✍ውሻችን የገደለብን ሰው ግደ* ሉት!!
በአንዲት ገጠራማ መንደር ውስጥ የሚኖር አርብቶ አደር አባወራ ነበር። ይህ አባወራ የሚያረባቸው ከብቶች እና ልጆቹ አብረውት በዚችኑ መንደር ተሰብስበው ይኖራሉ። ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ ጥጋበኛ ይመጣና ለአርብቶ አደሩ ከብቶቹን ሲጠብቅለት የነበረው ውሻ ይገልበታል።
ይህንን ዐይተው የደነገጡ ልጆች በፍጥነት ወደ አባታቸው ሄደው የተከሰተው ይነግሩታል። አባታቸው………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብን ሰው ግደ* ሉት።" አላቸው።
ልጆቹ እርስ በእርስ እየተያዩ ተነስተው ወጡ። ከአባታቸው ጋ ከወጡ በኋላ ግራ ተጋብተው መነጋገር ጀመሩ። "አባታችን ግን ምን ሆኖ ነው? እርጅና ነው ወይስ እብደት? እንዴት: ሰው ለውሻ ይገደላል?" ተባብለው ነገሩን በቸልታ አለፉት።
ቀናቶች ካለፉ በኋላ የመንደሩ ወሮ_በላዎች ተሰብስበው ከዚሁ ቤት ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው ይሮጣሉ። ክስተቱን የተመለከቱ ልጆች ወደ አባታቸው ቀርበው ይነግሩታል። አባታቸው ፍፁም በተረጋጋ ስሜት………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብንን ግደ* ሉት" አላቸው።
ልጆቹ ይበልጥ ተናደዱ አዘኑም። አባታቸው ምንም የማያውቅ እርጅና ላይ መድረሱ ወይም አእምሮው ትክክል እንዳልሆነ ጠረጠሩ። "እኛ ስለ ከብቶች መሰረቅ እናወራዋለን እሱ ውሻ የገደለውን እንድንገድል ይነግረናል: ምን ዐይነት መዘባረቅ ነው?" ብለው ትተውት ሄዱ።
ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ከሚኖሩበት መንደር ራቅ ካለ ሰፈር የሚኖሩ ጎሳዎች ይመጡና የቤቱ ታላቋ እና ተወዳጇ ሴት ልጅ ጠልፈው ይወስዷታል። ልጆቹ ለአባታቸው ከመንገር ቅሮት አልነበራቸውምና አሁንም መጥተው መርዶው ይነግሩታል። እሱጋ ግን የተቀየረ ስሜትም ይሁን ንግግር አልነበረም………
"ሂዱና ውሻችን የገደለብን ግደ* ሉት" አላቸው።
ልጆቹ ከአባታቸው ጋ መግባባት ባለመቻላቸው እየተበሳጩ፤ በአባታቸው ሁኔታም እያዘኑ ግራ በመጋባት ላይ ሳሉ: ታላቁ ወንድማቸው "እንግዲያውስ ዛሬ የአባቴን ትዕዛዝ ልፈፅም ነው። የውሻችን ገዳይ እገድልና የሚፈጠረውን አብረን እናያለን" ብሎ ሰይፉን ስሎ ይሄዳል።
የውሻቸው ገዳይ ጋ ሲደርስ "አንተ ነህ የእኛን ውሻ የገደልከው?" ብሎ ካረጋገጠ በኋላ በቅፅበት ጭንቅላቱን ከአንገቱ ላይ በጠሰው።
ይህ ወሬ እንደጉድ ሀገሩ ላይ ተናፈሰ። ሁሉም ቦታ "የእንትና ልጆች ውሻችን ገድለሃል በሚል እከሌን ገድለ* ውታል" እየተባለ ይወራል።
ይህንን ዜና የሰሙ ዘራፊዎች "እነዚህ ሰዎች የውሻቸው ገዳይ የሚገድሉ ከሆኑ: እኛን ምን ሊያደርጉን ነው? በሚል ሰግተው ልክ መሸትሸት ሲል ጠብቀው የወሰዷቸው ከብቶች በአጠቃላይ አምጥተው ግቢ ላይ ለቀቋቸው።
ሴት ልጃቸው ጠልፈው የሄዱትም "የውሻቸው ገዳይ የሚገሉ ከሆኑ: ልጃቸው እና ክብራቸው ለደፈረማ ምንም ምህረት አይኖራቸውም" በሚል የጎሳቸው መሪ ለነበረው ንጉስ ለልጁ ሊድሯት ሽማግሌ መራርጠው ወደ አርብቶ አደሩ ቤት ላኩ።
ምን መሰለህ ወዳጄ…………
አንዳንድ መብቶችህ ሲረገጡ በዝምታ የምታልፍበት ሂደት በጣም ከበዛ ማንነትህ እና ህልውናህ የሚረግጥብህ ሌላ ቡድን ይመጣብሃል። በመብትህ ላይ የሚረማመዱ ጨቋኞቹ የሚቀያየሩብህ ግን እነሱ ጀግኖች ስለሆኑ ሳይሆን: አንተ ለመብትህ የማትጨነቅ ዝምተኛ በመሆንህ ነው።
ዛሬ ላይ………
በክልል አዋጅም ይሁን በተቋም ስርዓት ሊጣስ አይችልም የሚባለው የሀገሪቷ ህገ_መንግስት በመጣስ "ሙስሊም ሴቶች ሂጃብ መልበስ የለባቸውም" ብሎ የሚደነፋው የመንደር ዘገምተኛ ስርዓት ማስያዝ ካልቻልክ:
ነገ "ሙስሊም ወንዶች ፂማቸውን ማርዘም አይችሉም" ብሎ ያስልጭህና;
ከነገ ወድያ ደግሞ "ልጅህን አሕመድ ሙሐመድ ብለህ መሰየም አትችልም" የሚል አዋጅ ያፀድቅልሃል።
ይህ የሚሆነው ግን………
በእሱ ጀግንነት ሳይሆን: በአንተ ዝምታ ነው!!
Copy