Ethio 251 Media


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ETHIO 251 is an independent media offering you News, Political Analysis and Information feeds from Addis Ababa, Ethiopia.
YouTube -- https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIAEthiopia

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


‹‹በሚዲያ የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል ብለህ ሕዝቡን አነሳስተሀል›› ሲል ፖሊስ ወነጀለ!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቧል። ጋዜጠኛው የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል በማለት መንግስትን አስገድዶ ከስልጣን ለማውረድ በሚዲያ ሲንቀሳቀስ ነበር። ተከባብሮ የሚኖርን ሕዝብ ለመለያት ሲሰራ ነበር የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፤ ለተጨማሪ ማጣራት 14 የምርመራ ተን ታስሮ ይቆይልን ሲል ፖሊስ ጠይቋል።

የጋዜጠኛው ጠበቆች በበኩላቸው ፤ የሚዲያ ባለሙያ ታስሮ የሚጣራበት የሕግ አግባብ የለም ስለዚህ የዋስትና መብቱ ተከብሮ በዋስ ይለቀቅ›› ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። አክለውም -ደንበኛችን ከሕግ አግባብ ውጪ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ 48 ሰዓት አልፎታል፤ የመብት ጥሰት ተከናውኖበታል ሲሉ ፖሊስን ከሰዋል። ፖሊስም ‹‹ከባህርዳር መከላከያ ነው የያዘው፤ ከነሱ እስክንረከብ ነው ጊዜ የሄደብን›› የሚል ምላሽ ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል።

በመጨረሻ፣ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ በጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ላይ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። በተያያዘ ዜና የኢትዮ ሰላም ሚዲያ ባለቤት የሆነውና ከጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሰው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው፤ በተመሳሳይ ክስ የተከሰሰ ሲሆን፤ የአስር ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ጊዜያዊ እስረኛ ማቆያ በእስር ላይ ይገኛል፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


በአማራ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የሚከተሉትን የቴሌግራም ገፆች ይቀላቀሉ።

1) https://t.me/D_free1

2) https://t.me/RasMeried

3) https://t.me/ethio251media

4) https://t.me/AmharaFirsttt

5) https://t.me/kokit2121

6) https://t.me/VOAamhara

7) https://t.me/Mulugetaanberberr

8) https://t.me/Qal_Alen

9) https://t.me/moresh143yo

10) https://t.me/Horn_African_News


ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide


በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊለቀቁ ይገባል
...
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችንና አባላትን፣ የሚዲያ አባላትንና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ዒላማ ያደረገ እስር እና ወከባ በእጅጉ አሳሳቢ መሆኑን ገለጸ። ኢሰመኮ በተለያየ ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ በተለይ የሚዲያ አባላትን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂዎችን (Activists) ጉዳይ በተመለከተ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ ከእነሱም መካከል ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር የዋሉ፣ የሚዲያ አዋጁን (የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013) በሚጻረር መልኩ የታሰሩ፣ በተራዘመ ቅድመ-ክስ እስር ወይም ክስ ሳይመሠረትባቸው በእስር የቆዩ መኖራቸውን፣ በተወሰኑት ላይ የወንጀል ክስ ተመሥርቶ የነበረ ቢሆንም ክሱ በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ በፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ ተደርጎ ወይም በፖሊስ ውሳኔ ከተራዘመ እስር በኋላ በነጻ ወይም በዋስትና የተለቀቁ መኖራቸውንም ኮሚሽኑ ተመልክቷል።

ኮሚሽኑ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እስከ አሁን ድረስ በእስር ላይ ከሚገኙት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮችንና የሌሎችም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ላይ የሚደርሱ እንግልት እና እስሮችን ጠቅሶ መንግሥት የሰዎችን በሕዝባዊ ጉዳዮች ውስጥ የመሳተፍ መብታቸውን የሚገድቡ ተግባሮችን የመመርመርና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት ማሳሰቡ የሚታወስ ነው። በቅርብ ጊዜ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያተኮሩ እስሮች እና ማዋከብ እናት ፓርቲን፣ በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲን እና የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲን ይጨምራል።

በዚህ ወር ውስጥ ብቻ ከታሰሩ የሚዲያ አባላት መካከል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻውን (አራት ኪሎ ሚዲያ) ጨምሮ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው (የኔታ/መድሎት ሚዲያ)፣ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ (ሮሃ ኒውስ/Roha News)፣ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው (ኢትዮ ሰላም)፣ ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ (የአማራ ድምፅ/Voice of Amhara)፣ ጋዜጠኛ በየነ ወልዴ (ጉራጌ ሚዲያ ኔትወርክ )፣ ጋዜጠኛ ሰናይት አያሌው (አሻራ ሚዲያ) ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ (ኢ ኤም ኤስ) እንዲሁም በማኅበረሰብ አንቂነት (Activist) እና በሚዲያ ሥራም የሚታወቁት መስከረም አበራ (ኢትዮ ንቃት) ይገኙበታል፡፡ ከፊሎች በእስር ወቅት ተገቢ ላልሆነ አያያዝ የተዳረጉ፣ ከፊሎች ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ እስር ተዳርገው የነበሩ እና፣ ከፊሎችም ከተለያየ ጊዜ መጠን እስር በኋላ የተለቀቁ ናቸው።

መንግሥት የወንጀል ተግባሮችን ሁሉ የመከላከል፣ የመመርመርና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና የማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ የሚያተኩር እስር ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብቶች ላይ የሚያስፈራራ፣ የሚያሸማቅቅ እና የሚገድብ ውጤት (chilling effect) እንዳይኖረው ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ነው።

በመሆኑም የመንግሥት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላትና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ እስርና ማዋከብ እንዲቆጠቡ፣ በወንጀል የተጠረጠሩና በበቂ ሕጋዊ ምክንያት በቅድመ-ክስ ሊታሰሩ የሚገባቸው ሰዎች በሚኖሩበት ሁኔታም በሕግ በተመለከተው መንገድ ብቻ በጥብቅ ጥንቃቄ አንዲፈጸምና የተጠረጠሩ ሰዎችን ሁሉ ከምርመራ በፊት ከማሰር እንዲቆጠቡ፣ በተጨማሪም በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 (የሚዲያ አዋጅ) መሠረት በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቤ-ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት መሆኑ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ፤ በዚሁ መሠረት እንዲፈጸምና በሚዲያ አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑ ታሳሪዎች በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቀቁ ኢሰመኮ ያሳስባል።

#Ethiopia #HumanRightsForAll

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


Forward from: Mulugeta Anberber
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


በመሳይ መኮንን

አልገባኝም ‼️

አልገባኝም። በእውነት አልገባኝም። የአማራ ክልል አመራሮች ምን እየሆኑ ነው? ህወሀት ሃይሉን አጠናክሮ ወደ ወልቃይትና ራያ ተጠግቷል። ባለፉት ሁለት ቀናት ይበልጥ ወደፊት በመምጣት ምሽጎችን በኮንክሪት እየሰራ ነው። ህወሀት ወደ ቀደመው ቁመናው እየተመለሰ ይገኛል። በወለጋ ከትላንት ሌሊት ጀምሮ ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ ዳግም አገርሽቷል። በተለይ አንገርጉትን በተባለችው ከተማ በርካታ ዜጎች መገደላቸውን ሌሊቱን በስልክ መረጃ ስቀበል ነው ያነጋሁት። ያነጋገርኳቸው ሰዎች ግድያውን የሚፈጽመው መከላከያ ሰራዊት ነው ይላሉ። ለማመን ተቸገርኩ። መለዮና ዩኒፎርም ተቀይሮ ካልሆነ በቀር መከላከያ በዚህ ደረጃ ግድያ ውስጥ ይገባል የሚል እምነት የለኝም። ከሆነ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ነው። ምናልባት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከስምሪት ውጪ ነው እያሉ የሚነግሩን የክልሉ ባለስልጣናት በሌላ ዩኒፎርም ልዩ ሃይላቸውን አሰማርተው ከሆነስ? ያነጋገርኳቸው ሰዎች የሸኔን ስም ተሳስተው እንኳን አልጠሩም። ምንድን ነው ነገሩ?

ትላንት አመሻሽ ላይ ከደሴ ወደ ሸዋ ሮቢት ያመሩ የነበሩ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት በኦነግ ሸኔ ተፈጸመ በተባለ ጥቃት በርካታዎቹ እዚያው ረገፉ። የተረፉት ወዴት እንደደረሱም አልታወቀም። መሳሪያ ተነጥቀው ባዶ እጃቸውን ነበር የተሸኙት። እጅና እግራቸውን ብቻ ይዘው እንዲሄዱ ተፈረደባቸው። አረ በህግ አምላክ?! ምን እየሆነ ነው? እስቲ የትኛው ክልል ልዩ ሃይል ነው በዚህ ደረጃ ትጥቁን የፈታው? የምን መደንዘዝ ነው? አቶ ግርማ የሺጥላ ስለዚህ ጉዳይ ምን አፍ ኖሮት የቴሌቪዥን መስኮት ላይ ይደቀናል? ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ይሄን ያህል ባርነት እንዴት ቻሉት? ተበልቶ ማስበላት። እንዴት ያሉ ጉዶች ናቸው የአማራን ክልል የሚመሩት ጎበዝ?!

ህወሀት ፈርጥሟል። ትጥቅ መፍታት የሚሉት የጅሎች ጨዋታ ነው ብሎናል። የኦሮሚያ ልዩ ሃይል መለዮ ይቀይር ይሆናል እንጂ ጫፉም የሚነካ አይደለም። የሌሎችም እንደዚያው። የአማራ ክልል ላይ የሆነው ግን ፍጹም ግራ የሚያጋባ፡ ወዴት እያመራን እንደሆነ አዛዦቹም፡ ተላላኪዎቹም፡ ሰለባዎቹም እርግጠኛ መሆን የማይችሉት አደገኛ አዝማሚያ ነው። እንዴት አንድ ስጋት ያለበት ክልል ባርነትን በገዛ ፍቃዳቸው የተቀበሉ ሰዎች ስልጣኑን ይዘው ለጌቶቻቸው ህዝብን እንደመስዋዕት በግ ያቀርባሉ? ይኸው ውጤቱን እያየነው ነው። የኤፍራታ ግድም ወረዳ አንድ አመራር እንደነገሩኝ ልዩ ሃይሉ ትጥቅ መፍታቱን ተከትሎ ሸኔ መሳሪያውን እየወለወለ ነው። መከላከያ አጠገባችን ሆኖ ትዕዛዝ አልተሰጠኝም ብሎ የልዩ ሃይል አባላቱን አስጨፍጭፏል ነው የሚሉኝ። በማይጠብሪ የልዩ ሃይሉን መውጣት እግር ተከትሎ ህወሀት ዘንባባ እያነጠፈ ሊገባ ተዘጋጅቷል። በራያ የልዩ ሃይሉ መውጣት ለህወሀት ሰዎች ጮቤ ያስረገጣቸው ዜና የሆነው ያለምክንያት አይደለም። ጎበዝ! ምን እየሆነ ነው ?

Mesay mekonnen (Anchor Media)
ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/




ኦነግ ሸኔ ትጥቅ በፈቱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ያደረገው ጭፍጨፋ።


ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ታፈነ!

የአማራ ተወላጆችን እያሳደደ ወደ እስር ቤት እያጋዘ ያለው የዐቢይ አህመድ መንግሥት በትላንትናው ዕለት አመሸሽ 12:30 ጎንደር ላይ የደህንነት አካላት በዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ላይ አፈና እንደፈፀሙበት አይን እማኞች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

በዐቢይ አህመድ የሚመመራው የደህንነት እና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል በቁጥጥር ስር አውየዋለሁ ካለ ከሳምንታት በኋላ አፈና ፈጽመውበታል። እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም።

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የትህነግ ኃይል ከብልጽግና መንግሥት ጋር ድርድር ለማድረግ ሲታሰብ የአማራ ሕዝብ እንዲደራደሩ ከወከላቸው ግለሰብ አንደኛው መሆናቸው ይታወቃል።

የጤና ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር አሚን አማን ቦታውን በለቀቁ ወቅት የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ለጤና ሚኒስትርነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧቸው የነበሩ ግለሰብ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "የአማራ ሸኔያችሁን፤ አሳልፋችሁ ስጡኝ" በሚል የአማራ ብልጽግና አመራሮችን ሲያስገድድ እንደነበር ከዚህ ቀደም ለኢትዮ 251 ሚዲያ ከውስጥ አዋቂዎች የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የመንግሥት ተከፋይ አክቲቪስቶች አጀንዳ ተሰጥቷቸው እንዲታሰር ጫና አድርጉ ተብለው እንደነበረ ኢትዮ 251 ሚዲያ ከደህንነት ምንጮች ማረጋገጥ ችላለች።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


#ሰበር
ትጥቅ በፈቱ በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ።

ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት በሁለት መኪና ተጭነው ይጓዙ በነበሩ ትጥቅ የፈቱ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት የከፈተው ኦነግ ሸኔ መሆኑን ለኢትዮ 251 ሚዲያ መረጃውን ያደረሱ ምንጮች ገልጸዋል።እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ጥቃቱ የተከፈተባቸው፤ ገርቢና ባልጪ በተባለ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ ነው።

የጥቃቱንና የተጎጂዎችን መጠን ለማወቅ ከሚመለከተው የክልሉ ቢሮ ደጋግመን ያደረግነው ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም። ሆኖም እንደመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የአማራ ልዩሀይል የህይወት መስዋዕት መክፈላቸውን ለማወቅ ችለናል።

በተያያዘ ዜና በወልቃይትና በራያ አላማጣ እና በኮረም በኩል ህወሓት ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ ሲሆን፤ በመተማ ዮሀንስ ሰፈር 4 የልማት ቦታ ደግሞ የሱዳን ጦር ዘልቆ መግባቱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


እነዚህን የቴሌግራም ቻናሎች በመቀላቀል ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ።


1) https://t.me/D_free1

2) https://t.me/RasMeried

3) https://t.me/ethio251media

4) https://t.me/kokit2121

5) https://t.me/Mulugetaanberberr


ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በሔሊኮፕተር ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እንደተወሰደ ታወቀ።

ትላንት በደህንነት ኃይሎችና በመከላከያ ኮማንዶዎች ከባህርዳር ሆምላንድ ሆቴል ታፍኖ የተወሰደው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ማታውኑ በሔሊኮፕተር ተጭኖ አዲስ አበባ እንደገባ ኢትዮ 251 ሚዲያ ማረጋገጥ ችሏል። 

ጋዜጠኛው አሁን በአዲስ አበባ ፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት እንደታሰረ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ማህበር መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል እና የአራት ኪሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


#የችሎት_ዜና
ጋዜጠኞቹ ተጨማሪ 10 ቀናትን በእስር እንዲቆዩ ተወሰነ

ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ ትናንትና ተጨማሪ 14 ቀናትን ጠይቆ ነበር።

የጋዜጠኞቹ ጠበቆች ተጨማሪ 14 ቀን መጠየቁ ተገቢ እንዳልሆነና ጋዜጠኞቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ በዋስ ሊለቀቁ እንደሚገባ ተከራክረዋል።

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት መዝገቡን አይቶ ለመወሰን ለዛሬ ሚያዚያ 03 2015 ጠዋት 3:00 ሰዓት ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ፤ በዛሬው ችሎትም ፍርድ ቤቱ ለፓሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀናትን ፈቅዷል።
በዚህም መሰረት ፖሊስ የቀሩትን የምርመራ ስራዎች አጠናቆ ሚያዚያ 13 እንዲያቀርብ ታዟል።
በምስጋናው ከፈለኝ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ተጨማሪ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው።

ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ጋዜጠኞቹ፤ ፖሊስ የምርመራ ጊዜዬን ስላላጠናቀኩኝ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን የጋዜጠኞቹ ጠበቆች በበኩላቸው "በባለፈው ጊዜ የተሰጠው 14 ቀን በቂ ነው፤ ፖሊስ በተሰጠው 14 ቀን ምርመራውን ሊያጠናቅቅ ሲገባው በድጋሚ መጠየቁ ተገቢ አይደለም፤ ጋዜጠኞቹ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ሊለቀቁ ይገባል" ብለው ተከራክረዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎትም መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመሰጠት ለነገ ሚያዝያ 3/2015 ዓ.ም 3:00 ቀጠሮ ይዟል።

በምስጋናው ከፈለኝ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ታሰረች።

መስከረም አበራ ዛሬ ሚያዚያ 01 ቀን ከምሽቱ 12:00 ላይ
የአዲስ አበባ ፖሊሶች የቤት ብርበራ ካከናወኑ በኋላ "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ" ብለው እንደወሰዷትና ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረች ባለቤቷ ለኢትዮ 251 ተናግሯል።

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የታሰረች ሲሆን በቅርቡ በአቋቋመችም ኢትዮ ንቃት ሚዲያ ስራ መጀመሯ የሚታወስ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


መምህርት እና የፖለቲካ ተንታኝ መስከረም አበራ ታሰረች!

የአማራ ሕዝብን ማሳደድ እና ማሰር መገለጫው የሆነው ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግሥት መምህርት እና የፖለቲካ ተንታኝ መስከረም አበራን ማሰሩን ኢትዮ 251 ሚዲያ አረጋግጧል።

መስከረም አበራ ዛሬ ሚያዚያ 01 ቀን ከምሽቱ 12:00 ላይ
የአዲስ አበባ ፖሊሶች የቤት ብርበራ ካከናወኑ በኋላ "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ" ብለው እንደወሰዷትና ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰረች ባለቤቷ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ የታሰረች ሲሆን በቅርቡ በአቋቋመችም ኢትዮ ንቃት ሚዲያ ስራ መጀመሯ የሚታወስ ነው።

ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና መንግሥት የአማራ ምሁራንን፣ ጋዜጠኞችን፣ ፖለቲከኞችን እና አክቲቪስቶችን እያሳደደ እያሰረ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በዚህ ወር ብቻ ከ10 ሺ በላይ የአማራ ተወላጆች በአዲስ አበባ መታሰራቸውን ኢትዮ 251 ሚዲያ ማረጋገጥ ችላለች።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


አርቲስት ዮርዳኖስ ዓለሜ ታሰረ።

" ያበጠው ይፈንዳ " በሚል ዘፈኑ የሚታወቀው አርቲስት ዮርዳኖስ ዓለሜ፤ ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 30/2015 ዓ/ም "ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ብለው እንደወሰዱትና እስካሁንም እንዳልተመለሰ ኢትዮ 251 ቤተሰቡን አነጋግሮ ማረጋገጥ ችሏል።

አርቲስት ዮርዳኖስ ዓለሜ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ዘማች ኪነት" በሚል መጠሪያ፤ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ለሰራዊቱ ግንባር ድረስ እየገባ የሞራል ድጋፍ ይሰጥ ነበር።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/


"የአማራ ልዩ ኃይል ለአማራ ሕዝብ የጀርባ አጥንት ነው።"
ጎንደር

የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘውን ኦህዴድ መራሹን የብልጽግና መንግሥት የጎንደር አማራ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሟል።

በሰልፉም የአማራ ልዩ ኃይል ለአማራ ሕዝብ የጀርባ አጥንት ነው፤ ሚኒሻ፣ አድማ ብተና እና የመፍረስ ተራችሁ ቅርብ ነው፤ የእርስቶቻችን ጉዳይ ለአፍታ የምንረሳው አይደለም እና ሌሎች መሰል የተቃውሞ ድምጿች ተሰምተዋል።

በተመሳሳይ በሌሎች የአማራ ከተሞች ሕዝባዊ ተቋውም እየተደረገ ይገኛል። እየተከታተልን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከኢትዮ 251 የተለያዩ የመረጃ መረቦች ያግኙ፦

ዩቱዩብ https://youtube.com/c/ETHIO251MEDIA
በቴሌግራም https://t.me/ethio251media
በፌስቡክ https: https://www.facebook.com/ethio251media/

17 last posts shown.

4 082

subscribers
Channel statistics