TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Alexo Tech

12 Oct 2020, 07:36

Open in Telegram Share Report

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮች
አንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡ የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡
የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡-
1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም
ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡
2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም
ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡
3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር
በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡
4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት
ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡
5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ
የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
6. 2 ደቂቃ ቢያቆይዎት ነው፤ ነገር ግን ይሄን መረጃ ሼር ብታደርጉት የተቸገሩ ሰዎችን በጣም ይጠቅማቸዋል፡፡ አሁኑኑ ሼር አድርጉት፡፡

156 1 0
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Blog Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot