የመ/ቁ.16648
ታህሣስ 20 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
4. ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ
5. ወ/ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን
መልስ ሰጭዎች፡- እነ አቶ አንለይ ያየህ /27 ሰዎች/
ስለ ስራ ክርክር- የይርጋ ጊዜና የዕዳ ጥያቄ ቅድሚያ- የመብት ጥያቄ ስለሚቀርብበት የጊዜ አቆጣጠር - የይርጋ ጊዜ መቋረጥ - የይርጋ መብትን ስለመተው - ኃላፊነት የተሰጠው ባለስልጣን ስላለው ስልጣን - የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 162፣ 163፣ 164፣ 165፣ 166 (በጉዳዩ የተሰጠው የህግ ትርጉም የአዋጅ ቁ.42/85ን በመሻር በወጣው አዋጅ ቁ.377/96 ድንጋጌዎችም ተፈፃሚነት አለው)
መ/ሰጭዎች በጌዶ፣ነቀምት እና ጊምቢ ባከናወነው የትራንስሚሽን መስመር መዘርጋት ስራ ለተሳተፉት ሌሎች ሰራተኞች አመልካች መጋቢት 15 ቀን 1992 ዓ.ም የሰጠው የሁለት ዕርከን ጭማሪ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ነሐሴ 15 ቀን 1993 ዓ.ም ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ባቀረቡት ክስ ክሱ በይርጋ ሊታገድ ይገባዋል በማለት አመልካች ያቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ቦርድ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ውሳኔ በመስጠቱና ውሳኔውም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመጽናቱ የቀረበ አቤቱታ፡፡
ውሳኔ፡- የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዩ ወሳኝ ቦርድ የሰጠውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያጸናው ውሳኔ ተሽሯል፡፡
1. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162 /3/ መሰረት የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የሌሎች ክፍያዎች ጥያቄ ሊጠየቅ ይገባው ነበር ከሚሰኝበት ጊዜ ጀምሮ የስራ ውሉ ተቋርጦ ቢሆን እንኳን ይህን ከግምት ሳያስገባ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል፡፡
2. የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ጥያቄ በተተኪዎቻቸው ወይም በወራሾቻቸው በሚቀርብበት ጊዜ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/3/ በተደረጉ የይርጋ ድንጋጌዎች ይመራል፡፡
3. የሰራተኛው ወይም የአሰሪው ተተኪዎች ወይም ወራሾች የሰራተኛውን ወይም የአሰሪውን ሳይሆን የራሳቸውን መብት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት ጥያቄ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 162/3/ እና 162/4/ በተደነገጉት ሳይሆን በአንቀጽ 162/1/ በተደነገገው የይርጋ ድንጋጌ ይመራል፡፡
4. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው ክሱ በአዋጅ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን በተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በፍርድ ቤቶች በተቋቋሙ የስራ ክርክር ችሎቶች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡
5. ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ባልተሰጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ወይም በስራ ክርክር ችሎት የቀረበ ክስ በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/1/ መሰረት የይርጋ ጊዜን መቆጠር አያቋርጥም፡፡
6. በአዋጅ ቁ.42/85 /377/96/ አንቀጽ 164/2/ መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚቋረጠው አቤቱታው የቀረበው ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበ እንደሆን ብቻ ነው፡፡
7. ለአሰሪ የቀረበ አቤቱታ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 164(2) መሰረት የይርጋ ጊዜ መቆጠርን አያቋርጥም፡፡
8. በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ከፍትሐ-ብሄር ህግ ቁጥር 1793 ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት፡፡
9. ሰራተኛ ወይም አሰሪ በአዋጅ ቁ.42/85 (377/96) አንቀጽ 166(1) ለመጠቀም በድንጋጌው የተመለከቱት ሁኔታዎች መከሰታቸውን እና ክሱ በይርጋ የሚታገድበት ከመድረሱ በፊት ያልቀረበው በድንጋጌው ከተመለከቱት ሁኔዎች ቢያንስ በአንዱ መከሰት ምክንያት መሆኑን በማስረጃ ማረጋገጥ አለበት፡፡