"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢክላስ)
ክፍል አራት (4)
......ሁሉም በፍርሀት እና በጭንቀት ቀጥ ብለው እንደቆሙ ይገኛሉ። ከውጪ ያለው ማንኳኳት ግን ደጋግሞ መንኳኳቱን ተያይዞታል። የግቢው በር በተደጋጋሚ በመንኳኳቱ ግራ የሚገባ ስሜት ውስጥ ገቡ። ምክንያቱም ሰሚር ከሆነ የመጣው የግቢውም ሆነ የሳሎኑ ቁልፍ አለውና ለምን እራሱ ከፍቶ አልገባም ሲሉ እራሳቸውን ይጠይቃሉ። ሰሚር ካልሆነ ደሞ በዚ ምሽት የሚያንኳኳው ምን አልባትም ሀዋ ላይ ክፉ ድርጊት የፈፀመባት ይህ እኩይ ሰው ሊሆን ይችላልና ማን ከመሀከላቸው ከፍቶና ደፍሮ ሊወጣ እንደሚችል ግራ ተጋብተው ይተያያሉ።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ከተደጋጋሚ ማንኳኳቶች በኋላ ድንገት የሳሎኑ በር ተከፍቶ አንድ ሰው ብቅ አለ። ያ ባለግርማ ሞገሱ ፊቱ የሚያበራው ውድና ተወዳጁ ሰሚር ድንገት ገባ። እስካሁን ድረስ ቁልፍ እያለው ደጅ ላይ ሆኖ ሲያንኳኳ የነበረው ከሰአታት በፊት ደውሎ በነበረበት ሰአት ያናገረችው ሙና ነበረችና ምን አልባት ዛሬ እቤታቸው መጥተው በነበሩበት ሰአት አይብ ይኖራቸዋልና ድንገት ከፍቼ ብገባባቸው የማይሆን ነገር እንዳልመለከት ሲል ሀያእ አርጎ ነበር። ሰሚር ገና ከደጅ ሲገባ ልክ ሰው ከኤርፖርት እንደሚቀበሉ ነገር ሁሉም ተደርድረው ሲጠብቁት ግር መሰኘቱ አልቀረም። ከዛም ኻሊድ እና ሱመያ ተሯሩጠው አባታቸው ላይ ተጠመጠሙ። ናፍቆታቸውንም እቅፍ እና ሳም አርገው ከትወጡ በኋላ እትዬ መርየምን እና ሙናን አከታትሎ የሚገባቸውን ሰላምታ ስጣቸው። በመቀጠልም ከወንበሩ ቁጭ አለ።
የሰሚር እና የሀዋ ቤት እጅግ ላይን የሚማርክ ውብና ግማሽ ሶፋ እንደዚሁም በግማሽ አረቢያን መጅሊስ በሚያምር ጂብሰን የተቃኘ ውብ ቤት ነው። ሰሚር ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ አረፍ እንዳለ ውድያውኑ ተጠባቂውን ጥያቄ አፈፍ አረገው። በማለት ቀልድ የታጀበ ጥያቄ አቀረበ። ይሄን ግዜ ሙና ተቅለብልባ ወድያውኑ ሳታስበው በማለት መለሰች። ሰሚርም ደንገጥ ብሎ በማስከተል በማለት ጠየቃት። ሙናም በማለት መለሰችለት። ነገር ግን ሰሚር ዝም አላለም በማለት ጠየቃት። ይሄን ግዜ ሙና ደንግጣ ዝም ስትል...እትዬ መርየም ጣልቃ ገብተው ብለው መለሱለት።
ይሄኔ ሰሚር እትዬ መርየም እና ሙና ለምን ዛሬ እዚ ቤት እንደመጡ መልስ ያገኘ ይመስል አረፍ አለ። ምክንያቱም ትናንሽ ልጆቹን የሚጠብቁ ሰዎች ስለሚያስፈልጉ ሀዋ እዛ ካደረች የሁለቱ እዚ መምጣት የሚያስገርም አይደለም ብሎ ለራሱ መልስ ሰጠ። ግና ነገሮችን አምኖ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ የፈቀዱለት አይመስልም። እይታዎቻቸው፣ ድርጊቶቻቸው እና እርስ በእርስ መተያየታቸው ለሰሚር ከፍተኛ የሆነ የጥርጣሬ በር የሚከፍትለት ቢሆንም ሰሚር ግን መጠራጠር የፈለገ አይመስልም። ይሁን እንጂ የሰሚር አይኖች ውዷን ሀዋን እንደናፈቁ እጅግ በጣም ያሳብቃሉ። እሷን እሷን እየማተረ እንዳለ ልቡ ስለሷ እያሰበ እንዳለ አይኖቹ ልዩ ምስክሮች ናቸው። ይህ ስለሆነም ይመስላል ዛሬ ብዙም መጫወት ሳይፈልግ ድንገት ቀለል ባለ ሰላምታ ብቻ ተሰናብቷቸው ወደ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ጥቅልል ብሎ ለመተኛት የተገደደው። የሰሚር መተኛት ሀዋን መናፈቁ ቢገባቸውም እንኳን እነሱ ግን ይሄን አጋጣሚ አስቸኳይ ስብሰባ ለማድረግ እድሉን ተጠቀሙበት። በስብሰባቸውም ዛሬ በሸወዱበት መንገድ ነገ እና ከነገ ወዲያ ሰሚርን ስለማይሸውዱት እንዲያውም ሀዋ ከ አንድ ቀን በላይ እዛ አድራለች ብለው ለቅሶ ቤት ነው ያለችው ብለው መሸውድ እንደማይችሉ ልቦናቸው ስለተረዳ....ያለውን አጋጣሚ በመልካም ተጠቀሙት። በዚህም መፍትሄ ለማበጀት ይበልጡን ተጠጋጉ።
በውይይታቸው ላይም የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ከተሰነዘሩ ሀሳቦች መሀከል...ምን አልባት ልጅቷ ብቸኛ ስለሆነች ሀዋ ቤተሰቦቿን እያስተናገደች.....አልያም ደግሞ ሟች ክፍለ ሀገር ስለሆነ ቤተሰቦቿ ያሉት ልታስቀብር እዛው ሄዳ....ወይም ደሞ ዛሬ የመጣው ለቀስተኛ በጣም ብዙ ስለሆነ ሀዋ ምንም አይነት መውጫ እና መፈላፈያ ስላላገኘች እዛው ደጋገማ ለማደር ተገዳለች እና የመሳሰሉትን ሀሳቦች......ለስብሰባው ሰነዘሩ። ግን የትኛውም ሀሳብ አመርቂ ሆነው አላገኙም...ምክንያቱም በሰሚር አመለካከት ሀዋ ባሏ ከፊልድ መጥቶ ሰሚር እቤት ድረስ ትገኝቶ እንኳን ሰው ሞተ ብላ እራሷ እንኳን ብትሞት መቃብሩን ፈንቅላ ትመጣለች እንጂ እዛው የምትቀር አይደለችም። ይህን አመለካከቱን አሳምረው ስለሚያውቁ የትኛውም ሀሳብ አላጠገባቸውም። ይህን አየትባባሉ እየተወየዩ እና እየተነታረኩ መፍትሄ ላይ ሳይደርሱ ሁሉም ወደ መኝታቸው አመሩ።
ሁሉም በከፍተኛ እንቅልፍ ተውጠው አለማቸውን እረስተዋል። ነገር ግን አንድ አይን ብቻ እንቅልፍአልወሰደውም። እሷም ሙና....ሙና ዛሬ እንቅልፍ አልወሰዳትም። ምን እንዳሰበች አይታወቅም ቅጥ ያጣ አለባበስ ለብሳ እራሷን አቆነጃጅታ ከክፍሏ ድንገት ወጣች። ከዛም በሩጫ ሄዳ አንድ የመኝታ ቤት በርን በለሆሳስ ማንኳኳት ጀመረች። በንግግሯም ድምጿን እንዳሰሙ ቀንሳ በማለት ድምጾቿን አሰማች። ይህን ግዜ ሰከንዶችም ሳይቆጠትሩ እያንኳኳች የምትገኘው በር ድንገት ተከፈተ። ይሄኔ ያየችውን ሰው ማመን አቅቷት ደርቃ ቀረች። በሩ ከፍተው የወጡት እትዬ መርየም እንጂ ሰሚር አይደለም። መኝታ ቤቱን ተሳስታ ኖሮ ድንገት ሳታስብ የሳቸውን በር አንኳኩታ ነው።
ይቀጥላል........
https://t.me/halal_couples