የግዕዝ ቋንቋ መማርያ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ጣልያን ውስጥ ትልቅ የግዕዝ መማርያ ት/ቤት አለ ኢትዮ ውስጥስ ?
በቴሌግራም ለመማር
@lesangeez128

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ይሄው ቻናሉ ለመመዝገብ @ASRATEGABRIEL




ግዕዝን በልዩ ሁኔታ ለማስተማር ዝግጅታችንን ጨርሰናል መመዝገብያ ዋጋ 75 ብር አሁን ተመዝጋቢዎችን እየጠበቅን ነው
ለመመዝገብ @asrategabriel


ለ አስተያየት @asrategabriel


#ልሳነ_ግዕዝ (የግዕዝ ቋንቋ)
#መግቢያ
ቋንቋ የመግባቢያ ዘዴ ከመሆኑ ባሻገር በጽሐፍም ደረጃ አንድን ማኀበረሰብ ከሌላው ጋር ሊያግባባ፣ ሊያዛምድና ሊያስተሳስር የሚችል መሳሪያ ነው ። በዓለም ላይ በሺህ የሚቆጠሩ ቋንቋዎች መኖራቸው ይታወቃል ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የግዕዝ ቋንቋ ነው ። #ግዕዝ የሚለው ቃል የተገኘው #አግዐዘ ከተሰኘው ግስ ሲሆን የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ። እነርሱም መጀመሪያ ፣ የቋንቋ ስም ፣ የፊደል ስም ፣ የንባብ ስም ፣ የዜማ አይነት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ቋንቋው #የአግዓዝያን ቋንቋ ነው ። #አግዓዝያን ማለት የሚያጉዙና የሚጓዙ ተሰደው ፣ ተጉዘው የመጡ ስደተኞች ፣ ባለብዙ ጓዞች በማለት ከሌላ አገር የመጡ መሆናቸውን ይገልጻል። አንድም #አግአዝያን ማለት ነጻ አውጪዎች ከመገዛትም ነጻ የሆኑ ሕዝቦች ማለት ነው ። እነዚህ የሴም ወገኖች ነገደ ዮቅጣን ራሳቸውን አግዓዚ ብለው የሰየሙ ክፍሎች ከደቡብ ዐረቢያ ግዕዝ ከተባለ አካባቢ ተነስተው ዛሬ በኢትዮጵያ ትግራይ ፡ትግረ በተባለው ስፍራ እንደሰፈሩ የታሪክ ድርሳናት ይነግሩናል። #አግዓዝያን የኩሽን መንግስት በጦርነት ድል ነስተው በነገሱ ጊዜ በነገዳቸው ስም ግዕዝ ቋንቋቸው አብሮ ነግሷል ። የመንግስታቸው የስራ ቋንቋም እንዲሆን አድርገውታል ።ከላይ እንደተጠቀሰው ነገደ ዮቅጣን ራሳቸውን #አግዓዝያን ብለው ጠሩት ። ይህንንም ያሉበት ም/ት ለኩሽ መንግስት ከማስገዛት ነጻ መውጣት እና በነፃነት የሚኖሩ ወገኖች መሆን ስለፈለጉ ራሳቸውን #አግዓዚ በማለት ሰይመዋል ። ነገደ ዮቅጣን ፊደልንና አኀዝን በመቅረጽ፣ ሥነጽሑፍንና ሥነጥበብን በማስፋፋት እንዲሁም ሕገመንግስት አርቅቀው ሀገሪቱን ይመሩ እንደነበር በድንጋዮች ፣በሳንቲሞችና ብራናዎች ላይ የተጻፋ ጽሑፎች ምስክሮች ናቸው ።የአክሱም መንግስትም የግዕዝ ቋንቋን የሥራ ቋንቋ አድርጎ ይጠቀምበት ነበር ።ኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ሀገር ናት የሚባለው በግዕዝ በርካታ መጻሕፍት ስለሚገኙበት ነው ። ለምሳሌ የዜማ ፣ የቅኔ መድብላት ፣ የፍልስፍና ፣ የነገስታት ዜና መዋዕሎች ፣ የቅዱሳን ገድላት ፣ የታሪክ ድርሳናት ፣ የጥበብ መጻሕፍት ፣ የግዕዝ የትርጓሜ መጻሕፍት ተጠቃሾች ናቸው ። እነዚህ ድርሳናት በአሁን ጊዜ ላይ የተለያዩ የጥናትና የምርምር ስራዎች ሆነዋል። በሀገራችን የግዕዝ ስነፅሁፍ በአክሱም ዘመነ መንግስት እንደተጀመረ የታሪክ ድርሳት ይናገራሉ። #ንጉስ_ኢዛና የተቀበለውን አዲሱን የክርስትና እምነቱን ለማስፋፋት ይረዳው ዘንድ ብዙ መጻሕፍትን ከግሪክ ወደ ግዕዝ እንዲተረጎሙ አድርጓል። በዘመነ አክሱም የግዕዝ ቋንቋ ዓለም አቀፍ እውቅና ከነበረው ከግሪክ ቋንቋ ጋር ተጓዳኝ ቋንቋ በመሆን አገልግሏል። ለዚህም ማስረጃ የሚሆኑን በአክሱም በሚገኝ የድንጋይ ሰሌዳ ላይ ንጉሱ ኢዛና በ3 ቋንቋዎች በግሪክ፣በሳባና በግዕዝ የፃፋቸው ፅሁፎች ናቸው ። ንጉሱ በ3 ቋንቋ መፃፋ ስለ 3 ነገር ነው ። #በሳቢኛ መፃፉ ጥንታዊ ቋንቋ መሆኑን ለማጠየቅ፣ #በግሪክኛ መዘገቡ በዘመኑ ግሪክ የስልጣኔ መገኛ በመሆኑ ምክንያት ነው ። የግሪክ ስልጣኔ በዘመኑ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ስለነበር መላው ዓለም ይህን ቋንቋ እንደዛሬው እንግሊዝኛ ይፈልገውና ይገለገልበትም ስለነበር ነው ። በግዕዝ መፃፉ ግዕዝ የቤተ መንግስቱም የሕዝቡም መግባቢያ ቋንቋ ስለነበር ነው።


በአዲስ መንፈስ ትምህርታችንን ቀጥለናል ደስ እንዳላቹ ተስፋ አደርጋልው በቅርቡ በቪድዮ የታገዘ ትምህርት እንጀምራለን
#ድጋፍ_ነቀፋ_እርምታ_አስተያየት_ካላቹ
በ 💚💚💚💚💚💚💚💚💚
💚 @Asrategabriel 💚
💚💚💚💚💚💚💚💚💚
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
❤️ @Asrategabriel ❤️
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💛💛💛💛💛💛💛💛💛
💛 @Asrategabriel 💛
💛💛💛💛💛💛💛💛💛
አመሠግናለሁ ፡፡ 💚💛❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_11
#ትውውቅ

ሀ፡ ሰላም ለከ
     (ሰላም ለአንተ ይሁን)
ለ፡ ወሰላም ለከ
     (ሰላም ላንተም)

ሀ፡ መኑ ስምከ?
     (ስምህ ማን ነው?)
ለ፡ ቡሩክ ውእቱ ስምየ።
     (ስሜ ቡሩክ ነው።)

ሀ፡ ወመኑ ስመ አቡከ?
     (የአባትህ ስም ማን ነው?)
ለ፡ ኖላዊ ውእቱ ስመ አቡየ
     (ያባቴ ስም ኖላዊ ነው።)

ሀ፡ እስፍንቱ አዝማኒከ?
     (እድሜህ ስንት ነው?)
ለ፡ እሥራ ወክልኤቱ
     (ሀያ ሁለት)

ሀ፡ እም አይቴ መጻእከ
      (ከየት መጣህ?)
ለ፡ እም አዲስ አበባ
      (ከአዲስ አበባ)

ሀ፡ ግብር እፎ ውእቱ
     (ሥራ እንዴት ነው?)
ለ፡ ሚመ ኢይብል
     (ምንም አይል)

ሀ፡ እሉ አብያፂከ ውእቶሙ
     (እነዚህ ጓደኞችህ ናቸው?)
ለ፡ እወ
     (አዎ)

ሀ፡ አይቴ ብሔሮሙ
     (ሀገራቸው የት ነው?)
ለ፡ ኤርትራ ወእቱ
     (ኤርትራ ነው።)

ሀ፡ አይቴ ውእቱ ቤተ ትምህርትከ
     (ትምህርት ቤትህ የት ነው?)
ለ፡ አድማስ ውእቱ ቤተ ትምህርትየ
     (አድማስ ነው ትምህርት ቤቴ።)

ሀ፡ በል እግዚእ የሀብከ ፀንአቶ ወይከስትለከ
     (በል ጌታ ፅናትን ይስጥህ ይግለፅልህም።)
ለ፡ አሜን
     (ይሁንልኝ /ይደረግልኝ)

ሀ፡ ሠናይ ሶቤ
     (መልካም ጊዜ)
ለ፡ ሠናይ ሶቤ
     (መልካም ጊዜ)

💚 @lesangeez128 💚
💛 @lesangeez128 💛
❤️ @lesangeez128 ❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_10
🤝 #ሰላምታ 🤝


ሀ: እፎ ኀደርከ እኁየ?
(እንዴት አደርክ ወንድሜ)
ለ: እግዚአብሔር ይሴባሕ
(እግዚአብሔር ይመስገን)

ሀ: ትምርት እፎ ውእቱ
(ትምህርት እንዴት ነው)
ለ: ሠናይ ውእቱ
(ጥሩ ነው)

ሀ: ማዕዜ ውእቱ ዘፈጸምክሙ ፈተናክሙ
(መቼ ነው ፈተናችሁን የጨረሳችሁት)
ለ: ዘዮም ወር
(የዛሬ ወር)

ሀ: በጽባሕ አይቴ ሖርከ ኢረክብኩከ
(በማለዳው ያላገኘኹኽ የት ኼደኽ ነው)
ለ: ኀበ ከኒሣ ቤተ ክርስቲያን
(ወደ ቤተ ክርስቲያን)


ሀ: አንሰ በጽባሕ ኀበ ቤተ ምግብ ውእቱ ዘሖርኩ
(እኔስ በማለዳ ወደ ካፌ ነበር የሄድኩ)

ለ: እግዚእ ይባርክ ኩን ትጉህ
(ጌታ ይባርክህ ትጉህ ሁን)

ሀ: ኲሉ ሰብኣ ቤትከ ዳኅና ውእቶሙ
(ሁሉም ቤተሰቦችህ ደህና ናቸው)
ለ: እወ ሎቱ ስብሐት
(አዎ ምስጋና ለሱ ይሁን)

ሀ: በል ሠናይ ምስየት ... ጌሰም ንትራከብ
(በል መልካም ምሽት ነገ እንገናኝ)
ለ: ኦሆ ለኲልነ
(እሺ ለኹላችን)

💚 @lesangeez128 💚
💛 @lesangeez128 💛
❤️ @lesangeez128 ❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_9

🐅 #አስማተ_እንስሳ (የእንሰሳት ስሞች)

ከልብ ➺ ውሻ
ድርኒ ➺ ድመት
አንጼዋ ➺ አይጥ
በግዕ ➺ በግ

ብዕር ➺ በሬ
ዖፍ ➺ ወፍ
አባግዕ ➺ በጎች
አድግ ➺ አህያ

በቅል ➺ በቅሎ
ሶር ➺ ላም
ሔለይ ➺ ዔሊ
አካሂ ➺ ጥጃ

አፍርኅት ➺ ጫጩት
ቴፈን ➺ ወይፈን
ሐለሰትዮ ➺ ጦጣ

ንህብ ➺ ንብ
ሣሬት ➺ ሸረሪት
ቃሕም ➺ ጉንዳን

ዐንበሪ ➺ ትልቅ ዓሣ
ሰገኖ ➺ ሰጎን
መንተሌ ➺ ጥንቸል

💚 @lesangeez128 💚
💛 @lesangeez128 💛
❤️ @lesangeez128 ❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_8
#አካለ_ሰብእ ( የሰውነት ክፍሎች )

ስእርት ➺ ጸጉር
ገጽ ➺ ፊት
ዐይን ➺ ዐይን
ፍጽም ➺ ግንባር

አንፍ ➺ አፍንጫ
ልሳን ➺ ምላስ
አፍ ➺ አፍ
አስናን ➺ ጥርስ

ከንፈር ➺ ከንፈር
መልታሕት ➺ ጉንጭ
እዝን ➺ ጆሮ
እድ ➺ እጅ
ጸንቢል ➺ ቅንድብ
ሕልቅ ➺ አገጭ
ሕንብርት ➺ እንብርት
ከርስ ➺ ሆድ

ጥብ ➺ ጡት
ጽፍር ➺ ጥፍር
ገቦ ➺ ጎን
መንበር ➺ መቀመጫ

ብርክ ➺ ጉልበት
ክሣድ ➺ አንገት
መጉረጽ ➺ ቁርጭምጭሚት
እግር ➺ እግር

💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_7
#አስማተ_ጊዜ (የጊዜ ስሞች)

፩. ዮም ➜ ዛሬ
፪. ትማልም ➜ ትላንት
፫. ጌሰም ➜ ነገ

፬. ናሁ ➜ አሁን
፭. ይእዜ ➜ ዛሬ
፮. ድሕረ ጌሠም ➜ ከነገ በኋላ
፯. ቅድመ ትማልም ➜ ከትላንት በፊት

፰. ሳኒታ ➜ ማግስት
፱. ጥንት ➜ ዱሮ
፲. ዘዮም ዓመት ➜ የዛሬ ዓመት

፲፩. ከመ ዮም ➜ እንደ ዛሬ
፲፪. ሣምን ➜ ሣምንት

፲፫. ወርኅ ➜ ወር / ጨረቃ
፲፬. መዓልት = ቀን
፲፭. ሌሊት = ማታ

💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_6
#ሞክሼ_ፊደላት

ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።

በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።

እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።

ሀ ➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል።

ሐ ➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።

ኀ ➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

አ ➺ አልፋው "አ" ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ዐ ➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።

ሠ ➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።

ሰ ➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።

ጸ ➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።

ፀ ➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።

✅ እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ ፦
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ
ሰአለ = ለመነ
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ

💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_5
#የግእዝ_ፊደላት

የግእዝ ፊደላት ከሌሎች ቋንቋዎች ፊደል የሚለየው ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ትርጉም ስላላቸው ነው።
ለምሳሌ፦


ሀ - ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡
- ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም።

ለ - ማለት የእኛን ሥጋ ለበሰ።
- ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚአነ።

ሐ - ማለት ስለእኛ ታሞ ሞተ።
- ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ።

መ - ማለት የእግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው፡፡
- ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር።

ሠ - ማለት ከድንግል በሥጋ ተወለደ(ተገለጠ)
- ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል፡፡

ረ - ማለት በጥበቡ ፤ ሰማይና ምድር ረጋ።
- ብሂል ረግዓ ሰማይ ወምድር፡፡

ሰ - ማለት እንደእኛ ሰው ሆነ።
- ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ።

ቀ - ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበረ።
- ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ።

በ - ማለት ለዓለም ሁሉ ቤዛነት በትሕትናው ወረደ፡፡
- ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኩሉ ዓለም።

ተ - ማለት ፍፁም ሰው ሆነ።
- ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ።

ኀ - ማለት ራሱን (ባህሪውን )ሰወረ (ሸሸገ)
- ብሂል ኀብአ ርእሶ።

ነ - ማለት ደዌያችንን ያዘል ሕማማችንንም ተሸከመልን።
- ብሂል ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ።

አ - ማለት እግዚአብሔርን ፈፅሞ አመሰግነዋለሁ።
- ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር።

ከ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው፡፡
- ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር።

ወ - ማለት ከሰማያት ወረደ።
- ብሂል ወረደ እምሰማያት።

ዐ - ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
- ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር።

ዘ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን የሚይዝ (የሚገዛ ነው)።
- ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር።

የ - ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
- ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ።

ደ - ማለት መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አንድ አደረገ።
- ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ፡፡

ገ - ማለት ምድርና ሰማያትን የፈጠረ ነው፡፡
- ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር።

ጠ - ማለት እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡
- ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር።

ጰ - ማለት ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡
- ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፡፡

ጸ - ማለት እግዚአብሔር ጸጋና እውነት ነው።
- ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

ፀ - ማለት እግዚአብሔር የእውነት ፀሐይ ነው።
- ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር፡፡

ፈ - ማለት በጥበቡ ዓለምን ፈጠረ።
- ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ።

ፐ - ማለት የእግዚአብሔር ስሙ ፓፓኤል ነው፡፡
- ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር።
@መሠረተ ግዕዝ
💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_4
#ግሥና_የግሥ_ምንነት
#ግሥ
ግሥ ገሠሠ፣ ዳሠሠ ካለው ዐቢይ አንቀጽ ይወጣል ። ትርጉሙም ልዩ ልዩ ርባታዊ ቃላትን በየፈርጃቸው መግለጽን ማብራራትን ይመለከታል ። ግስ ከካዕብና ሳልስ በስተቀር በቀሩት #በ፭ቱ የኆኄ ቤቶች ይነሳል። ለምሳሌ ከፈለ፣ባረከ፣ ሤመ ፣ ክህለ፣ቆመ።
#አዕማደ_ግሥ
አዕማድ የዐምድ ብዙ ቁጥር ሲሆን በቁሙ ዋና ፣ ቀዋሚ፣ ተሸካሚ ... የሚል ትርጉም አለው ። አዕማድ የሚባሉት #፭ ናቸው ። እነሱም ፦ አድራጊ፣ተደራጊ፣አስደራጊ፣ተደራራጊ፣አደራራጊ ናቸው ።ለምሳሌ ፦ ቀተለ/ገደለ/ #አድራጊ ፣ ተቀትለ/ተገደለ/ #ተደራጊ ፣አቅተለ/አስገደለ/ #አስደራጊ ፣ ተቃተለ/ተጋደለ/ #ተደራራጊ ፣ አስተቃተለ /አጋደለ/ #አደራራጊ
#አርእስተ_ግሥ
አርእስተ ግሥን በተመለከተ የግሥ አርእስ ቀተለ ብቻ ነው የሚሉ አሉ። ልሎች ክፍሎች ደግሞ ቀተለ፣ ባረከ፣ዴገነ፣ኖለወ፣ ደንገፀ፣ማህረከ በማለት የግሥ አርእስት #7 ናቸው የሚሉ ክፍሎች አሉ።
#ፀዋትወ_ግሥ
ፀዋትወ የቋንቋ ሰፊ ሕግ ነው ። አንድ የቋንቋ ተማሪ ፀዋትወ ግሥን ለየ ማለት ስለ ቋንቋው በቂ ግንዛቤ አለው ብሎ ማለት ይቻላል። ፀዋትወ የተባሉት #4 ናቸው ። እነሱም ፦ ሀ እና አ አንድ፣ ወ ሁለት ፣የ ሶስት ፣ ሀ፡አ፡ወ፡የ የሌሉበት ማንኛውም ግሥ ሲባል በመነሻ ፣ በመሀልና በመጨረሻ ሊሆን ይችላል። ፀዋትወ ግሥን ለማወቅ በቅድሚያ አርእስተ ግሥ ፣ ሠራዊተ ግሥ መሠረት ናቸው። ፀዋትወ ግሥ ሲጠና መጀመሪያ የመመደብ ሥራ ነው የሚካሄደው ይህም ሲባል ይህ ግሥ የማን ቤት ነው ከየት ይመደባል የመሳሰለው ሁሉ።
#ገዳፍያነ_ዘመድ
ገዳፍያነ ዘመድ የኒባሉት ቤታቸውን ለቀው የኒሄዱ ናቸው ።እነዚህም "ወ" ና "የ" ናቸው ። ወ በመነሻ በመድረሻ በመሐል ቤቱን ለቆ ወደ ሌላ ቤት ይሄዳል ። ለምሳሌ ወለደ ብሎ ይወልድ ይላል ።
#ወሳክያነ_ባዕድ
እነዚህ ደሞ ከግሥ ያልነበረ ቀለምን የሚጨምሩ ናቸው ለምሳሌ ፦ ቆመ ብሎ ይቀውም ፣ ኤለ ብሎ የአይል ይላል።
#ሠጋርያን
ሠጋርያን ማለት መሸጋገሪያ ማለት ነው ። ሰጋርያን የተባሉ ቤታቸውን ለቀው ያለቤታቸው የሚገኙ በመሆናቸው ነው ። እነዚህም ወ ና የ ናቸው ።
#ውላጤ_ግዕዝ
ውላጤ ግዕዝ የተባሉ(ሀ፡አ፡ወ፡የ) በመነሻ በመድረሻ በመሀል በደጊመ ቃል የሚገኙባቸው ግሦች ናቸው ።እነዚህም በመነሻና በመድረሻ እንዲሁም በመሀከላቸው የተገኘባቸው ግሶች ራብዑን ግዕዝ ፡ ግዕዙን ራብዕ ሳድስ ያደርጋሉ።
#አላህላህያን
አላህላህያን የተባሉ ፫ ናቸው ። እነርሱም ሀ፣ አ፣ በ ናቸው ።እነዚህ ቀለማት በመካከል የተገኙበት ግሥ አይጠብቅም ።
#ወኀጥያን
ወኀጥያን የሚባሉት ፊደላት (አ፡ቀ፡ከ፡ገ) ናቸው ። ወኀጥያን በአንስቱ ቅርብ አነ፣አንተ፡አንቲ፡አንትሙ፡አንትን በረባ ጊዜ ቀለማትን ውጠውና አጥብቀው የሚያስቀሩ ናቸው
❤️ @lesangeez128❤️
💛 @lesangeez128💛
💚 @lesangeez128💚


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_3
#መራሕያን_ገቢር_ተገብሮ
መራሕያን(ተውላጠ ስሞች) ማለት የሚመሩ ፣ መሪዎች ፣ ፊት አውራሪዎች ማለት ነው ። የግዕዝ ቋንቋ መሪዎች ፲ (10) ናቸው ። እነርሱም ፦ (አነ ፣አንተ፣ አንቲ፣ ውእቱ፣ይእቲ፣ንሕነ፣አንትሙ፣አንትን፣ ውእቶሙ ፣ውእቶን) በመባል ይታወቃሉ።
#መደብ #መራሕያን #ትርጉም
፩ አነ እኔ
፪ አንተ አንተ
፪ አንቲ አንቺ
፫ ውእቱ እሱ
፫ ይእቲ እሷ
፩ ንሕነ እኛ
፪ አንትሙ እናንተ (ተባዕት)
፪ አንትን እናንተ (አንስት)
፫ ውእቶሙ እነርሱ (ተባእት)
፫ ውእቶን እነርሱ (አንስት)
#ገቢር_ተግብሮ
#ገቢር ማለት አድራጊ ወይንም ወራሽ ማለት ሲሆን #ተገብሮ ደግሞ ተደራጊ ወይም ተወራሽ ማለት ነው ። በስም ጊዜ ባለቤትና ተሳቢ ብሎ መግለጽ ይቻላል። በግሥ ጊዜ ደግሞ ተሳቢ ብሎ መግለፅ ይቻላል። ከዚህም አንፃር ፦ አድራጊ፣አስደራጊ፣አደራራጊ፣ገቢር ናቸው ። ተደራራጊና ተደራጊ ደግሞ ተገብ ናቸው ። ምሳሌ፦
#አድራጊ ፦ አይሁድ ቀተሉ አምላከ (አይሁድ አምላክን ገደሉ ) #አስደራጊ ፦ ሳዖል አቅተለ ዳዊትሀ ጎልያድሀ (ሳዖል ዳዊትን ጎልያድን አስገደለ) #አደራራጊ ፦ ዳዊት አስተራወጸ አሳሄልሀ ምሰለ ፈረስ (ዳዊት አሳሄልን ከፈረስ ጋር አሯሯጠ) ። ተደራጊና ተደራራጊ ያለ #ተ ፊደል አይነገሩም ። ለምሳሌ ፦ አምላክ ተሰብሐ (አምላክ ተመሰገነ) ። ተደራራጊ ተገብሮ ነው የሚጠላና የሚፈቀር በውስጡ አለው ። ምሳሌ፦ በተጠላ አምላክ ተሳነነ ምስለ አይሁድ (አምላክ ከአይሁድ ጋር ተጣላ ) ። #ገቢር የሚያናግሩ ቀለማት ፫ ናቸው ። እነርሱ ፣ ግዕዝ ፣ ኅምስ ፣ ሳብዕ ናቸው ። #ተገብሮ የሚያናግሩ ቀለማት ፫ ናቸው ። እነዚህም ካዕብ ፣ ሣልስ ፣ ሳድስ ናቸው ፤ ራብዕ ግን ተፈቃቃሪ ነው ለሁሉ ይሆናል ። ይኸውም ሲባል ሳድሱን ግዕዝ ይወርሰዋል ፡ ሣልሱን ኀምስ ይወርሰዋል ፡ ሣልሱን ኃምስ ይወርሰዋል ፡ ካዕቡን ሳብዕ ይወርሰዋል ፡ማለታችን ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጊዜ ይህ ሕግ ሲጣስ ይስተዋላል። መጨረሻው ሳድስ የሆነ ቀለም #ተገብሮ ይሆናል ። ምሳሌ ፦ አንበሳ ፣ ደብተራ ፣ ደመና ፣ ሐራ የመሰለው ሁሉ።
💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_2
#አኀዝ / #የግዕዝ_ቁጥሮች
#አኀዝ ማለት መጀመሪያ ፣ መቋሚያ ፣ መያዥ፣ ዋስ ፣ ቁጥር ማለት ነው ። ከዚህ በታች የግዕዝ ቁጥሮችን በፊደልና ትርጉማቸውን እናያለን
#አኀዝ #ፊደል #ትርጉም
፩ አሐድ፡ዱ አንድ፡ዱ
፪ ክልኤት፡ቱ ሁለት፡ቱ
፫ ሠለስት፡ቱ ሦስት
፬ አርባዕት፡ቱ አራት
፭ ኀምስት፡ቱ ዐምስት
፮ ስድስት፡ቱ ስድስት
፯ ሰብዐት፡ቱ ሰባት
፰ ስምንት፡ቱ ስምንት
፱ ተስዐት፡ቱ ዘጠኝ
፲ ዐስርት፡ቱ አስር
፳ ዕስራ ሀያ
፴ ሠላሳ ሠላሳ
፵ አርብዐ አርባ
፶ ኀምሳ ዐምሳ
፷ ስድሳ(ስሳ) ስልሳ
፸ ሰብዓ ሰባ
፹ ሰማንያ ሰማኒያ
፺ ተስዓ ዘጠና
፻ ምእት መቶ
፲፻ አስር ምእት አንድ ሺህ
፳፻ ዕስራ ምእት ሁለት ሺህ
፴፻ ሠላሳ ምእት ሶስት ሺህ
፵፻ አርብዓ ምእት አራት ሺህ
፶፻ ኀምሳ ምእት አምስት ሺህ
፼ እልፍ ዐስር ሺህ
፲፼ ዐስርቱ እልፍ አእላፍ መቶ ሺህ
💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128❤️


#ልሳነ_ግዕዝ
#ክፍል_1
#ፊደል
ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ፊደልና አኀዝ ያላት ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ናት ። ፊደል ማለት የነገር ፣ የቃል ምልክት፣ አምሳል መግለጫ ወይም ማስታወቂያ ማለት ነው ። የግዕዝ ፊደላት ቅጥያዎች ከካዕብ እስከ ሳብዕ ድረስ ስድስት ኆኄዎች ናቸው ።ለምሳሌ ፦ ኡ፣ኢ፣አ፣ኤ፣እ፣ኦ(ኡ=ካዕብ ኢ=ሣልስ ኣ=ራብዕ ኤ=ኃምስ እ=ሳድስ ኦ=ሳብዕ) የ(ጰ) ና የ(ፐ) ፊደላት ተፅዕኖ የመጣው በአባ ሰላማ ፍሬምናጦስ አማካኝነት መጻሕፍት ከጽርእ ወደ ግዕዝ ሲተረጎሙ ተጨምረዋል ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትውፊት አሌፋት ፊደል መገኛ መሰረት የሚከተለውን ይተርካል ። ጻድቁ አቤል በወንድሙ ተገድሎ ከሞተ በኀላ የሰው ልጆች ደመ አቤል ያጥፍአነ ፣ደመ አቤል ያስጥመነ እያሉ ሲምሉ እግዚአብሔር በሩቅ ብእሲ ደም መማል እንደማይገባ በ3ኛው ትውልድ በሄኖስ አማካኝነት 22ቱን ፊደላት በ22ቱ ሥነፍጥረታት አምሳል በጸፍጸፈ ሰማይ ቀርጾ እንደሰጠው ይተርካል ።ከ81 መጽሐፍት ውስጥ መጽሐፈ ሔኖክና መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ አሌፋት ፊደል በሰፊው ያትታል ።የግዕዝ መሰረታዊ ፊደሎች 26 ሲሆኑ እያንዳንዳቸውም 7 የጽሑፍ ሆሄ አላቸው ። ስለዚህ 26ቱ ፊደሎች በሰባት ቅርፆቻቸው ሲባዙ 182 ይሆናሉ ። በተጨማሪም 4 ዲቃላ ፊደሎች (ጎ፣ኈ፣ኰ፣ቔ) እነዚህም እያንዳንዳቸው 5 ሆሄያት በአንድነት 20 ይሆናሉ። የግዕዝ ፊደላት ቅደም ተርታ የሚጀምረው አ፣በ፡ገ፡ደ... በማለት ሲሆን የአማርኛ ደግሞ ሀ፣ለ፡ሐ፡መ... በማለት ነው ። በመሆኑም የሁለቱን ቋንቋዎች ፊደል ተርታ በጥንቃቄ በመለየት መጠቀም ያስፈልጋል።
💚 @lesangeez128💚
💛 @lesangeez128💛
❤️ @lesangeez128 ❤️


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆




መጽሐፈ ፈውስ በpdf መግዛት ምትፈልጉ inbox

20 last posts shown.

1 557

subscribers
Channel statistics