ክፍል 8⃣
ኒያና
"ለሷ ጣጣ የለም ናፍቆት ከተጠራ ትሽመደመዳለች"
ሰይጣናዊ ፈገግታ ፈገግ አለች
በቀል ግን ከሞት ይከፋል አይደል አዎ ምክንያቱም ገደብ የለውም የሰው ልጅ ልክ ከሚያጣ ደሞ መሞት ይሻለዋል
ጥርሱን ነከሰ ለእህቱ ቢያዝንም ግን ደሞ በቀል ፈልጓል ኒያናን ይፈራታል ግን እጅና እግሩን አሳጥታዋለች
እያንዳንዱ ጥላቸው በበቀል ሰበብ ነው ማን ጀመረ እንጃ ሁሉም መጠቋቆም እንጂ እኔ የሚል የለም
ብቻ ቸኩሏል ስቃዩዋን ለማየት ግን ንግግሩ ውስጥ መቸኮሉ አያሳብቅም
"ጥሩ ሂጂ ስትዘጋጁ እደሩ ቻው በይ እህቴ"
♦️♦️♦️በሌላ ትእይንት♦️♦️♦️
"በይ እህቴ ዛሬ በቀልሽን ተወጥተሻል አደለ ኬኩን ብይው"
ተቁለጨለጨ ፍቅሩ ናት በዘመኑ ከሷ ውጪ አፍቅሮ አያውቅም ግን በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ እህቱ ናት ደግሞ የመፈጠር እድል ቢያገኝ የመጀመሪያ ፍላጎቱ የኒያ ስጋ ዘመድ አለመሆን ነው
ግን ምን ያደርጋል እህቱ ናት ምናልባት ከደማቸው ይሆናል ገግሞ ማፍቀር እሷም ከናፍቆት ውጪ ለምኔ ናት
"ያለሱ አልችልም አዝናለሁ" አይኖቿ በእንባ ተሞሉ
ሮቤል ራሱ አይኑ እንባ ሞላ በፊት አልበላ ስትለው የሚዘፍንላትን ቀጠለ ምናልባት እንኳን ብትበላ ብሎ ነበረ
ግንኮ ደስ ብሎታል ከአመታት ቡሀላ ራሱ ያለሱ አልበላም እያለች ነው እድለኛ መሆኑን አስቦ በዛ ተስረቅራቂ ድምፁ ቀጠለ
"በዛ በበጋ
በዛ በሙቀት የሚስቅ ጠፍቶ በፍለጋ
መሸበትና ሰው ቤት ገባ
ኒያዬን አያት ተከናንባ
አለቀሰች አላቀሳት
አብረው ጠፉ በለሊቱ
ደሞ ደሞ አልበላም አለች
ሆዷ እየሞላ ለመጉረስም ሲሞክሩ
እንቢ አለችው የሱ ፍቅሩ
አዘነና ሆዱ ባባ
አለቀሰ የድካም እንባ"
እሱ ከዘፈነለት ሰው በላይ የድካም እንባ የተሰማት እሷ ነበረች እያንዳንዱ ንግግራቸው በዜማ ነበረ ምክንያቱም በጣም የሚያምር ድምፅ አለው
እሷ ደሞ ገጣሚ ናት ትገጥምለታለች እሱ ያቀነቅናል ድምፁ ግን ረፍት ነበረው
"ናፍቆቴ"😭 በድካም ያወጣችው ድምፅ ነው
"እባክሽ ኒያ ብይ" በልምምጥ አይን እያያት ነበረ
እሷ ግን ተናደደች በቃ ማንም ፍቅሯን አይተካም የሚያዜምላት እሱ ነው የሚለምናት እሱ ነው የሚያባብላት እሱ ነው
ሌላ ሰው እሱን አይተካም ግን አሁን የአባባ ቃል አለ አስጠንቅቀዋታል በዙሪያዋ እንደሚኖሩ ስለምታውቅ በጩኧት
"አባባ መላ በሉት ልገድለው ነው" አለች
ረጋ ብለው አሉ ከነ ግርማ ሞገሳቸው ከነ ለዛቸው በሰከነ ድምፅ መለሱላት ንግግራቸው ብቻ የሚያረጋጋ ነው
"ምን አደረገሽ"
ንዴቷ ጠፍቶ ሆድ ይብሳት ጀመር ግን የመፎከር አባዜዋ ሊለቃት አልቻለም
"አባባ ይሙት እገለዋለው ናፍቆቴን ለመምሰል እየሞከረ ነዋ"
ትንሽ ቆጣ አሉ
"ንክች ብታረጊው ልዑል ህይወት ላይ ፈረጂ"
በቃ ደከማት ደክሟችሁ ያውቃል ሰባት የብቸኝነት አመታት አደከሟት ደሞ ሲደርስ የበለጠ ይደክማል ልክ በ11ኛው ሰአት
የብዙ አመት ጥበቃችን ይደክማል አስሩ ሰአታት ተረስተው አንድ ሰአት መታገስ ያቅታል
"ኡፍፍፍ እሺ መቼ ነው ማገኘው"
"ጦርነቱ ሲያበቃ"
"የምን ጦርነት"
"ሀማን ያቆን ለመግደል እየተዘጋጀች ነው በለሊት ትመጣለች"
የቀራት ወንድሟ ሲጠራ ነዘራት ከመቀመጫዋ ተነሳች ኧረ ጎራው ሽለላ መድፍ ቅበላ ጋሻ መከታ ጦር ውርወራ ነው የቀራት
"ምን ማለት ነው እኔ ቀድሜ አንጀቷን ነው ምዘረግፈው"
እሳቸው እንደሷ ሞኝ አይደሉም አንዳንድ በጉልበት የማናሸንፋቸው ነገሮች አሉ ለዛ ደሞ ዘዴ ያስፈልጋል
"አደንዛዡ ጭስ አለሽ አደለ"
ታውቃለች እሳቸው ከሷ የተሻለ ያስባሉ ስለዚህ ተረጋጋች እና መልስ ሰጠች
"አዎ"
"በቃ እናንተ ኦክስጅን አርጉና ሲመጡ ነግርሻለሁ ዝግትግት አርገሽ አጭሽው ለ6 ሰአት ያህል ራሳቸውን አያቁም"
"ሁለት ነው ያለው እኮ"
"እኔ ትንሽ ረዳሻለሁ"
"ማለት እኔ ያለ ኦክስጅን ልቀመጥ እቃዣለሁ እኮ"
"ችግር የለም ለሁለቱ አስረጃቸው ከዛ ያስሯቸዋል ስትነቂ አትቸገሪም"
"እሺ"
"ያቆ ሮቤል"
"አቤት"
"አሁን ምን እናረጋለን መሰላችሁ"
ብላ አባቷ ያሏትን ተረከችላቸው እነሱም ተዘገጃጁ በርግጥ ሮቤል እነ ሀማን እስከሚመጡበት ሰአት ድረስ እየቀባጠረች መስሎት ነበረ
ሌሊት ወደ7 ሰአት ገደማ ሀማንና ጭፍራዎቿ ቤቱን ከበቡት ከገመተችው በላይ ብዙ መሆናቸው ሁሉንም አስደንግጧል ወደ አስር የሚጠጉ ሰዎች ወደቤታቸው ገቡ እነ ያቆ ሀሳባቸውን ትተው ተስፋ ቆርጠዋል ሶስቱ ወዳሉበት ክፍል ተሰብስበው ገብተው ዙሪያቸውን ሽጉጥ ደቀኑባቸው