Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የአብስራ ፈርኒቸር በድሬ ዳዋ አስተዳደር መስቀለኛ አካባቢ የሚገኝ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን በማምረት በጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን ተደራሽ በማድረግ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

ውድ ተከታዮቻችን ስለኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎች ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።

🟩 ቴሌግራም፦ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

🟪 ፌስቡክ፡- ethiopianenterprisedevelopment

🟧 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCcYPTxshoazsonFU5ceQMgg

🔵ድረ ገጽ፦ https://www.sme.gov.et/

🟢 ኢ-ሜይል፡- ethiopianenterprise@gmail.com

🙏 ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን!።




🟩 የአብስራ ፈርኒቸር

===//===

EED የካቲት 27/2015 ዓ.ም

የአብስራ ፈርኒቸር በድሬ ዳዋ አስተዳደር መስቀለኛ አካባቢ የሚገኝ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን በማምረት በጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቹን ተደራሽ በማድረግ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

የአብስር ፈርኒቸር ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወይዘሮ ሙሉአበባ ሞገስ ድርጅቱ በ2007 ዓ.ም በቤተሰብ ደረጃ በአነስተኛ ገንዘብ ትንንሽ የእንጨት ስራ ውጤቶችን በማምረት የተቋቋመ መሆኑን ተናግራለች፡፡

የፈርኒቸሩ ስያሜ ድርጅቱን የመሰረተችው ትልቅ እህታችን ስም ነው፡፡ ጥሩ የእንጨት ስራ ሙያ ነበራት የምትለው ስራ አስኪያጇ የእሷ ታታሪ ሰራተኛ መሆን በዕድሜ ትንሽ የነበርነው እህት ወንድሞቿ ወደ ሙያው እንድንሰማራ አነሳስቶናል ብላለች፡፡

እህታችን አሁን ላይ በሕይወት የለችም የምትለው ሙሉአበባ እህታችን ሙያውን በደንብ አውቀነው ድርጅቱን እንድናሳድገውና የቤተሰባችን ሕይወት ተለውጦ የማየት ትልቅ ህልም ነበራት የእሷን ህልም እውን ለማድረግ እየሰራን ባለንበት ወቅት በ2010 ዓ.ም በአካባቢው በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ተከራይተው የሚሰሩበት ቦታ ሙሉ በሙሉ በእሳት ቃጠሎ እንደወደመባቸው ትናገራለች፡፡

በአካባቢው ማህበረሰብና ከቤተሰባቸው በተደረገላቸው ድጋፍ እንዲሁም ከኦሮሚያ ባንክ አንድ ሚሊየን ብር ብድር በመውሰድና እንደ አዲስ ከበፊቱ በተሻለ መልኩ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ በመስራት ዳግም ስራ ጀመርን ትላለች፡፡

የአብስራ ፈርኒቸር እነዚህን ውጣውረድ አልፎ አሁን ላይ በኪራይም ቢሆን ሁለት ትልልቅ የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎች እንዳሉት፣ ለ65 ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ካፒታሉም ከ5 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱንና ከሌላ ቦታ ተመርተው ወደ ድሬዳዋ የሚገቡ የእንጨት ምርቶች ማስቀረት እንደቻሉ ስራ አስኪያጇ አብራርታለች፡፡

የማምረት አቅሙንም በማሻሻል ኢንተርኔትን (በይነመረብ) በመመልከት የተለያዩ የቢሮና የቤት ዕቃዎች እንዲሁም ደንበኞች የሚያመጡትን ማንኛውንም አይነት ዲዛይን በጥራት በመስራት በተባልነው ጊዜና ሰዓት እናደርሳለን ይህ የኛ መለያችን ነው ብላለች፡፡
ምርታቸውንም በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቀርሳ፣ ጅግጅጋ፣ ጭሮ፣ ቁልቢና አወዳይ ከተሞች ድረስ በስፋት እንደሚሸጡ ተናግራለች፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለስራችን እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጎልናል የምትለው ሙሉአበባ የተለያዩ ስልጠናዎችን፣ መንግስት በሚያሰራቸው የቢሮ ዕቃዎች ላይ እንድንሳተፍ በማድረግና ያለብንን የመስሪያ ቦታ ችግር አይቶ በኢንዱስትሪ መንደር ለመስሪያ የሚሆን ሼድ እንደሰጣቸው ጠቁማለች፡፡

የመስሪያ ማሽን ችግር እንዳለባቸውና መንግስት ድጋፍ ቢያደርግላቸው ከዚህ የተሻለ ስራ በመስራት ተጨማሪ የስራ እድል ለመፍጠርና ምርቶቻቸውን በብዛት በሚጠቀሙ ከተሞች ላይ ቅርንጫፍ የመክፈት ሀሳብ እንዳላቸው ስራ አስኪያጇ ተናግራለች፡፡

🟩 የአብስራ ፈርኒቸር

👍 አድራሻ:- ድሬዳዋ ከተማ መስቀለኛ አካባቢ

☎️ ስልክ 09 20 89 84 48/ 09 09 62 76 77/ 09 40 87 44 73




“የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ አክሲዮን ማሕበራትን በሁሉም ክክሎችና አስተዳደሮች ለማቋቋም የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን”
አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED የካቲት 24 2015 ዓ.ም

የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ልማትን ለማፋጠን በሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ዙርያ እየተካሄደ ያለው የባሕርዳሩ የምክክር መድረክ እንደቀጠለ ነው፡፡
በመድረኩ ከቀረቡ ሠነዶች መካከልም “የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ተቋም ማቋቋም የሚኖረው ጠቀሜታ፣ በስራ ላይ ያሉ የሕግ ማዕቀፎችና ልምዶች” በሚል ርዕስ በአቶ መሳይ ኢንሠኔ የቀረበው ሠነድ ተጠቃሽ ነው፡፡ አቶ መሳይ የካፒታል ዕቃ አከራይ ተቋማት ዘርፍ ማሕበር ሲሆኑ በዚሁ ፅሁፋቸው የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ በሐገራችን በ2005 ዓ.ም የተጀመረ መሆኑን ገልፀው ይህም ከሐገራዊ ቅርፅ ይልቅ ክልላዊነትን ታሳቢ ባደረገ አግባብ የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበራቱ በደቡብ (ደቡብ) ፣ ኦሮሚያ (ኦሮሚያ)፣ በአዲስ አበባ (አዲስ)፣ በአማራ (ዋልያ) እና በትግራይ (ካዛ) የአክሲዮን ማሕበራት እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡

በዚህ መነሻነት በተደረገው ምክክር የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ በተቋቋመባቸውና በሌላቸው ክልሎች መካከል ግልፅ የሆነ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ውጤታማነት ልዩነት እየተፈጠረ መምጣቱን የገለፁት ተሳታፊዎች ይህ ልዩነት ይበልጥ ከመስፋቱ በፊትና ሐገራዊ ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄ ከመሆኑ በፊት በተለይም አክሲዮን ማሕበራቱን ያላቋቋሙ ክልሎች በቶሎ አቋቁመው ለኢንተርፕራይዞች የማሽነሪ ብድር ጥያቄ አፋጣኝና ምቹ የሆነ ስርዓትን መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋ/ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ በበኩላቸው ተቋማቸውየአክሲዮን ማሕበራቱን በማቋቋም አስፈላጊነት ዙርያ በቂ ግንዛቤ የመፍጠር እቅስቀቃሴን አስቀድሞ መጀመሩን ጠቅሠው ይህ እንቅስቃሴ ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንዲችል ከክልሎች ጋር ተከታታይነት ያለውን ውይይት ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡




#የዋልያ_የካፒታል_ዕቃ_ሊዝ_ፋይናንስ_አክሲዮን_ማሕበር ተቋማዊ ተሞክሮ ምን ይመስላል?

EED የካቲት 24 2015 ዓ.ም
ባሕርዳር
በባሕር ዳር ከተማ እየተካሔደ ባለው የዘርፉ ልዩ የምክክር መድረክ በተለይ የካፒታል ዕቃ ሊዝ አክሲዮን ማሕበር ላላቋቋሙ ክልልና አስተዳደር የአምራች ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ አመራሮች የዋልያ የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበር ተቋማዊ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡

ተሞክሮው በአክሲዮን ማሕበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ወንዳለ ጌታሁን የቀረበ ሲሆን ከቀረበው ሠነድ በማስታወሻችን ያስቀረነውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
#የዋልያ_የካፒታል_ዕቃ_ሊዝ_ፋይናንስ_አክሲዮን_ማሕበር በ2005 ዓ.ም የተቋቋመና እንደሐገርም በካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ዘርፍ የመጀመርያውን ፈቃድ የወሠደ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ ከአማራ ክልል ልዩ ልዩ ተቋማት በአክሲዮን ባሠባሠበው 400 ሚልየን ብር የተቋቋመ ነበር፡፡ በ11 ከተሞች አገልግሎት መስጠትን የጀመረው ተቋሙ ዛሬ ላይ በ192 ከተሞች ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

እስካሁን ከ4,460 በላይለሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች ግምታቸው ከ1.5 ቢልየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 12,671 ማሽነሪዎች በብርድ መልክ አሠራጭቷል፡፡ በዚህም ከ25 ሺህ በላይ የሆኑ ዜጎች ስራ ዕድል እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የካፒታል ዕቃ አቅርቦት ስርዓትን መዘርጋትና በዚህም ለኢንዱስትሪው ሠፊ መሠረት የሚጥሉ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከርን ዓላማው አድርጎ የተነሳው ዋልያ የኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ ጫና በመቀነስ በኩል የተሳካ የሚባል አፈፃፀምን አስመዝግቧል፡፡

ዋልያ ኢንተርፕራይዞች በብድር የሚፈልጉትን ማሽነሪ በዋናነት በራሳቸው እንዲመርጡ የሚያደርግ አሠራርን የሚከተል ሲሆን ይህም በብድር አሠጣጥ ወቅት የሚፈጠርን ቅሬታ ለማስቀረትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታን አስገኝቶለታል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሚያስከፍለው ክፍያ የአገልግሎት ክፍያ በመሆኑ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ጭምር ተመራጭ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን አስችሎታል፡፡

ከ25 ሺህ እስከ 10 ሚልየን ብር ዋጋ ያላቸውን ማሽነሪዎች በአንድ ጊዜ ለአንድ ኢንተርፕራይዝ የማበደር አቅም ያለው ዋልያ የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበር የዱቤ ግዢ (hire purchase) እና የፋይናንስ ኪራይ (financial lease) የተሠኙ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ሊዝ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራው የብድር ማስመለስ ምጣኔውን ከ99 በመቶ በላይ ለማሳደግ የቻለ ሲሆን አጠቃላይ ካፒታሉንም ወደ1.4 ቢልየን አሳድጎታል




“የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ድጋፍ አሠጣጥን ለማጠናከር ስፋት ያላቸው እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው”
አቶ ጳውሎስ በርጋ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋ/ዳይሬክተር

በዘርፉ ልማት ዙርያ ልዩ የምክክር መድረክ በባሕርዳር እየተካሄደ ይገኛል

EED የካቲት 24 2015 ዓ.ም
ባሕርዳር

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በዘርፉ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አገልግሎት አሠጣጥና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እንዲሁም ፍኖተ ካርታዎች ዙርያ የሚመክር መድረክ በባሕርዳር ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋ/ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደገለፁት እንደሐገር የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማቱን ውጤታማነት ለማሻሻልና በዘርፉ የሚጠበቁ ውጤቶችን ለማሳካት በተለይ በድጋፍ አሠጣጥ ዙርያ ያሉ ክፍተቶችን ጥናትን መሠረት ባደረገ አግባብ ለማሻሻል ሠፊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው፡፡

አቶ ጳውሎስ አያይዘውም የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅም መፍጠሪያ እንደመሆኑ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ውጤታማ የሆኑ ማሻሻያዎችን ማከናወን ያስፈልጋል፡፡ በ10 ዓመቱ የዘርፉ መሪ እቅድ መጨረሻ በዘርፉ 2 ሚልየን የስራ ዕድል ለመፍጠርና በዓመት እስከ11 ሺህ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የመፍጠር አቅም ላይ እንደሚደረስ አስታውሠው ይህን አቅም ለመፍጠር ዛሬ ላይ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ጠቅሠዋል፡፡

እነዚህን እንቅስቃሴዎች ለማሳካት የተቋሙ ተልዕኮዎች በአዲስ መልክ መሻሻላቸውን የጠቀሱት ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በዚህም የማምረቻ ክላስተር ማዕከላትን የመገንባትና የማስተዳደርንና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠትን ጨምሮ በርከት ያሉ አዳዲስ ተልዕኮዎችን መውሠዱን ጠቅሠዋል፡፡

በዚህም መሠረት ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦችን ለማሠባሠብ፣ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥና ልዩ ልዩ የጥናት ውጤቶችን የጋራ ለማድረግ የሚያስችለው ይህ መድረክ መመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ የእንኳን ደሕና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ም/ቢሮ ሐላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ የተሳኩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሠው በዚህም በሠው ሐይል ልማትና በካፒታል ዕቃ ፋይናንስ እንቅስቃሴው የበርካታ ኢንተርፕራይዞችንና የዘርፉ አስፈፃሚዎችን አቅም መገንባቱን ገልፀዋል፡፡

የዋሊያ ካፒታል ዕቃ ሊዝ አክሲዮን ማሕበርም የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አቅርቦት ላይ ባለፉት 10 ዓመታት ያሳየው የተሳካ ውጤታማነት በተለይ ይህን መሠል አክሲዮን ማሕበር ለሌላቸው አዳዲስ ክልሎችም ሆነ ነባር ክልሎች በተሞክሮነት መወሠዱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ ከሁሉም ክልሎችና አስተዳደሮች የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት ሓላፊዎች፣ አማካሪ ተቋማትና የሚመለከታቸው ተቋማት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን መድረኩ ነገም በልዩ ልዩ ርዕሠጉዳዮች እየተወያየ የሚቀጥል ይሆናል፡፡


እንኳን ለ ጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው  ለ127 ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ🇪🇹።



11 last posts shown.

2 038

subscribers
Channel statistics