የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጠ፡፡
፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ
1. አንድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ላይ የቀረበባቸው የዲሲፕሊን ክስ የክስ ምክንያት ያለው በመሆኑ መልስ እንዲሰጡበት፤
2. ሁለት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች የቀረበበት የዲሲፕሊን ክስ ተጨማሪ ማጣሪያ ተደርጎበት በድጋሚ ለጉባኤ እንዲቀርብ፤
3. በሰባት የተለያዩ መዝገቦች የክስ ሂደታቸው ሲታይ የነበሩ ስምንት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛች የቀረበባቸው የዲሲፕሊን ክስ አቤቱታዎች ዳኞቹን የማያስጠይቁ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረጉ፤
4. በሌላ በኩል ጉባኤው የአርባ ሰባት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ሬጅስትራሮች ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡
የሬጅስትራሮቹ ሹመት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን የሰው ሃይል እጥረት ለማቃላልና ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ
rel='nofollow'>Http://t.me/lawabelethio