GK PASSPORT / VISA / TRAVEL


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ስለ ፓስፖርት እና ኢሜግሬሽን ጉዳዮች መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
ጥያቄ ካላችሁ ወይም ወረፋ ለማስያዝ
@fasilgk ወይም
@passportgk ላይ ያናግሩን

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🇮🇹 ጣልያን ወይም አውሮፓ 🇪🇺 ለትምህርት ከመሄዳችሁ በፊት #10 መደረግ ያሉባቸው ነገሮች #ሼር

→ ስኮላርሺፕ እስኪወጣ ድረስ ምን መደረግ አለበት? ስኮላርሺፕ ጊዜ የሚወስድ እና ሂደት ስለሚኖረው ከሀገር ለመውጣት ከመወሰን በፊት በቅድሚያ ይህንን እንድታቅዱ አሳስባለሁ

1) በትንሹ ለአንድ ወር የሚሆን በቂ 500€ ወይም ከዛ በላይ ገንዘብ መያዝ ይህንን ተበድራችሁም ቢሆን ውሰዱ መልሳችሁ በስራ ትከፍላላችሁ

2) የቤት ኪራይ ለመከራየት Idealista የሚባል App አለ እሱ ላይ ሰብሰብ ብሎ ከጓደኞች ጋር ደጋግሞ ቤት መፈለግ

3) ነገሮች እስኪስተካከሉ ከጓደኞች ጋር አማካኝ ቦታ መሰብሰብ ወጪ መቆጠብ!

4) ከአውሮፕላን እንደወረዳችሁ ከኤርፖርት ውጭ ስልክ ስለማይሰራ  ብትችሉ ምታርፉበትን ኤርፖርት ወጣ ብሎ ካለ ቦታ ሲም ካርድ እስከ 30€ ድረስ መግዛት።  ይህንን ያልኩት ከኤርፖርት ውጪ ዋጋ ስለሚቀንስ ነው

5) ወቅቱን የጠበቀ አለባበስ መልበስ ለምሳሌ የእጅ ጓንት፣ የሹራብ ኮፍያ ጆሮ ድረስ ሚሸፍን፣ ከላይ የሚለበስ ሞቅ ያለ ሹራብ እና ጃኬት

6) Google Translator App በማውረድ ሁሉንም ነገር ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎም መሄድ፣ ይህንን ያልኩት አውሮፓውያን ከማያውቁት ሰው ጋር ስለማያወሩ ቋንቋም ስለምትቸገሩ ነው።

7) Google Map በማውረድ አጠቃቀሙን ከወዲሁ በደንብ መላመድ፣ ባስ፣ ሱፐር ማርኬት፣ ትምህርት ቤት በማፕ ብቻ ነው የሚኬደው ማንም ሰው አያናግራችሁም አይጠቁምም

8) በትንሹ 100€ ካሽ በኪስ መያዝ፣ ገንደባችሁን በአግባብ ለሚገባው ነገር ማውጣት/መቆጠብ Reasonable ለሆነ ምክንያት ብቻ ማውጣት

9) ጎማ ያለው ሻንጣ መያዝ፣ በእጅ የሚያዝ የማይገፋ ሻንጣ በፍፁም አለመያዝ በቀጣይም ብዙ የማያስፈልግ ነገሮችን መቀነስ ወይም አለመያዝ ምግብን ጨምሮ፣ እንደኔ ድርቆሽ ነገር መያዝ እንጂ በርበሬ፣ ሽሮ ነገር አለማብዛት፣ ከጥቂት ጊዜ በሗላ እዛው መመገብ እና ለስራ መንቀሳቀሳችሁ አይቀርም ልብ በሉ። አንድ ትንሽ እና ከፍ ያለ ሁለቱም የሚገፋ ያዙ ከቦታ ቦታ ስትንቀሰቅሱ አትደክሙም

10 ) የተለያዩ ጣልያን ከሚማሩ ተማሪዎች እና ሊሄዱ ካሰቡ ተማሪዎች ጋር በቴሌግራም ቻናል ተፈላለጉ፣ Join አድርጉ ተጠያየቁ ተጠቃቀሙ። ገንዘብ ቅድሚያ ላኩ ከሚሉ Scammer ተጠንቀቁ ⚠️

Finally በትንሽ ወር አየሩን እና እራሳችሁን አላምዳችሁ ወደ ሌላ ስራ ስለምትገቡ፣ አውሮፓ ላይም ሆነ ወደ ሌላ ሀገር መንቀሳቀሳችሁ ስለማይቀር፣ በፈተና መፅናት፣ ፈተና በየትኛውም አጋጣሚ ይኖራል ብላችሁ ማመን እና Expectation ዝቅ አድርጋችሁ ከሀገር ውጡ፣ ስራ ያገኛችሁትን ስሩ አትናቁ። ይህ ትልቅ ምክር ነው በውነቱ ይሄንን ባውቅ ኖሮ ከብዙ ልፋት ድካም እድን ነበር


Congratulations for those who made it, መልካም እድል በርቱ 💪

@gk_passport


በጎተራ ቢሯችን ስንሰጥ የነበረው የፓስፖርት እደላ አገልግሎት ከጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሳሪስ አደይ አበባ ቀይመስቀል አጠገብ ወደሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ የተዛወረ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት


ከዚህ በፊት ፓስፖርታችሁን ውሰዱ ተብላችሁ ነገር ግን ያልወሰዳችሁ ስም ዝርዝራችሁ ከላይ አለ በአልፋቤታችሁ መሰረት ጎተራ በመሄድ ይቀበሉ




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የፓስፖርትዎን መድረስ በትራኪንግ ቁጥር ወይም በስምዎ ለማግኘት የቴሌግራም ቦት እና የዌብሳይት አማራጭ አጠቃቀም


ፓስፖርትዎ ታትሞ መድረስ አለመድረሱን ለማረጋገጥ ስም ዝርዝር የለቀቅን  ስለሆነ ስምዎን እና ያመለከቱበትን ቅርንጫፍ  ወይም ስምዎን እና የትራኪንግ ቁጥርዎን በቴሌግራም ቦታችን @ICSPassportBot ወይም በድረ-ገፅ አማራጭ passport.ics.gov.et ገብተው ያረጋግጡ


ለፓስፖርት እርማት  መሟላት ያለባቸው ሰነዶች

የፓስፖርትዎን እድሜ፣የትውልድ ቦታ፣ ፎቶግራፍ፣ፊደል ለማስተካከል መሟላት ያለባቸው
- ኦርጅናል ፓስፖርት (ፓስፖርቱ የጠፋ ከሆነ የፖሊስ ማስረጃ)
- የልደት ምስክር ወረቀት
- አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ

የፓስፖርትዎን ሙሉ ስም ለመቀየር
- የፍርድ ቤት ውሳኔ
- ኦርጅናል ፓስፖርት (ፓስፖርቱ የጠፋ ከሆነ የፖሊስ ማስረጃ)
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
- አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ


t.me/gk_passport


ፓስፖርታችሁ መድረስ አለመድረሱን ማወቅ ከፈለጋችሁ በዚህ @ICSPassportBot የቴሌግራም ቦት ገብታችሁ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።




ከመስከረም 27 ጀምሮ መቀሌ እና ጅግጅጋ ፓስፖርት የደረሰላችሁ




☝️☝️መመዝገብ የምትፈልጉ @gkpassport2 ላይ አውሩኝ


የ11 ዙር ሀገር አቀፍ የበጎፍቃድ አገልግሎት እጩ ሰልጣኞች ምዝገባ ይመለከታል


ሰላም ሚኒስቴር በ2017 በጀት አመት የ11ኛ ዙር የብሄራዊ በጎ ፍቃደኞችን አሰልጥኖ ለማሰማራት በዝግጅት ላይ ይገኛል በመሆኑም ከዚህ ደብዳቤ ጋር ተያይዞ የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ እና በበጎ ፍቃደኝነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው ወጣት በጎ ፍቃደኞች ኦንላይን ማመልከቻውን በመጠቀም ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 12//2017 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

✅የሚያስፈልገው መስፈርት
📎እድሜ ከ18-35 አመት የሆነ/ች፣
📎የኢትዮጲያዊ ዜግነት ያለው
📎በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 📎ከፍተኛ የት/ት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ው ወይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ዲፕሎማ ወይም 10+3 ያለው/ት
👉ስልጠናው ካጠናቀቁ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ የትኛውም አካባቢ ተመድቦ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ የሆነ/ች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልገው ስፍራ ሁሉ ለመንቀሳቀስ የሚከለክል የጤናና የአካል ብቃት ችግር የሌለበት/ባት
ነፍሰጡር ያልሆነች፣ጡት የሚጠባ ልጅ የሌላት

📎ጥሩ የሆነ ስነ- ምግባ ያለውና ከማንኛውም አይነት ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/ች በስልጠና እና ስምሪት ወቅት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ደንብና መመሪያ ለማክበር ሙሉ በሙሉ ፍቃደኛ የሆነ/ች

📎በወንጀል ድርጊት ተካፋይ በመሆን ያልተከሰሰ እና በፍርድ ጥፋተኛ ያልተባለ/ች

📎 ከዚህ በፊት የብሄራዊ በጎ ፍቃድ ስልጠና ላይ ያልተሳተፈ እና ስምሪት ያልወሰደ/ች

📎ስራ አጥ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚኖርበት አካባቢ ማቅረብ የሚችል/ችል።


23 መስከረም 2017.pdf
4.1Mb
ሰመራ መስከረም 23.pdf
830.9Kb
ከመስከረም 24 ጀምሮ አዲስ አበባና ሰመራ ፓስፖርት የምትረከቡ ስም ዝርዝር


https://t.me/gkpassport1

ከዚህ ግሩፕ 100 ሰው አድ አደረገ ፓስፖርቱ ፕሮሰስ ላይ ከሆነ ያለ ምንም ክፍያ በነጻ አይለታለሁ

አድ ካደረጋችሁ በኋላ በውስጥ አናግሪኝ


#Dv_ሎተሪ

ነገ መስከረም 22/2017 ይጀምራል

የአሜሪካ diversity visa ወይንም DV ሎተሪ ይጀምራል።

#አንደኛ

ማንኛውንም የሚሞላ ሰው የግድ 12ኛ ክፍል የጨረሰ መሆን አለበት። ወይንም በትንሹ 2 አመት በፈጀ ስልጠና ወይም ትምህርት ካለፉት አምስት አመታት ሁለት አመታት የስራ ልምድ ያለው መሆን ይጠበቅበታል።

12 ያጠናቀቀ እና ያላጠናቀቀ ግን የሆነ ስልጠና ይወስዳል ወይንም ትምህርት ለምሳሌ ላብራቶሪ ተማረ እንበል ትምህርቱን በአንድ አመት ቢጨርስ ለdv አይሆንም። ነገር ግን በትንሹ ሁለት አመት ቢማር መስፈርቱን ያሟላል ይህም ማለት አንድ ሰው ትልቅ ፋብሪካ ጥገና ቢሰራ ጥገናውን ግን ለመማር 6 ወር ወይንም አመት ቢፈጅበት መስፈርቱ በትንሹ 2 አመት የስልጠና እና ትምህርት ጊዜ ስለሚል ውድቅ ይደረጋል።

2 እና ከዛ በላይ አመት የተማረ ከሆነ ደግሞ ባለፉት 5 አመታት ማለትም ከ2011-2016 ባለ ጊዜ ውስጥ ስራ ላይ የነበረና 2 አመት ያገለገለ መሆን አለበት።

የተፈቀዱ የስራ አይነቶችን ለማወቅ በኤምባሲው የተቀመጠውን ጥቆማ

onetonline.org ድህረገፅ ላይ በመግባት Job family ሚለውን ተጭናቹ የስራ ዝርዝሮችን ማየት ይቻላል።

#ሁለተኛ

አመልካቾች የግድ 18 አመት የሞላቸው መሆን አለባቸው። ፎርሙንም አንዴ በትክክል ሞልቶ submit ማድረግ ማስገባት ሲገባ የተደጋገመ ሙሌት በመስሪያ ቤታቸው ቴክኖሎጂ ስርአት ውድቅ የሚደረግ ይሆናል።

እዚህ ጋር submit ብለነው ቀይ ምልክት እና ያልተሟላ መረጃ እንዲሁም እንዳልተቀበለን ካሳወቀን መስፈርቶችን እያሟሉ እና እያስተካከሉ ደጋግሞ መሙላት ይቻላል ያልተፈቀደው ከተቀበለ በውሃላ የሚደረጉ ድግግሞሾችን ነው።

ተቀብሎ submit ካደረገ በውሃላ ራሱ confirmation code ካልተሰጠን ስላልተመዘገብን ጥቂት ከጠበቅን በውሃላ ዳግም መሞከር ይቻላል። ቁጥሩን ካገኘን በውሃላ ግን ዳግም መሞከር ውጤታችን ውድቅ እንዲደረግ ያደርጋል።

#ሶስተኛ

ባለትዳር የሆኑ ሰዎች የግድ ባልም ሚስትም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ካሟሉ የተለያየ ወረቀት በየግል መሙላት ይችላሉ ካላሟሉ ግን የሚያሟላው ባልም ይሁን ሚስት ቅፁን ከሞሉ በውሃላ ሌላኛውን በጥገኛ ማስመዝገብ ይችላሉ። ሚስትና ልጆች ወይንም ባልና ልጆች የግድ ስማቸው መሟላት አለበት።

ልጆቹ ያላገቡ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በታች መሆን አለበት ይህ DV እስከሚሞላበት ቀን ድረስ።

#አራተኛ

አንድ አመልካች በሌላ መንገድ ወደአሜሪካ ለመግባት እየሞከረ ከሆነ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በፖለቲካ ጥገኝነት ተመዝግቦ ጉዳዩ በሂደት ላይ ያለም ቢሆን DV መሙላት እና የነፃ እድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። DV እድል በነፃ ቢሆንም እድለኞች ከደረሳቸው በውሃላ ወደአሜሪካ ለመሄድ የቪዛ ክፍያ መፈፀም አለባቸው።

ፎርሙንም ማንኛውም ሰው ለሌላ ሰው መሙላት ሲችል ሂደቱ እንደተጠናቀቀ መመዝገቡን ለማረጋገጥ

dvprogram.state.gov ላይ በመግባት check status የሚለውን በመጫን የሚሰጠውን የወረቀት ቁጥር ተጠቅሞ ማረጋገጥ ይችላል።

#አምስተኛ

አሸናፊዎች ከላይ ባለው ሊንክ ማለትም በ dvprogram.state.gov በመግባት የDV አዘጋጅ የሃገሪቱ ስርአተ-ክፍል ሰዎችን በማንኛውም መንገድ ለማግኘት አይሞክርም ( email , facebook , telegram) በመሳሰሉት የእንኳን ደስ አላቹ መልእክት አይልክም።

በመሃል confirmation code ቢጠፋባችሁ ባስገባችሁት email አድራሻ የመለያ ኮዱን እንዲልክላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

#ስድስተኛ

ፎቶ ፎቶቤት መነሳት የምትችሉ ሲሆን ምንም አይነት ፈገግታ ፣ የፀጉር መገልገያ (ሻሽ መሰል ጨርቆች) ፣ የአይን መነፅር ፍሬም አይንን መከለል የለበትም ፣ የጆሮ ጌጦች የማይፈቀዱ ሲሆን ለdv የምትጠቀሙት ፎቶ አሁናዊ ሁኔታችሁን ለማወቅ እንዲረዳ ቢበዛ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሳቹት ፎቶ መሆን አለበት። scan ድደርጋችሁ የምትጠቀሙ ከሆነ ለማስተካከል

123passportphoto.com/upload_photo.php

ድህረገፅን መጠቀም ትችላላችሁ።

ባለፉት አምስት አመታት ከ50 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን በማስወጣት በ2025 የDV ሎተሪ ቻይና ፣ ናይጄሪያ ፣ ፓኪስታን ፣ ባንግላዲሽ ፣ ቻይና ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ቬትናም ፣ ሜክሲኮ ፣ ቬንዙዌላ ፣ ጃማይካ ፣ ሆንዱራስ ፣ ኮሎምቢያ ፣ካናዳ እንዲሁም ብራዚል ያልተፈቀደላቸው ሃገራት ናቸው።

DV 2026 55,000 ( ሃምሳ አምስት ሺህ) እድለኞችን ይቀበላል

መልካም እድል!




📎👉የፓስፖርት ወረፋ መያዝ የምትፈልጉ ከዶክመንቶቻችሁ በተጨማሪ ይሄን ፎርም እየሞላችሁ ላኩልኝ

🔤ስም እስከ አያት በአማርኛ
✅የእርስዎ ስም__
✅የአባት ስም_
✅የአያት ስም__

🧍🧍‍♀ጾታ__

🔤ስም እስከ አያት በእንግሊዝኛ
✅Name :__
✅Father's Name:___
✅Grandfather's Name :____

⏱የትውልድ ቀን ወር እና አመት
✅የተወለዱበት ቀን:___
✅የተወለዱበት ወር:____
✅የተወለዱበት ዓመተ ምህረት__

🌐የተወለዱበት ቦታ__

👩‍❤️‍👨የትዳር ሁኔታ___

💳የልደት ምዝገባ ልዩ መለያ ቁጥር__

🏠አድራሻ
✅አሁን የሚኖሩበት ክልል____
✅የሚኖሩበት ከተማ____

📱ስልክ ቁጥር__


18 መስከረም፣2017.pdf
3.7Mb
ከመስከረም 20 ጀምሮ አአ ጎተራ ኢሜግሬሽን ፓስፖርት የምትረከቡ


መቀሌ ፣ ጅግጅጋ ፣ ባህርዳር ፣ ጅማ ፣ ሀዋሳ ፓስፖርታችሁ የደረሰላችሁ

20 last posts shown.