ለፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል
*****
የፍትህ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለተቋሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ እንዳሉት እንደሀገር የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ከነዚህ ስራዎች አንዱ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያገለግል ወጥ ፣አስተማማኝና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስርኣት ለመዘርጋት ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አውስተዋል፡፡
የዲጂታል ስርኣት በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ አንስተው ከፍትሕ አንፃር ወንጀልን ለመከላከል፣ወንጀል ከተፈፀመ በኃላ አጥፊዎችን ለመለየት ፣ሀሰተኛ ምስክርነትን ለመከላከል እና ሀቀኛ ምስክሮችን ለመለየት፣ በተደጋጋሚ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ለመለየት እንዲሁም የማረምና ማነፅ ተግባራትን ለማከናወን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ፍትሕ ሚኒስቴርን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው፤የዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዋና ዳይሬክተርና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮዳሔ ዘ-ሚካኤል በበኩላቸው ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ በፍትሕ ተቋማት መካከል ያለውን የመረጃ ልውውጥ ቀላል፣ቀልጣፋና ታዓማኒ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የስልጠና መድረኩ በዛሬ ውሎው ከቤት እስከ መስሪያ ቤት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጥኖች እና ወቅታዊ ውጤቶች፣የብሄራዊ መታወቂያ የፖሊስ እና ስትራቴጂ መሰረት፣ የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ላይ ያተኮረ ነበር፡፡👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ.
Telegram
https://t.me/lawabelethio