ቶኔቶር


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ፍቅር ነው ዜማችን
ስለፍቅር የተገጠሙ ግጥሞች
የተለያዩ ወጎች
የታላላቅ ሰዎች ምክር
Adadis music/cover
ተከታታይ ልቦለዶች የሚያገኙበት ብቸኛ Channel
@Maneget
@zinashio

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ለ ፕሮፋይ ለሚሆኑ ምርጥ ፒክቸሮኝ ከፈለጉ👇👇
@manetio💥






💫💫💫💫ምኔ ነህ? 🤔

ልጠይቅህ አለሜ ግራ የገባኝን
ልመልስ ፈልጌ ያወዛገበኝን
ልጠይቅህ እና መልስ አግኝለት
ያጨናነቀኝን መፍትሄ አበጅለት
ለኔ አንተ ምንድነህ? እኔስ ላንተ ማነኝ?
ምንስ ይፈጠራል ብታገኝ ብታጣኝ?
መመለሱ ከብዶህ እኔን ከጠየከኝ
መልሽልኝ ብለህ አጥብቀህ ከያዝከኝ
እንግዲ ስማኝ አድምጠኝ ከልብህ
አንተ ካላወከው በቃ እኔ ልንገርህ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሳቅፍህኮ ሱሴ
ወደ ደስታ አለም ትነጉዳለች ነፍሴ
እኔ አንተን ሳገኝህ ሁሉን እፈታለሁ
ያስከፋኝንም ሰው ይቅር እለዋለሁ
ላስጨነቀኝ ነገር መፍትሄ አገኛለሁ
የፈለኩትንም ሁሉን አደርጋለሁ
ካንተጋራ ስሆን ሁሉም ይቀርና ደስተኛ ሆናለሁ
እና የኔ ደስታ አንተ ለኔ ማነህ?
ለምነው ከሰው ሁሉ ለኔ የተለየህ
መልሱን አላውቀውም ለኔ ምን እንደሆንክ
እንደሚመስለኝ ግን ...
አንተ ማለት ለኔ ደስታዬ ብቻ ነህ።

ገጣሚ z የታሜዋ
🔹▫️🔹▫️🔹▫️🔹▫️🔹▫️

ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ👍
ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን❤️

@manetio ፍቅር ነው ዜማችን💐


Mels yalagegnehulet tiyake


ኤርሚ በድንገት ፀባዩ እየተቀያየረ መጣ ከአብርሽ ጋር መታረቃችንን የወደደው አይመስልም ግን እኔ ምንም ነገር ደብቄው አላውቅም ከዛም በቃ በትንሽ ትልቁ ማኩረፍ ጀመረ ይነጫነጫል ስልክ ስደውልለት አያነሳም ደስ ሲለው ነው የሚያነሳልኝ እየራቀኝ መጣ።አንድ ቀን ግራ ገባኝ እየተለማመጥኩ ላወራው ሞከርኩ በድንገት ሲደውል አላየሁትም ነበር መልሼ ደውዬ ሳወራው ለምን ደወልሽ አብርሽ ቢሆን ኖሮ ታነሽለት ነበር አለኝ ባስረዳውም አላምን አለኝ ይቅርታ ብጠይቀውም ከልቡ አልቀበል አለኝ ከነጭራሹ ዘጋኝ ሶስት ቀን ስደውል አያነሳም። በ4ኛው ቀን አነሳና ምን ፈለግሽ አለኝ ኤርሚ ነው😳 እንደዚ ያለኝ ደንግጬ ስልኩን ዘጋሁት በጣም ናፍቆኝ ላወራው ብፈልግም ሲያመነጫጭቀኝ እንባዬ መጣ😢😢😢 እንደምንም ብዬ መልሼ ደወልኩለት ለምንድነው የጠፋኸው ስለው አይመለከትሽም አለኝ እንደውም የኔና ያንቺ ነገር እዚጋ ያበቃል አለኝ ።የደረሰባቹ ታውቁታላቹ ስሜቱን ማበድ እንጂ ምንም አልቀረኝም ምርር ብዬ አለቀስኩ ያኔ ብሞት ደስታዬ ነበር ስልኬን ዘጋሁት ቤተሰብ ክላስ ሁሉነገር አስጠላኝ።ህይወት ጨለማ ሆነችብኝ መፈጠሬን ያኔ ነው የጠላሁት ሁለተኛ የልብ💔💔 ስብራት ታመምኩ። አብርሽም እየደለወ ማውራት ጀመርን እሱ ቁርጥ ያለ ሀሳብ የለውም አንድ ጊዜ ላፈቅርሽ እየሞከርኩ ነው ይለኛል ኤርሚን በማጣቴ ብከፋም ቢያንስ እሱ ላይ ምንም አለማድረጌ የህሊና እረፍት ሰቶኛል። ቀናቶኝ መጉዋዛቸውን ቀጠሉ አብርሽም ቁርጥ ያለ መልስ ነገረኝ ከውስጤ ለማውጣት ሞከርኩ ልረሳው ግን አልቻልኩም። ብዙ ታገልኩ ግን አልሆነም በመጨረሻም ሁሉንም ርግፍ አርጌ ተውኩት ። ህይወቴን ማስተካከል ጀመርኩ ደስታዬን የሚያሳጡ ነገሮችን ከአጠገቤ አርቄአለሁ ወንድ አላፈቅርሽም ስላለኝ መሞት እንደሌለብኝ አወኩ ምክንያቱም የሚኖርልኝ የሚወደኝ ቤተሰብ የምኖርለት አላማ አለኝ ህይወቴን ለፈጣሪ ሰጥቼ አሁን ደስተኛ ሆኛለሁ። ግን እንደዚ እንደነገርኩዋቹ ቀላል አይደለም በጣም ብዙ ስቃዮችን አሳልፌአለሁ ግን ዛሬም አለሁ ችግር ሆኖ የማያልፍ የለም። ምናልባትም ስለህይወት እንድማር ይሆናል። ሁሉንም አይቼዋለሁ ሁሉም ሀላፊ ነው። እኔ በማንም አልፈርድም ሁሉም መሆን ስላለበት ሆነ ተመስገን የዘውትር ንግግሬ ነው ። የሞዴሊንግ ትምህርቴን ተመርቄአለሁ ሌላውን ደሞ እየተማርኩ ነው። ፍቅርን ትታደለዋለህ እንጂ አትታገለውም። እኔ ብዙ ታገልኩ በቃኝም!!! እስክታደል እጠብቃለሁ አላማ ቢስ ሆኜ አልቀርም ። ሁላችንም የኔ ባልናቸው ሰዎች 💔ተጎድተን ይሆናል ግን መሬት ጥለው ቢስቁብንም ተነስተን እንዳዲስ መሄድ እንደምንችል እናሳያቸው ስንቱ ወንድ አላፈቅርሽም ስንቱዋ ሴትስ አላፈቅርህም ብለዋችሁ ይሆን? እንኳንም ሄዱላቹ ምክንያቱም አብረዋቹ ቢቆዩ ህመም ብቻ ናቸው ስለዚህ ልባቹን ጠብቁ በኔ የደረሰ በናንተ አይድረስ ትክክለኛው ሰው በትክክለኛ ሰዓት ይመጣል ጌታ መልካም ነው ህይወት ይቀጥላል።

"በውሸት ተከባ በታጠረች አለም
መታመን ነውንጂ መካድ ብርቅ አይደለም!!!"

ከኔ ታሪክ ቢያንስ አንዲት ሀሳብ ትማሩበታላቹ ብዬ አስባለሁ አመሰግናለሁ ባለታሪኩዋ ሊሊ ነበርኩ ከቡራዩ🙏🙏🙏


🙋‍♀ታሪኩን አዘጋጅቼ ያቀረብኩላቹ ቤቲ ነኝ ቶኔቶር ፍቅር ነው ዜማችን ሳምንት በሌላ ታሪክ እመጣለሁ ሰናይ ምሽት😘😘😘

ሀሳብ አስተያየት ካላቹ
👇👇👇👇👇
@ethiopiawerk ብታደርሱኝ እቀበላለሁ እርሶም የምለው አለኝ ካሉ 👍👍👍👍

ሰናይ ምሽት✨✨✨✨✨✨
💥💥💥@manetio💥💥💥


💥✨💥✨💥✨💥✨
ፍቅርን ይታገሉታል ወይስ ይታደሉታል??

ሊሊ እባላለሁ እኔና አብርሽ ገና በልጅነታችን ነው የተዋወቅነው አብረን ነው ያደግነው። ክፋት በሌለበት ልባችን በልጅነታችን የፍቅርን ምንነት ሳናውቀው በልባችን የተፋቀርነው። እንዳጋጣሚ ሆኖ አብርሽ ከቤተሰቦቹጋር ሌላ ቦታ ሄደ ለ6 ዓመት ሳንገናኝ ቆየን በማንም ሳልተካው ነበር የማፈቅረው ታድያ አንድ ቀን ከ6 ዓመት በሁዋላ መጣ ሳገኘው በጣም ደስ አለኝ ተገናኝተን የድሮአችን እያስታወስን ብዙ አወራን ። እኔ አብርሽ አሁንም የሚያፈቅረኝ ነበር የሚመስለኝ ግን እሱ ሌላ ፍቅረኛ ይዙዋል። ከኔም ጋር እንደማይሆን ነገረኝ። እኔ ከአብርሽ ውጪ ሌላ ወንድ አላውቅም ከማንም በላይ ነው የማፈቅረው ያለሱ መኖር የምችል አይመስለኝም ነበር። ሲነግረኝ ልቤ ተሰበረ ለወራት ታመምኩ።💔💔💔 አብርሽ እውነቱን ነው ብዬ ማመን አቃተኝ ግን እስከዛ ድረስ እንደሚያፈቅረኝ ነበር የማውቀው። አላመንኩትም እባክህ አትተወኝ ብዬ ለመንኩት ምክንያቱም በጣም ነበር የማፈቅረው። ግን አብርሽ ለኔ ፍቅር እንደሌለው ነገረኝ። በብዙ ነገሮች ጠንካራ ሴት ነኝ ሴትነቴን ከምንም በላይ አከብረዋለሁ እወደዋለሁ ። እናም አብርሽን ለመርሳት መሞከር ጀመርኩ ግን ያማል ይበልጥ እንድናፍቀው አደረገኝ ። እሱን ለመርሳት ጣር ውስጥ እያለሁ ኤርሚያስ የሚባል ሰው ተዋወኩ በጣም ጥሩ ልጅ ነው ከማንም በላይ ይረዳኛል ከሱጋ ስሆን ህመሜን እረሳዋለሁ ብቸኝነት አይሰማኝም። ከዛ ኤርሚ እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ ለኔ ያለውን ፍቅር ስለማውቅ እንቢ ማለት ከበደኝ በጣም ጥሩ ሰው ነው። እኔ እሱን ላለማስቀየም ሁሉንም ባደርግም አብርሽን ከውስጤ ማውጣት ግን ከበደኝ። ስለ አብርሽ ሁሉንም ነግሬዋለሁ ለኤርሚ እናም እሱን እንድረሳው እሱም ሁሌም ያበረታኝ ነበር ከኤርሚጋር ደስ የሚል 1 ዓመት አሳለፍን።ከትምህርቴ በተጨማሪ ሞዴሊንግ እማራለሁ የሚያምር ቁመናና መልክ ፈጣሪ ሰቶኛል ደስተኛ መሆንን ጀምሬ ነበር። በመሀል ግን አብርሽ ድጋሜ ወደ ህይወቴ ገባ ከኤርሚ ጋር መሆኔን ሲሰማ ይቅርታ ጠየቀኝና ጓደኛሞች እንድንሆን ጠየቀኝ ለኤርሚ ነግሬው እሺ ሲለኝ ይቅርታ አርጌለት ማውራት ጀመርን
ግን አሁን ደሞ ሌላ ችግር ተፈጠረ ኤርሚ በድንገት......




ሰዎች አላቹ👀 ሊለቀቅ ነው 😊
አሁን ይለቀቅ ወይስ በሰዓቱ? 3:30


❤️ስወድሽ ውደጅኝ

...... ውዴ ...

እኔ አንቺን መውደዴ፤
መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ
ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ፤
ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ
ሰማይ ቤት አትቆምም ነብሴተጠይቃ ትዕዛዝ ተላልፋ፤

ታድያ አንቺን መውደዴ ምን ላይ ነው ጥፋቱ?
ወደድኩሽ ማለቴስ ምንድነው ክፋቱ?

ጠልተሽኝ እንዳይሆን ቁርጡን እንዳላውቀው
እንደምትወጅኝ ነው ውስጥሽ ሚያሳብቀው፤
ታድያ እየተዋደድን አንድ ሆኖ ውስጣችን
ለምን እንራራቅ እንሁን ለብቻችን፤

ስለዚህ ውድዬ......
ባንቺ ፍቅር ጨርቅ ሳልጥል
ወይ ሳታሳብጅኝ
በፍፁም ተማምነን ሳልከዳሽ
ሳትከጂኝ ሳልጎዳሽ ሳትጎጂኝ
መራራቁን ትተን ስወድሽ ውደጂኝ 🌹🌹።

🔸🔸🔸🔸🔸🔹🔸🔸🔸
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
@manetio
😘❤️ ፍቅር ነው ዜማችን🕊


ድሪቶ ነው ልብሴ ብለህ አትራቃት፤
ደሳሳ ነው ቤቴ ብለህ አትንገራት፤
በ ሀምሳ ብር ጃኬት ፏ ብለህ ሂድላት፤
ይሄ ቤት የኔ ነው ብለህ አስከልማት፤
እስክትባንን ድረስ ደህና አርገህ ሸውዳት፤
ሸ........ው..........ዳ...............ት....
ወጣትነት አልፎ እርጅናም ቢመጣ፤
ፊትህ ቢጨማደድ መልክህን ብታጣ፤
መቀመጥ መተኛት ቢሆን ያንተ እጣ፤
እሷኑ ከፈለክ ወደ አንተ እንድትመጣ፤
ወደ ካዝናህ ሄደህ ገንዘብህን አውጣ፤
እንጂማ
በእናትሽ በአባትሽ ቤት ጮማ ሰልችቶሻል፤
ነይ እስቲ ከኔ ዘንድ ልብ ይቀርብልሻል፤
ቪላም አላኖርሽ ጎጆ ይሻልሻል፤
ውበት ተፈጥሮ እንጂ አይደል አርቴፊሻል፤
ሜክ አፑንም ተዪው nature ይሻልሻል......
ብትላት ይህ አስተሳሰብ ለ romance movie ነው ትልሀለች👇👇👇👇👇👇👇👇👇፡፡
https://t.me/joinchat/McsQe-iQF9o4ZDc0


ጓደኛዬን በጣም ነው ማፈቅራት እሷም እንደዛው በፍቅር 3 አመት አብረን ቆይተናል እሷም በጣም ታፈቅረኛለች
በሌላ በኩል ደግሞ የጓደኛዬ እህት ቤዛ ትባላለች በጣም ነው ምወዳት በሂወቴ እንደሷ ደግና ንፁህ ልብ ያለው ሰው አይቼ አላቅም እንደ እህትና ወንድም በጣም ነው የምንቀራረበው ከድሮ ጀምሮ አብረን አንድ አልጋ ላይ ተቃቅፎ መተኛት የለመድነው ነገር ነው እኔ እሷ ወንድሟ ሆነን እሷን መሀል ላይ አቅፈናት እንተኛለን የሁለታችንም ቤተሰቦች በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ የላቸውም አሁን እያደግን ስንመጣ ግን የቤዛ እናት ከኛጋ እንዳትተኛ ይከለክሏት ጀመር አኔም እነሱ ቤት ማደር አቆምኩ ቤዛዬ ዛሬ እንዲህ አፈር ሳይበላት በፊት ሚስጥረኛዬ ነበረች ፍቅር እንኳን ሲይዘኝ መጀመሪያ ለሷ ነበር የነገርኳት እሷም እንድጠይቃት አበረታታቺኝ ጠየኳትና አብረን ሆንን ካሁኗ ጓደኛዬጋ ቤዛ የ12 ኛ ክፍል ፈተናዋን ወስዳ ውጤት እስኪለቀቅ በጣም ጓጉተን ነበረ ልክ የተለቀቀ ቀን ቤዛ እንዳለፈች ልትነግረኝ ለብቻዬ ወደ ተከራየሁበት ቤት መጣች በዛ በሚያባባል ሳቋ እየተፍለቀለቀች እንዳለፈች ስትነግረኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር አቅፊያት ጨፈረኩ ከዛ ግን ለምን እንደልጅነታቺን ተቃቅፈን አንተኛም አለቺኝ ደስ እያለኝ በሩን ዘጋሁና መሬት ላይ ወደተጋደመቺው ፍራሼ ሄደን አረፍ አልን ተቃቅፈን ተኝተን እያወራን ነበር በጨዋታቺን መሀል ህፃን እያለን አንድ ላይ ገላቺንን ስለታጠብነው አነሳን የዛኔኮ እራቁትሽን አይቼሻለሁ እኔምኮ አይቼሀለሁ እየተላፋን እንሳሳቃለን በልፊያቺን መሀል ቤዛን እላይ ላይ ሰፍራብኝ ስትኮረኩረኝ ስሜቴ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሄደ እሷም ዝም እኔም ዝም ብቻ በመሀላቺን ያለው ክፍተት እየጠበበ ሲመጣ ትዝ ይለኛል ከእንቅልፌ የቀሰቀኝ በር ላይ ቆሞ የሚያኳኳው ሰው ነበር ለመነሳት ስሞክር ቤዛ ከጎኔ እራቁቷን ተኝታለች ፈጣሪን በህልሜ እንዲያደርገው ተማፀንኩት ግን አልሆነም አየተርበተበትኩ ወደ በሩጋ ሄድኩ በቀዳዳ ሳይ ፍቅረኛዬ ነች ወደ ፍራሹ ተመልሼ በቁጭ አልኩ ሲሰለቻት እሷም ሄደች
ቤዛን ከተኛቺበት ቀሰቀስኳት ምን እንደተፈጠረ እንድታስረዳኝ ነገርግን እሷም እንደኔው ግራ ገብቷቷል አንሶላው በደም ተጨማልቋል ቤዛ ቀና ብላ አይኔን እንኳን ለማየት አፈረች በዛ ሰሞን እራሴን በጣም ጠላሁት የራሴ መልከስከስ ሳያንስ የዚቺን ምስኪን ልጅ ምስቅልቅሉን አወጣሁት





ይህ በተፈጠረ በ3ኛው ወር ቤዛ እራሷን አጠፋች ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘቺው እኔን ነበር በእጇ የያዘቺውን ወረቀት ሰጥታኝ እየሮጠች ሄደች ምናልባት ወረቀቱን በሰአቱ ከፍቼው ቢሆን ቤዛ ዛሬ በሂወት ትኖር ነበር የሰጠቺኝን ወረቀት ትኩረት ሳልሰጠው ዝም ብዬ ኪሴ ከተትኩት ከሰአታት ቡሀላ ሰፈሩ ሁላ በጩኸት ተናወጠ ቤዛ እራሷን ሰቅላ ሞታ ነበር አላመንኩም ከሰአታት በፊት ሳራ ከፊት ለፊቴ ቆማ ነበርኮ
እናቷ አንድ ያለቻቸውን ሴት ልጅ አጧት ሀዘናቸውን እንዲህ ብዬ ማስረዳት አልቺልም ለነገሩ ያላዘነ ሰው አልነበረም ሁሉም ሰው አይ ልጅ እንዳላት ነበር
የሰልስቱ ቀን ያ የሰጠቺኝ ደብዳቤ ትዝ አለኝ

እንጨርሰዋለን ነገ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/McsQe-iQF9o4ZDc0


*አፍቅሬ ያጣሁሽ*


አፍቅሬ ያጣሁሽ ያልሰመረው ህልሜ፡
ብመኝሽ ያልመጣሽ ደግሜ ደግሜ፡
ዞረሽ ያላየሽኝ ተሰባብሮ ቅስሜ፡
መጥተሽ ያላደሽው ባንቺ ታምቶ ስሜ፡

ልቤን አሳጥተሽ የፍቅርን ምላሽ፡
በባዶ ሸኘሽው ላይ ታች አንከራተሽ፡
እኔ ነኝ ምስኪኑ አፍቅሬ ያጣሁሽ፡

አይኖቼ አልቦዘኑም አልደከሙም ለ እንባ፡
ሙሾ አወርዳለው እጄ ላትገባ፡
ቀኑ አልነጋ አለኝ ቀትር ጨልሞብኝ፡
ምሽቱም ከሲኦል እኩያ ሆኖብኝ፡
መኖር ልክ እንደ ሞት መስሎ እየታየኝ

ከላዬ ላይ ይውረድ ጨርቄ ምን ያረጋል፡
አልግባ ከቤቴ ካደባባይ ልዋል፡
ሰንደል በፀጉሬ ኮተቱን በእጆቼ፡
ቆሻሻን ወድጄ ንፁውን ጠልቼ፡

በዛጋ እንዳትሄጂ ተይ እብድ አለ ካሉሽ፡
ስለማንም አይደል ላንቺ የነገሩሽ፡
እስካሁንም ድረስ በእብደት የማፈቅርሽ፡
እኔው ነኝ፡
እኔው ነኝ ውዴ ሆይ አፍቅሬ ያጣሁሽ፡
ስለማንም አይደል ላንቺ የነገሩሽ፡፡


~ማስታወሻነቱ ፍቅራችሁ ተቀባይነት ላጡ share
👇👇👇
https://t.me/joinchat/McsQe-iQF9o4ZDc0


#ለራቅሽኝ ............
............ #ለናፈቅሽኝ
~~~~~~~~~~~~ ✉


እኔስ ናፍቀሽኛል

ናፍቀሽኛል ብልሽ ቃሉን አሳንሼ፤
ቃላት ቢቸግረኝ መዛግብት አስሼ፤

እንዳትቀየሚኝ

ቋንቋ ባጣ ኖሯል ፤
እንዲ እንደዋዛ
ያልኩት ናፍቀሽኛል፡፡

ናፍቀሽኛል ስልሽ ናፍቀሽኝ ከልቤ
ሳቁ፡ ጨዋታሽን፡ ኩርፊያሽን ተርቤ

ያ የዋርካ ዛፍ ፥ ፍቅር ያወጋንበት
ያ ውብ ጎዳና፥ ዘውትር ምንሄድበት
ያዳመጥነው ዘፈን
የፈጠርነው ዜማ ፤
ያካለልነው ሰፈር
ያ ሰፊ ከተማ...

አብረን ያሳለፍነው ያንን ሁሉ ጊዜ
እኔ አልጠራልሽም ፤
'ትዝታሽ ትዝ አለኝ' ብዬ አላደክምሽም፡፡

ግና ብቻ ውዴ
የፍቅርሽን ጦም፥ የፍቅሬን ሁዳዴ ፤
ልባችን ውስጥ ያለ
ባዳ የማያውቀው ፤
'ሆድ ይፍጀው' ብያለው
ሆድሽ ስለሚውቀው፡፡


...
...........
........
...

https://t.me/joinchat/McsQe-iQF9o4ZDc0




ሰላማቹ ብዝትዝት ይበልልኝማ😘
ቤቲ ነኝ 🙋‍♀ ባለፈው ባልኩዋቹ መሰረት
📜ከ ህይወት ማህደረ📂

የተሰኘውን የሁላችንንም ቤት የሚዳስስ ፕሮግራም ዛሬ ከምሽቱ 3:30 ላይ አዘጋጅቼላቹዋለሁ።

"ፍቅርን ይታገሉታል❔❓❔❓
📝 ባለ ታሪክ ሊሊ
ዛሬ ቶኔቶር ላይ አይቀርም 🙅‍♀😁

ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ ሼር ያርጉ 👍👍👍
👇👇👇👇👇👇👇👇
💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨
✨💥✨@manetio💥✨💥
💥✨💥@manetio✨💥✨
✨💥✨💥💥✨💥✨💥✨







20 last posts shown.

715

subscribers
Channel statistics