Forward from: Thoughts
"ክብደት መቀነስ ይፈልጋሉ፤ ወይስ የተስተካከለ አቋም?ስለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው። ወደ ሞኬ ስፖርት ቤት ጎራ ይበሉ ፤ ሁሉንም በአይነቱ በተለየ አቀራረብ ያገኛሉ።" የሚል ትልቅዬ ባነር ሰፈራችን መውጫ ላይ ተሰቅሎ አየን ቅዳሜ ጠዋት።
ባነሩ ላይ እንደሌሎች ጂም ቤቶች የመሮጫ እና የክብደት ማንሻ መሳርያዎች የሉም ያለው ጠቆር ያለ ጠብደል ሰውዬ ነው።
እኔ ደግሞ ማትሪክ ተፈትኜ እቤት የተቀመጥኩበት ሰዓት ስለነበረ በማግስቱ ከጓደኞቼ ጋር ተሰብስበን ሄድን። ለመመዝገብ የሄደው ሰው ብዙ ነበረ። ይሄኔ 'በአይነቱ ለየት ያለ' ስላለ እኮ ነው እያልን እየሳሳቅን ሄድን።
የሰበሰበን የሰፈሩ ሜዳ ላይ ነበረ። ሁላችንንም በረድፍ ካስቀመጠን በኋላ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ወጣና ለንግግር መዘጋጀት ጀመረ። "ኦ ኦ ለስፖርት ነው ይሄ ሁሉ ወከባ" እያልን እያጉረመረምን እያለ ማውራት ጀመረ።
"ከመመዝገባችሁ በፊት ማወቅ ያለባችሁ ነገሮች ስላሉ ነው። በመጀመሪያ እንድታውቁ የምፈልገው ነገር ቢኖር የለመዳችሁትን አይነት ነገር እንዳትጠብቁ ነው።"
"በመቀጠል ልነግራችሁ የምፈልገው ከድሮ ጀምሮ የሚገርመኝ እና ብቀይረው የምፈልገው ነገር ነበር ይኸውም በየስፖርት ቤቱ በየጂሙ የሚለፋው ልፋት እና የሚባክነው ጉልበት ነው። ስለዚህ ጉልበታችንን ብረት ላይ ሳይሆን ፍሬያማ በሆነ ነገር ላይ ነው የምናፈስሰው ። ስለዚህ አሁንም ከእኔ ጋር መቀጠል የምትፈልጉ ነገ እንገናኝ እና እንጀምራለን" ብሎ ጨረሰ።
በማግስቱ ከጓደኞቼ ውስጥ እኔ ብቻ ነበርኩ ለመሄድ የወሰንኩት። እንገናኝ ያለው ቦታ ላይ ስደርስ ጥቂት ሰው ነበረ የነበረው "በሉ እንሂድ መስክ ነው ዛሬ የምንወጣው" ብሎ ወዳዘጋጀልን መኪና ጠቆመን። ወደከተማ መውጫ አካባቢ ያለ ቦታ ነበረ የወሰደን።
ስንደርስ ወደሰፊ ሜዳ እየጠቆመን "ይሄ የደረሰ ሰብል የአንድ ሽማግሌ ገበሬ ነው። ዛሬ ይሄንን ሰብል በማጨድ ያከማቸነውንም ስብ እናቃጥላለን፤ ገበሬውንም እንረዳቸዋለን" አለን። ደስ ብሎን ስናጭድ ውለን፤ ላብ በላብ ሆነን፤ አንደተባልነውም ስባችንን አቃጥለን በምርቃት ተንበሽብሸን ተመለስን።
በቀጣይ ስንገናኝ ደግሞ እንጦጦ ሄደን እንጨት የሚሸከሙትን እናቶች ስናግዝ ዋልን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንጨት ለሚሸጡ ሰዎች ፈልጠን ስናዘጋጅ ...ብቻ ምን አለፋችሁ ብዙ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን በጉልበታችን ረድተን፤ ሲደሰቱ አይተን፤ ሰውነታችንንም እያንቀሳቀስን ቆይተን ዩኒቨርሲቲ ተጠራሁ።
እያዘንኩም ቢሆን የግድ መውጣት ስለነበረብኝ ወጣሁ። ስወጣ ግን ለዚህ መልካም አስተሳሰቡ እንደምስጋናም ጭምር ለሞኬ አዲዳስ ጫማ ስጦታ ሰጥቼው ተለያየን።
እስኪ አስቡት ሁሉም ሰው በየስራ መስኩ ላይ ትንሽ ደግነት ቢጨምርበት እንዴት መረዳዳት እንደሚቻል።