ወደ እስታፍ ደረሰ፡ ዳይሬክተሩ ግራ ተጋባ " አንቺ አይደለሽ እንዴ አስፈራራኝ ስትይ የነበረው? መሲ ,,,,,,,,,,,
ክፍል ሶስት ይቀጥላል
@Ekutiiiii@Ekutiiiii@Ekutiiiii💔💔💔