TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ማር እስከ ጧፍ🙊😘🥰😜🙉

25 Apr, 20:57

Open in Telegram Share Report

ቬራ

ክፍል 43

ሀና "ተኩስ ምን ታመጣለህ"

አቡቹ "አባትና እናትሽ ፈሪ ነበሩ አንቺ ምንድነው የሚያውረገርግሽ"

ሀና "ሞት እኮ ክብር እንዳንተ ጭቃ ከመሆን"

አቡቹ "ምን ተማምነሽ ነው ቆይ"

ሀና "እመብርሃንን ነዋ"

አቡቹ "ሀሀሀ እሺ ወርዳ ታድንሽ"

ቢኒያም "ስርአት ያዝ"

አቡቹ "ምነው ሀይማኖትህ ሲነካ አንገበገበህ"

ቢኒያም "አዎ ያንገበግበኛል"

አቡቹ "ቆይ በእመብርሀን እተማመናለሁ ነው ያልሽው 🤣"

ሀና "እኔ አለ አባ ጊዮርጊስ ባንቺ የምተማመነው በውቅያኖስ እና በጠፈር መካከል ካለው አልማዝ ድንጋይ በላይ ያንቺን መጠጊያነት እተማመናለሁ

ለምን??? ካንቺ የተወለደው ለዳንኤል አናብስት ያሰገደ
ለሰልስቱ ደቂቅ እሳት ያጠፋ
ለእስራኤል ባህር የከፈለ
ለዳዊት ጠላት ያጠፋ ነውና ምኑን እፈራዋለሁ"

አቡቹ "እሺ ሰባኪያችን ሌላ የለሽም አትፈሪም ኧረ ምነው አሳጠርሽው ታዲያ"

ቢንያም "አትሳለቅ"

አቡቹ "ከኔ 10 ሰዎች የእናንተ እምነት ከበለጠ በል ሞክር"

ሀና "አውሬ እንዳልፈራ የአናብስቱን ጌታ
እሳት እንዳልፈራ የእሳቱ ጌታ
ውሀ እንዳልፈራ የባህሩ ጌታ
ካንቺ ማህፀን ተገኝቶልኝ ምኑን እፈራዋለሁ

ስለዚህ....

ከማርያም የበለጠ መመኪያ የለም
ሰማይ መጅ ቢሆን ምንድር ወፍጮ ቢሆን ከመሀል አርገው ቢፈጩኝ አንቺ እስካለሽ እኔ ምን እሆናለሁ"

የያዘውን ሽጉጥ አቀባበለው ስቃዩዋን ማየት ስለፈለገ ወደ ሆዷ ተኮሰ

አቡቹ "ምንም ካልሆንሽ እንይ"

ቅኔ "ምንድነው ያደረግከው ሀኒቾ ወይኔ ጉዴ"

ትንፋሿ መቆራረጥ ጀመረ ግን መናገሯን አላቆመችም
"እንደ ኖህ ዘመን ሰማይ ንፍር ውሀ ቢያዘንብ ምድር የፈላ ውሀ ብታወጣ አንቺ መከብ ከሆንሽልኝ እኔ ምን እሆናለሁ"

አቡቹ "አልሞት ባይ ተጋዳይ ነሽ"

ልጅ አለም "እጅ ወደላይ ሽጉጡን ጣለው በቁጥጥር ስር ውለሀል"

እጅ ከመስጠት የተሻለ አማራጭ አልታይ ስላለው ሽጉጡን አስረክቦ እንቱን በገበያ እንደሸኘ ህፃን አንገቱን ደፋ

ሀና በጣም ደሞ እየፈሰሳት ነበረ ይሄንን ያየችው ራሄል እናቷን ስላስታወሳት ለቅሶ ይሁን ምኑ ቅጡ የሌለው ድምፅ ማሰማት ጀመረች

ዶሮ ሆኗ ምግቧን ለማግኘት እየሞከረች ይመስል እርቧት እንደምትጭር ሁሉ ሀናን ትነካካታለች

ቢኒያም ይዟት ወደ ሀኪም ቤት ሮጠ....

282 0 1 32 27
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot