ክፍል 7⃣
ኒያና
"እኔ ማለት ሮቤል አለባቸው ነኝ አንድ እህት አለቺኝ እናቴና አባቴም አርፈዋል"
"እሺ ናፍቆቴን የት ነው ምታቀው"
"አላቀውም"
ትታው ስራዋን ጀመረች ወጥ ከሰራች ቡሀላ ሊጥ ማቡካት ጀመረች
"ለምንሽ ነው ውዴ"
"ውድህን ሄደህ ፈልግ ኬክ ለመስራት ነው"
"ለምንሽ ነው ኬክ"
"እሱን ስጨርስ ታየዋለህ"
"እሺ የኔ ቆንጆ"
መልስ ሳትሰጠው እስኪገርመው ምርጥ ኬክ ሰራች ቤቱን አስተካከለች ባይገባውም እያያት ነበረ ወደ መጨረሻ ልክ የሌለው ፈገግታ እያሳያት
"የኔ ንግስት ለዚ ነውኮ ምወድሽ ልደቴ መሆኑን አውቀሽ ነዋ የኔ አስታዋሽ አመሰግናለሁ"
ሁሉ ነገር ነው የተደበላለቀባት ናፍቆት የሚላትን ቃል በቃል ነበረ የደገመው እንባዋ መውረድ ጀመረ ቢጠራት አትሰማም
"ናፍቆቴ የኔ ልዑል እኔን አታመስግነኝ አላልኩህም አንተን ፍቅሬን ያላስታወስኩ..."
ሳትጨርሰው ራሷን ሳተች
"ያቆ ኧረ ያቆ የሰው ያለህ"
"ምንድን ነው....እንዴ ኒያ ምን ሆነች ኧረ ንቂ በፈጣሪ ስም"
"ከዚ በፊት ያማታል እንዴ"
"ፍቅሯና እህቷ አብዝተው ሲናፍቋት በቃ በወር አንዴ የሞቱበት ቀን ላይ ነበረ"
"አቃተኝ አቃተኝ ችሎበት መገኘት
በሌለኝ እውነታ እራሴን ማሞኘት
አሞኛል ሰላሜ ርቆኛል
ያለ መታመኔ ያንከራትተኛል
አሞኛል ሰላሜ ርቆኛል
ያወቁኝ ይመስል ሮቤል ይሉኛል
ናፍቆቴ እንቅልፍ እያሳጣኝ
በአይኖችሽ ጧት ማታ ሲቀጣኝ
ራሴን ለራሴ እየዋሸው
አለሁኝ ካንቺም እንደሸሸው"
በደንብ ሰምታዋለች በሰመመን ውስጥ እሷም ቀጠለች
"በናፍቆትህ እሳት ነድጄ ሳልከስል
ባይንህ በጠረንህ መልሼ እንዳገግም
ልምጣ ያልክ እንደሆን ቀና ነው ጎዳና
ልቤ ተመላልሶ ደልድሎታልና"
"ንቂ ኒያዬ የኔ እህት እባክሽ በቃሽ ለኔ ለወንድምሽ ስትይ"
👰♀"ናፍቆቴ ልደቱ ነው ዛሬ ና በለው ያቆ"
🙎♂"በቃ እሱኮ ሞቷል ተይው በቃ"
👰♀"አልሞተም አባባ አልሞተም ብሎኛል"
🙎♂"እየቃዠሽ ነው መንፈስ ታምኛለሽ"
👰♀"አዎ ወንድሜ አምነዋለሁ አልሞተም"
🙎♂"ሮባ አንድ ነገር በላት እንጂ"
🤵"ምን ልበላት እኔኮ ስለምታወሩለት ሰው አላቅም"
👰♀"እሱ ነው ወንድሜ እሱ ነው ናፍቆቴን ነው የሚመስለው"
🙎♂"ወይኔ እህቴ ምናቸው ነው ሚመሳሰለው"
👰♀"ሁሉ ነገሩ ነው ንገረው አንተ"
🤵"ምን ልንገረው"
👰♀"ናፍቆቴን እንደምትመስል ንገረው"
🤵♂"እኔ እሱን አላቀውም እኮ በምኔ ልመስክር"
♦️♦️♦️በሌላ ትእይንት♦️♦️♦️
"ያቺን እንሽላሊት ቆርጬ ልጣላት"
"ቆይ እናንፈራፍራት እንጂ"
"እንደዛ ይሻላል ወጥመዱን ልጣልባታ"
"በይ ቀጥይ የኔ ጀግና እህት"
"እጅና እግርህን ቆርጣ በሰላም የምትኖር መሰላት እንዴ ዝም በይ ብለህ እንጂ ምላሷን እቆርጥላት ነበረ"
"ሀማን ደሞ አትቸኩይ እኔ የማዝሽን ብቻ አርጊ"
"ቀጣይ ምን ላርግ እሺ"
"አብሯት የሚንጦለጦለውን ያዕቆብ እጅና እግሬን አስመልሽልኝ"
"በጣም ጥሩ እና መቼ ይሁን"
"ነገውኑ ደሞ ሰው ያዢ ልጅቷ አትቻልም እንዳትነድፍሽ"
"ለሷ ጣጣ የለም ናፍቆት ከተጠራ ትሽመደመዳለች"
ኒያና
"እኔ ማለት ሮቤል አለባቸው ነኝ አንድ እህት አለቺኝ እናቴና አባቴም አርፈዋል"
"እሺ ናፍቆቴን የት ነው ምታቀው"
"አላቀውም"
ትታው ስራዋን ጀመረች ወጥ ከሰራች ቡሀላ ሊጥ ማቡካት ጀመረች
"ለምንሽ ነው ውዴ"
"ውድህን ሄደህ ፈልግ ኬክ ለመስራት ነው"
"ለምንሽ ነው ኬክ"
"እሱን ስጨርስ ታየዋለህ"
"እሺ የኔ ቆንጆ"
መልስ ሳትሰጠው እስኪገርመው ምርጥ ኬክ ሰራች ቤቱን አስተካከለች ባይገባውም እያያት ነበረ ወደ መጨረሻ ልክ የሌለው ፈገግታ እያሳያት
"የኔ ንግስት ለዚ ነውኮ ምወድሽ ልደቴ መሆኑን አውቀሽ ነዋ የኔ አስታዋሽ አመሰግናለሁ"
ሁሉ ነገር ነው የተደበላለቀባት ናፍቆት የሚላትን ቃል በቃል ነበረ የደገመው እንባዋ መውረድ ጀመረ ቢጠራት አትሰማም
"ናፍቆቴ የኔ ልዑል እኔን አታመስግነኝ አላልኩህም አንተን ፍቅሬን ያላስታወስኩ..."
ሳትጨርሰው ራሷን ሳተች
"ያቆ ኧረ ያቆ የሰው ያለህ"
"ምንድን ነው....እንዴ ኒያ ምን ሆነች ኧረ ንቂ በፈጣሪ ስም"
"ከዚ በፊት ያማታል እንዴ"
"ፍቅሯና እህቷ አብዝተው ሲናፍቋት በቃ በወር አንዴ የሞቱበት ቀን ላይ ነበረ"
"አቃተኝ አቃተኝ ችሎበት መገኘት
በሌለኝ እውነታ እራሴን ማሞኘት
አሞኛል ሰላሜ ርቆኛል
ያለ መታመኔ ያንከራትተኛል
አሞኛል ሰላሜ ርቆኛል
ያወቁኝ ይመስል ሮቤል ይሉኛል
ናፍቆቴ እንቅልፍ እያሳጣኝ
በአይኖችሽ ጧት ማታ ሲቀጣኝ
ራሴን ለራሴ እየዋሸው
አለሁኝ ካንቺም እንደሸሸው"
በደንብ ሰምታዋለች በሰመመን ውስጥ እሷም ቀጠለች
"በናፍቆትህ እሳት ነድጄ ሳልከስል
ባይንህ በጠረንህ መልሼ እንዳገግም
ልምጣ ያልክ እንደሆን ቀና ነው ጎዳና
ልቤ ተመላልሶ ደልድሎታልና"
"ንቂ ኒያዬ የኔ እህት እባክሽ በቃሽ ለኔ ለወንድምሽ ስትይ"
👰♀"ናፍቆቴ ልደቱ ነው ዛሬ ና በለው ያቆ"
🙎♂"በቃ እሱኮ ሞቷል ተይው በቃ"
👰♀"አልሞተም አባባ አልሞተም ብሎኛል"
🙎♂"እየቃዠሽ ነው መንፈስ ታምኛለሽ"
👰♀"አዎ ወንድሜ አምነዋለሁ አልሞተም"
🙎♂"ሮባ አንድ ነገር በላት እንጂ"
🤵"ምን ልበላት እኔኮ ስለምታወሩለት ሰው አላቅም"
👰♀"እሱ ነው ወንድሜ እሱ ነው ናፍቆቴን ነው የሚመስለው"
🙎♂"ወይኔ እህቴ ምናቸው ነው ሚመሳሰለው"
👰♀"ሁሉ ነገሩ ነው ንገረው አንተ"
🤵"ምን ልንገረው"
👰♀"ናፍቆቴን እንደምትመስል ንገረው"
🤵♂"እኔ እሱን አላቀውም እኮ በምኔ ልመስክር"
♦️♦️♦️በሌላ ትእይንት♦️♦️♦️
"ያቺን እንሽላሊት ቆርጬ ልጣላት"
"ቆይ እናንፈራፍራት እንጂ"
"እንደዛ ይሻላል ወጥመዱን ልጣልባታ"
"በይ ቀጥይ የኔ ጀግና እህት"
"እጅና እግርህን ቆርጣ በሰላም የምትኖር መሰላት እንዴ ዝም በይ ብለህ እንጂ ምላሷን እቆርጥላት ነበረ"
"ሀማን ደሞ አትቸኩይ እኔ የማዝሽን ብቻ አርጊ"
"ቀጣይ ምን ላርግ እሺ"
"አብሯት የሚንጦለጦለውን ያዕቆብ እጅና እግሬን አስመልሽልኝ"
"በጣም ጥሩ እና መቼ ይሁን"
"ነገውኑ ደሞ ሰው ያዢ ልጅቷ አትቻልም እንዳትነድፍሽ"
"ለሷ ጣጣ የለም ናፍቆት ከተጠራ ትሽመደመዳለች"