Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™


Channel's geo and language: not specified, Amharic
Category: Psychology


አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@MentalCounsel
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, Amharic
Category
Psychology
Statistics
Posts filter




መንገድ ፈልግ!
፨፨፨//////፨፨፨
ካለህበት አጣብቂኝ የምትወጣበት አይነተኛ መንገድ ፈልግ፤ ስሜትህን የምታስተካክልበት፣ የገዛ ሰላምህን የምታገኝበት፣ ከእራስህ በላይ ለሰዎች መረጋጋት አስተዋፅዖ የምታበረክትበትን፣ የመፍትሔ ሰው የምትሆንበትን ሁነኛ መንገድ ፈልግ። የነገሮች መምታታት፣ ባላሰብከው ሁኔታ መቀያየር፣ ወዳልተፈለገ ክስተት ማምራት ሊያስፈራና ሊያስደነግጥ ይችላል። ነገር ግን ከዚህ የምትወጣበትና ብዙዎችንም የምታወጣበት መንገድ አይጠፋህም። ችግሩን ባትፈጥረው እንኳን የመፍትሔ ሰው መሆን አያቅትህም። ትኩረትህን ሁሉ ጠቃሚ መንገድና አካሔድ ላይ በማድረግ፣ ሃሳብህን በሙሉ ወደ መፍትሔ በማዞር የተሻለውን አዋጭና ዘላቂ መንገድ መፈልግ ጀምር። ያንተ የተወሰነ አስተዋፅዖ ብዙዎችን ሊታደግ እንደሚችል አስተውል። የቻልከውን ባለማድረግህ እንዳትቆጭ በመጥፎ ጊዜ መልካም ተግባርን ፈፅመህ ተገኝ። 

አዎ! ጀግናዬ..! ተስፋህ በሚፈተንበት ወቅት ተስፋ ላለመቁረጥ በርታ፤ አጣብቂኝ ውስጥ በሆንክ ሰዓት አምላክህን ደጅ ከመጥናት በፍፁም እንዳትቦዝን፤ ፍረሃት በወረረህ፣ ስጋት በከበበህ ወቅት በቻልከው አቅም ስሜትህን ለመቆጣጠር ሞክር፤ እራስህን አረጋጋ፤ ለይትኛውም ተግባርህ ሃላፊነት ይሰማህ። ብዙ ጊዜ ሰዎች መጥፎ ስሜታቸውን ከመሸሽ በተሻለ ሌላ   ሁነኛ መፍትሔ ሲጠቀሙ አይታይም። ሽሺት፣ ማሳለፍ ወይም ማረሳሳት ግን ተመራጩና ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ምን እንደሚያስጨንቅህ፣ ለምን ስሜትህ እንደተረበሸ፣ ስለጉዳዩ ምን ማድረግ እንደምትችል፣ እስከመቼ እንደዚህ እንደምትቀጥል እራስህን ጠይቅ። እራስህን ማረጋጋት ካልቻልክና ስሜትህን ካልተቆጣጠርክ የሚከተለው አደጋ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል አስተውል።

አዎ! ማስተዋል እያንዳንዱን እንቅስቃሴህን መቆጣጠር ላይ ትልቅ ሚናን ይጫወታል፤ የተበላሹ ነገሮችን የምታስተካክለው፣ የጠፉት ላይ እርማት የምትወስደው በሰከነ መንፈስ ተረጋግተህ በማስተዋልና ማሰላሰል ስትችል ብቻ ነው። ሰውነት በአዕምሮ ይመራል። በጥንቃቄ የሚያስብና አስተዋይ ልቦናም ህይወትን ቀላልና አስደሳች ያደርጋል። ከወትሮው በተለየ ስሜትህ ላይ መንገስ የሚኖርብህ፣ እራስህን መቆጣጠርና መታደግ የሚጠበቅብህ ወቅት ሊኖር ይችላል። ስሜታዊነት እንዳይመራህ ተጠንቀቅ፤ ግልፍተኝነትና ንዴት እንዳይነዳህ እራስህን ለመቆጣጠር ሞክር። ድርጊቶችህን በሙሉ በተጠናና በተረጋጋ ሁኔታ አድርጋቸው። ችግርን በችግር ሳይሆን በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ፣ በአስተዋይ ልቦና ለመፍታት የተቻለህን ሁሉ አድርግ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha Aschalew)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪




እየሰራህ ነው!
፨፨፨////፨፨፨
አነሱ ሲያወሩብህ አንተ እየሰራህ ነው፤ እነርሱ ሲያሙህ፣ ሲያብጠለጥሉህ፣ ስምህን በክፉ ሲያነሱ፣ አለመቻልህን ሲተነትኑ አንተ አንገትህን ደፍተህ እንዳልሰማህ ግዴታህን እየተወጣህ ነው፤ ጉዳይህን እየፈፀምክ ነው፤ የተሻለውን ምህዳር ለእራስህ እየፈጠርክ ነው። ማውራት ስራ ነው፤ ሰዎችን እየተከታተሉ አቅማቸውን ማሳነስ፣ በመስፈርት ማስጨነቅና ጥረታቸውን ዋጋ ማሳጣት ግን ክፋት ነው። የፈለከውን አይነት ሰው የመሆን መብት አለህ፤ መብትህንም ለመፈፀም የማንም ድጋፍና ይሁንታ አያስፈልግህም። ሰዎች በሚሰራና ከእነርሱ ተለይቶ እራሱን ለማሻሻል በሚጥር ሰው ላይ ከአመታት በፊት ያወሩ ነበር፣ ዛሬም እያወሩ ነው፣ ነገም እንዲሁ እያወሩ ይቀጥላሉና ይህ አዲስ ነገር አይደለም። የወሬውን፣ የሐሜቱን፣ የትቺቱን ሜዳ ለእነርሱ ተውላቸው፣ አንተ የስራውን፣ የጥንካሬውን፣ የብርታቱን ሜዳ አጥብቀህ ያዝ። የሚያዋጣህን ካንተ በላይ የሚያውቅልህ ሰው የለም። የሚያወራብህ፣ አስተያየት የሚሰጥህ፣ የሚያብጠለጥልህ፣ የሚተችህ ሁሉ ካንተ ተሽሎ እንዳልሆነ ተገንዘብ።

አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች ቀላሉን ሲመርጡ አንተ ከባዱን በሃላፊነት እየተወጣህ ነው፤ ሌሎች ስም በማጥፋት ሲጠመዱ አንተ ስራህን እየሰራህ ነው፤ አንዳንዶች ዋጋህን ሊያሳንሱ፣ ክብርህን ሊያጎድሉ ሲጥሩ አንተ በፈለከው መጠን ህይወትህን እየመራህ ነው። እንደ ባሪያ ትሰራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትተጋለህ፣ ላብህን ታፈሳለህ፤ እንደ ንጉስ በክብር፣ በፍቅር፣ በነፃነት ትኖራለህ። ማንም ስለስራህ ምንም ቢል አይገድህም፤ ማንም ያልሆንከውን ስም ቢለጥፍብህ አያስጨንቅህም፤ የትኛውም ሰው በማይመለከተው እየገባ ሊያወክህ ቢሞክር ትኩረት አትሰጠውም፤ እርሱን የምትሰማበት ጊዜ አይኖርህም። ሊያቆሙህ ይደክማሉ እንጂ አያቆሙህም፤ ሊያሰናክሉህ ይለፋሉ እንጂ አያሰናክሉህም፤ ስሜትህን ሊጎዱ ብዙ ቃላት ይሰነዝሩብሃል እንጂ ስሜትህን በፍፁም አይጎዱትም። ካንተ ፍቃድ ውጪ የትኛውም ተፅዕኖ ሊያቆምህም ሆነ ወደኋላ ሊመልስህ አይችልም።

አዎ! ስራህ ማምለጫ ብቻ ሳይሆን አላስፈላጊ ጫናዎችን መከላከያህ ነው። ስላመንክበት ታደርገዋለህ እንጂ ስላመኑበት አታደርገውም። ያንተን ጉዳይ ለመፈፀም መንገድ አታጣም፤ ከልብህ ልታሳካው የምትፈልገውን ነገር በምንም ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ታሳካዋለህ፤ ታደርገዋለህ። የምትመኛቸው አበርታች ቃላት፣ የምትናፍቃቸው ድጋፍ ሰጪና አነቃቂ ንግግሮች እንዳሰብከው የቅርብ ከምትለው ሰው ላይገኙ ይችላሉ። አንተ ስለእራስህ ለእራስህ የምትነግረው ግን ከማንም የበለጠ አነቃቂና አበርታች ቃል እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት፣ በሰዎች አሉታዊ ንግግር፣ በሁኔታዎች አለመመቻቸት ብትወድቅ የምትነሳው እራስህ ነህ። ትችላለህ! መቻልህን በተግባር አሳይ፤ ታውቃለህ! እውቀትህን ኑረው፤ አቅሙ አለህ! በህይወትህ ግለጠው፤ ሰዎች ከሚያስቡህ በላይ ነህ! መሆንህን በእራስህ መንገድ አረጋግጥላቸው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪


ነገ ምሽት 1:0ዐ ሰዓት!

❇️ በራስመተማመን እንዳይኖረን ያደረጉን መጥፎ ልማዶች ምንድናቸው?
❇️ እንዴት እነርሱን አሸንፈን በራስመተማመናችንን መገንባት እንችላለን?

ነገ ምሽት 1:00 ሰዓት በተከታዩ ዩትዩብ ቻናል እንነጋገርበታለን!

https://www.youtube.com/channel/UCSdpYXLmn4YzEzA3y_Qn64A?sub_confirmation=1

አሁን SUBSCRIBE በማድረግ ጠብቁኝ!
🦋
በቸር ያገናኘን! 😍🙏


እራሳችሁን ታደጉ!
፨፨፨/////////፨፨፨
ለራሳችሁ ጥራት ያለው ጊዜ መስጠት ላይ እንዴት ናችሁ? ራሳችሁን ምንያህል ትንከባከባላችሁ? ለአስተሳሰባችሁ፣ ለጤናችሁ፣ ለውሏችሁ፣ ለውስጣዊ መረጋጋታችሁ ምንያህል ትጠነቀቃላችሁ? የዓለምን እውነታ መቀየር አትችሉም። ከጥንቃቄ ማነስና እራስን ችላ ከማለት የሆነ ነገር ቢፈጠርባችሁ ማንም ቆሞ ለተከሰተባችሁ ጉዳይ መፍትሔ አያፈላልግም። እናንተ ደህና ሆናችሁም አልሆናችሁም፣ እናንተ በህይወት ኖራችሁም አልኖራችሁም ዓለም ወደፊት መጓዟን ትቀጥላለች። በአጉል የዋህነት እራሳችሁን አታታሉ። እናንተ ስለወደቃችሁ ሰማይና ምድር አይገለባበጡም፣ እናንተ ስለተሳሳታችሁ ትክክል የሆኑ መርሆች አይቀየሩም። የራሳችሁ ልኬት፣ የእራሳችሁ የህይወት መንገድና የእራሳችሁ አላማ እንዳላችሁ አስታውሱ። ይሔንን እወቁ፦ ህይወት ለልፍስፍስና እራሱን ለማይንከባከብ ሰው ቦታ የላትም። ነቃ ብላችሁ እራሳችሁን ጠበቁ። ከእናንተ ቦሃላ የሚመጣ የትኛውም ነገር ትርፍ እንደሆነ አስተውሉ። ከምንም ከማንም እናንተ ትቀድማላችሁ። የምታሳድዱት የትኛውም ነገር የእናንተ አገልጋይ እንጂ እናንተ የእርሱ አገልጋይ አይደላችሁም።

አዎ! እራሳችሁን ታደጉ! እራሳችሁን ጠብቁ፣ ለእራሳችሁ ትኩረት ስጡ፣ እራሳችሁን ለመንከባከብ በፍፁም እንዳትሰለቹ። እናንተ ደከማችሁም አልደከማችሁም፣ ጠንክራችሁ ሰራችሁም አልሰራችሁም፣ ብዙ የማይተካ ዋጋ ከፈላችሁም አልከፈላችሁም ህይወት በሆነ ቦታ ክፍተት ማሳየቷ አይቀርም። ክፍተቷን የምትሞሉትም ለእራሳችሁ መድረስ ሰትችሉና እራሳችሁ ላይ የሰራችሁ እንደሆነ ብቻ ነው። የዓለም ዝናና ገንዘብ እንዲያታልላችሁ አትፍቀዱ። ሁሉን ምድራዊ ንብረት አፍርታችሁ ጤናና ሰላማችሁን ብታጡ ምን ይጠቅማችኋል? ምንም። በሰዎች ዘንድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ሆናችሁ እናንተ ግን በእራሳችሁ ደስተኛ ካልሆናችሁ ምን ይረባችኋል? ምንም። የማንም ሰው ድክመት እራሱ ከሆነ ይሔንን ድክመቱን የሚሞላውም እራሱ ብቻ ነው። ስኬትም ሆነ መትረፍረፍ ሮጦ በቀደመ፣ ፈጥኖ ሪቫኑን በበጠሰ፣ ሃብት ንብረቱን ባግበሰበሰ ወይም በሰዎች በተከበበ አይደለም። ትልቁ የእያንዳንዳችን ከፍታና ስኬት የሚለካው እራሳችንን በመጠበቅ አቅማችንና ለእራስ ብቁ ሆኖ ከመገኘት አንፃር ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ካጣህ ዓለም ላይ ምንም የሚቀርህ ነገር የለም። ለእራስህ መሆን ካልቻልክ ለማንም ልትሆን አትችልም። ነገሮችን አታወሳስብ፣ የራስህ ትልቅ ችግር ሆነህ አትገኝ፣ እራስህን ፋታ በሌለው አዙሪት ውስጥ አትክተተው። ለእራስህ ጊዜ ስጥ፣ እራስህን ተንከባከብ፣ ውስጥህን አዳምጥ፣ የጥሞና ጊዜ ውሰድ፣ ለራስህ ቅርብ ሁን። አብዛኛው የሰው ልጅ የማያውቀውና የማይጠቀመው አንድ የተለየ ስጦታ ተሰጥቶታል። ይሔም ስጦታ፦ ከጤንነቱ ጀምሮ እስክ ትልቅ አቅሙ እራሱን ስካን (scan) አድርጎ የማወቅ ሃይል ነው። እንዳለመታደል ሆኖ የህመሙን ምልክቶች ተናግሮ ከዛም በላይ በጣም ጥልቅ ምርመራ ተደርጎለት ምን ችግር እንዳለበት ከሌላ አካል ይነገረዋል። ነገር ግን እራሱን የሚከታተልና እያንዳንዱን ስሜቱን የሚያዳምጥ ቢሆን ማንም ድክመቱንና ችግሩን ባልነገረው ነበር። አንተ ስለራስህ ካላወቅክ ማንም ስላንተ ሊያውቅልህ አይመጣም። ምናልባት ለእራስህም ሆነ ለወዳጆችህ ብለህ ፊትለፊት መጋፈጥ ያለብህ ብዙ ነገር ይኖርብህ ይሆናል የትኛውም ነገር ግን እራስህን የመታደግን ያህል ዋጋ ሊኖረው አይችልም። እራስህን ተንከባከብ፣ ጤናህን ጠብቅ፣ አስተሳሰብህን አንፅ፣ ጠንካራ ማንነትንም ገንባ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪

2k 0 20 4 32



እየተቀጣን እናምፃለን!
፨፨፨፨///////////፨፨፨፨
ሰዎች ነን፣ ማንነታችን ሁለት ተቃራኒ መለያ አለው። ክፋትና ደግነት፣ ርህራሔና ጭካኔ፣ ሰላማዊና ጠበኛ፣ አልሚና አጥፊ፣ ተስፈኛና ተስፋቢስ፣ ደፋርና ፈሪ፣ አሳቢና አድራጊ። ብቻ ብዙ ብዙ ተቃራኒ መገለጫዎች አሉን። ሁለቱን አስታርቆ መኖር ጥበብን ይጠይቃልና ትናንትም፣ ዛሬም እንዲሁ እንደተቃራኒዎቹ ማንነታችን እኛም ጎራ ከፍለን በተቃርኖ ዓለም ውስጥ እንኖራለን። በገዛ እጃችን የህይወት እንቆቅልሽነት እያደረ እየጨመረ እንዲመጣ እያደረግን ነው። ፍላጎታችን ሰላም ይሁን ጥፋት፣ ምኞታችን ፍቅር ይሁን ጥላቻ፣ ምርጫችን እድገት ይሁን ጥላቻ የምናውቀው ነገር የለም። ሰላምን የሚፈልግ ሰው ወንድሙ ምንም ቢያደርገው ሊያጠፋው አይነሳም፣ ፍቅር የሚመኝ ሰው የትኛውም ወገኑ እንደበደለው ቢያስብ ሰይፍ አይመዝበትም። የእውነት ፍላጎታችን ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻልንም። የውሸት እናለቅሳለን፣ ደጋግመን በአስመሳይ ማንነት እንገለጣለን፣ ይቅርታ የጠየቅንበትን ጥፋት አስሬ እንደጋግመዋለን፣ በትናንት አፈታሪክ ዛሬያችንን እናመሰቃቅላለን፣ ባለፈ ክንውን ማንነታችንን እናስራለን።

አዎ! እየተቀጣን እናምፃለን! እየተገረፍን እንበድላለን። ችግር በችግር ላይ፣ ፈተና በፈተና ላይ ሲደራረብብን እንኳን ለምን እንደሆነ መጠየቅ አልፈለግንም። ፈጣሪን ይህን ያህል ያሳዘነ ትውልድ ይኑር አይኑር እራሱ ፈጣሪ ያውቃል። እኛ ግን በጊዜ ካልነቃን፣ ጥፋታችንን ካላቆምን፣ ድርጊት ሀሳባችንን ካላስቀደምን ጉዟችን ተያይዞ ወደመጥፋት እንደሆነ ግልፅ ነው። ልባችን ምነኛ ደንድኗል? ውስጣችን ምንኛ ጨክኗል? አይናችን ምነኛ ታውሯል? ጆሯችን ምነኛ ተደፍኗል? በጥፋታችን እየተቀጣን ዛሬም ጥፋታችንን ገፍተንበታል፣ ለበደላችን ዋጋ እየከፈልን ዛሬም እርስበእርስ እንበዳደላለን። ፈጣሪ ታጋሽ ነው፣ የትዕግስቱን ያህልም የቅጣት አምላክ ነው። ቅጣቱን ፈርተን ሳይሆን የትዕስቱን ብዛት አይተን፣ በክፍያው ተደናግጠን ሳይሆን በፍቅሩ ተማርከን እንዳቅማችን ለህጉ ለመገዛት እንሞክር፣ በሰላምና በጤና ያኖረን ዘንድ በሰጠን ቃሉ እንመራ። በምንም ጊዜ ወንድም ከወንድም፣ ጎረቤትም ከጎረቤቱ ጋር ላይግባባ ይችላል፣ ከዛም በላይ ሊጋጭ ይችላል። መፍትሔው ግን ዞሮ ዞሮ ይቅርታ ነው። ተነጋግሮ መግባባት፣ ይቅር መባባል፣ ለፍቅር ቦታ መስጠት።

አዎ! ጀግናዬ..! የሰው ቁጣ ፈልቶ እንደሚቀዘቅዝ ውሃ ነው። የፈጣሪ ቁጣ ግን በእርሱ ፍቃድ የሚመጣ በእርሱም ፍቃድ የሚነሳ ነው። ፈጣሪ ያዘነበትን ትውልድ ከእራሱ ከፈጣሪ በቀር ማንም ሊታደገው አይችልም። ዓለም በሙሉ በአምላክ መዳፍ ውስጥ ነች። ሁሉን ያውቃል፣ ለሁሉም መፍትሔ አለው። ውስጥህ የሚነገርህን እውነተኛ ነገር አዳምጥ፣ ሳትሰላች የዓለምን የጉዞ አቅጣጫ ተመልከት። ምንም ሲመጣ ምን ቦታ እየለቀቀ ነው? የሰው ልጅ አቅም በምን እየተገለጠ ነው? መጠፋፋት ወይስ መረዳዳት በዝቷል? የዓለም ገዢዋ ማነው? አንተንስ ማን ገዝቶሃል? ዓለም ላይ ምንም ብትመለከት ስለተመከትከው ነገር ከማውራትና የሆነ ነገር ከማድረግ የቀረበውና ቀዳሚው ነገር እራስን አውቆ፣ በእራስ መንገድ የተረዱትን ህይወት መኖር መቻል ነው። አመፁን ወደ ጎን እንበለው፣ ማጉረምረሙን እናቁም፣ ከሁሉም በፊት በጥፋታችን ምክንያት የመጣብንን ቅጣት በፀጋ እንቀበል፣ የደነደነውን ልባችን እናለስልሰው፣ የእውነትም ምህረትን ከፈጣሪ እንለምን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪




ፍጥነትህን ጨምር!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
ሩጫህ የት ለመድረስ ነው? ለምንድነው የምትጣደፈው? እንቅልፍህን የምታጣው ለምን ይሆን? ትግልህ፣ ድካምህ፣ አልበገር ባይነትህ፣ ፅናትህ፣ ትዕግሥትህ፣ ወኔህ ለምን ይሆን? ይህ ሁሉ ለህይወት አለማህ /Life Purpose/ የምትሰጠው ስጦታ፣ የምትከፍለው መሱዓትነት ነው።

አላማ ላለው ሰው እያንዳንዱ ቀናት፣ እያንዳንዱ ሰዓትና ደቂቃዎች የእራሳቸው ትርጉም አላቸው። እያንዳንዱ ተግባሩ በሰዓታት የተከፈሉ፣ ከዓላማው የተገናኙ፣ ወደፊትቱን የሚወስኑ መሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል። የህይወት ጠዓም፣ እርካታዋ ከልብ ይሰማዋል።

አዲስ ቀን ሲያይ በምክንያት እንደሆነ ይረዳል፣ አዲስ ሰው ሲያገኝ የሚሰጠው፣ የሚቀበለው ነገር እንዳለ ያጤናል፤ ያሯሩጠው፣ አብሮት ይጓዝ ይሆን፣ የጋራ አለማ፣ ተያያዥ ራዕይ ይኖራቸው ይሆን ይመረምራል።

አዎ! ጀግናዬ..! በህይወት አላማህ ወሳኝነት ልክ ፍጥነትህን ጨምር፣ ፅናትትህን ከፍ አድርግ፣ ትዕግስትህን አብዛ፣ ትግልህን አጠንክር። የአላማህ አስፈላጊነት፣ የራዕይህ ትልቅነት ለእያንዳንዱ ተግባርህ በምትሰጠው ትኩረት የሚወሰን ነው።

ፊትለፊትህ ብሩህ ነው፤ አላማህ ግብ አለው፤ ህይወትህ ትርጉም አግኝቷል፤ ለምን እንደምትኖር አውቀሃል፤ አምላክ አብሮህ እንዳለ ተረድተሃል፤ ጉዞህን የምታመቻቸው አንተ እንደሆንክ ገብቶሃል።

አዎ! የሩጫህ ሚስጥር፣ ትጋት፣ የትግልህ ምክንያት በግልፅ ታይቶሃል፤ የቀናት መምጣት ትለቁ የህይወት በረከት፣ የህይወት ስጦታ መሆኑን ተረድተሃል፤ ጀምሮ የሚተው፣ የሚያቆም ማንነት የለህም፤ የምትታወቀው በአላማ ፅናትህ፣ በትዕግስትህ፣ በአድራጊነትህ ነው።

በርታ! መልካም ጊዜያት ከፊትህ አሉ፤ በጎ፣ ተናፋቂ ሁነቶች ከፊት ይጠብቁሃል። ተስፋህን ከሚቀሙህ፣ የህይወት ትርጉምህን፣ አለማህን ከሚያሳጡህ ተግባራት ተቆጠብ፤ ዞር በል፤ የህይወትህን እጣፋንታንም እራስህ ወስን።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

🔺🔻 SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊💪




ድጋሜ አታገኘውም!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ተሳስተህ የምትማረውን ትምህርት ድጋሜ አትማረውም፤ ያመለጠህን ጊዜ ድጋሜ አታገኘውም፤ በብዙ ጥረት የምታካብተውን ልምድ እንደገና አታገኘውም። ምድርን መሰናበቻህ ሲቀርብ ከምትነቃ አሁን በጊዜ ንቃ፤ ድጋሜ ለማታገኛቸው ስጦታዎችህ ትኩረት ስጣቸው፤ ውድነታቸውን ውድ ነገር በማድረግ ግለፅላቸው፤ ልብህን ለማሞቅ ቁጭ ብለህ መቆዘም ሳይሆን ተነስተህ የፈለከውን አድርግ። ሽልማት እያሰብክ እራስህን አታድክም፤ ቁስ ባትሸለም ውስጣዊ ሃሴትን የሚሸልምህ፣ የማያልቀውን ደስታ የሚያድልህ ተግባር ውስጥህ አለ። የምትናፍቀው ለውጥ፣ የምትመኘው ከፍታ፣ የምታስበው ስኬት በጥረትህ ልክ የሚመጣ ጉዳይ ነው። ተስፋን በብዙ ተንከባከበው፤ ለእምነትህ ድጋፍ ሁነው፤ የታላቅነት አመለካከትህን አጥብቀህ ያዘው፤ በእራስመተማመንህን ከምንም በላይ ዋጋ ስጠው፤ ዛሬህ ላይ በሚገባ ሰልጥን። ታሪክ ሆኖ በኩራት የምታወራበትን ቅፅበት አሁን መፍጠር ጀምር።

አዎ! ጀግናዬ..! ድጋሜ አታገኘውም፤ እንደገና አይመጣምና እያንዳንዱን የህይወት ስጦታህን፣ ቀንህን፣ ጤናህን፣ ሰላምህን፣ እውቀትህን፣ ጥበብህን፣ ማስተዋለህን፣ ብለሃትህን እንደ ብርቅ፣ አላቂና ውድ ነገር በአግባቡ ተጠቀመው። እንዲሁ እንደ ቀላል የሚባክን፣ ዋጋ የሌለው፣ ተስፋህን የማያጎላ፣ ለምኞትህ የማያቀርብህ ስጦታ እንደማይሰጥህ አስብ። በብረሃናማው ጊዜህ በሚገባ መኖር ከቻልክ ፀሃይህ መጥለቅ ስትጀምር፣ የድካም ዘመንህ ሲመጣ፣ ተፈጥሮ ስትሰለጥንብህ አንዳች የሚያስቆጭህ ነገር አይኖርም። የአሁኗን ቅፅበት ድጋሜ የመኖር እድል እንደማታገኝ መረዳትህ ብቻ በሙሉ ስስት እንድትጠቀማት ሊያደርግህ ይገባል።

አዎ! አስቸኳይ ሃላፊነት፣ ጊዜ የማይሰጥህ ተጠያቂነት፣ ድጋሜ የማይፈፀም ግዴታ እንዳለብህ አስታውስ። ህይወትን በሙላት የመኖር ሃላፊነት፣ መኖርህን ትርፋማ የማድረግ ግዴታ፣ ለእያንዳንዱ ቅፅበቶችህ፣ ለእያንዳንዱ ስጦታዎችህ ዋጋ የመስጠት፣ ትርጉም የመፈለግ ተጠያቂነት አለብህ። የሚጠይቅህም ሌላ ማንም ሳይሆን የእራስህ እውነተኛ ማንነት፣ ውስጥህን በሃሴት ለመሙላት፣ ከፍታህን ለማምጣት የሚታገለው ድንቁ ማንነትህ ነው። ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ ሊደረግ ይገባል። መጨረሻህ ቁጪት፣ ስቃይና የልብ ስብራት እንዲሆን ካልፈለክ አሁን ነቃ በል፤ ህይወትህን ሙሉ አድርጋት፤ በእያንዳንዱ ቀናት ውስጥ በመኖርህ፣ የእራስ ፍለጋ ጉዞ ውስጥ በመሆንህ፣ እራስህን ለማሳደግ በመጣርህ በእርግጥም ኩራት ይሰማህ፤ በምርጫህና በውሳኔህ ሃሴት አድርግ፤ በማንነትህ ሁሌም ደስ ይበልህ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪


በTikTok ልታገኙን ለምትፈልጉ!
እነሆ አድራሻችን
👇👇
@mikre_aimro' rel='nofollow'>http://tiktok.com/@mikre_aimro


ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች!
፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨
ዶ/ር ቪክቶር ፍራንክል (Dr. Victor Frankl) ይባላል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ኦስትሪያዊ ታዋቂ ኒዎሮሎጂስት (Neurologist) እና ሳይኮሎጂስት (psychologist) ነው። በህይወትና የህይወትን ትርጉም በማግኘት ዙሪያ በሚያነሳቸው ሀሳቦችና አስተምህሮዎች ይታወቃል። በአንድ ወቅትም እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለምን እንደሚኖሩ ለማያውቁና ከህይወት ምንም ለማይጠብቁ ሰዎች ህይወት በእራሷ ከእነርሱ ሌላ ነገር እነደምትጠብ ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።" የህይወት አላማችሁን ፍለጋ ብዙ ዋጋ ብትከፍሉም ላታገኙት ትችላላችሁ፣ ለዘመናት ስታደርጉት የነበራችሁት ነገር የሆነ ጊዜ ስትነቁ ትርጉም አልባ ሊሆንባችሁ ይችላል፣ ከዚህም በላይ ከእራሳችሁና ከህይወታችሁ ምንም የተሻለ እሴትን መጨመር የሚችል ነገር መጠበቅ ታቆሙ ይሆናል። ነገር ግን ይሔንን አስተውሉ። እናንተ በሰውኛ አዕምሮ አስባችሁ፣ አውጥታችሁ አውርዳችሁ ደክሟችሁና ሰልችታችሁ ያላገኛችሁት የህይወት ትርጉም ዝም ብላችሁ ስትኖሩና እያንዳንዱን ሃላፊነታችሁን ስትወጡ በሒደት ወደ እናንተ ይመጣል። እናንተ የምትኖሩት ህይወት አለ፣ ህይወት ደግሞ እንድትኖሯት የምትፈልግበት መንገድ አለ።

አዎ! ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች! እናንተ በህይወታችሁ ውስጥ ትርጉምን እንደምትፈለጉ ሁሉ ህይወታችሁም ከእናንተ አንድ የተለየና የእናንተ መገለጫ የሆነ ልዩ ነገር ትጠብቃለች። የህይወት አላማን ለማግኘት መውጣት መውረድ፣ እራስን ማታገልና ማስጨነቅ አያስፈልግም። አንዳንድ ክስተቶች እራሳቸው ፍሰት አላቸው፣ ሲጨመቁ ከሚያወጡት መልካም ነገር ይልቅ እንዲሁ በራሳቸው ሲፈሱና በኡደታቸው ሲጓዙ የሚያመጡት ውጤት ይበልጥ ትርጉም ይሰጣል። የትኛውም ትልቅ ነገር መነሻው ትንሽ ነው። "ህይወት ትርጉም አልሰጥ አለችኝ" ከማለት ይልቅ "ህይወት ከእኔ ምን ትጠብቃለች?" ብሎ መጠየቅ ብዙ የተደበቁ አቅማችንን እንድናወጣ ያግዘናል። በየትኛውም ዘርፍ ሊሆን ይችላል፣ በምንም ስራ ውስጥ ሊሆን ይችላል በእኛና በእኛ ብቻ መሞላት የሚችል ክፍተት አለ። ተምረን፣ አውቀን፣ ተረድተንና አስተውለን ወይም በተፈጥሮ በተሰጠን የተለየ ክህሎት ይህንን ክፍተት መሙላት አንችላለን። ዓለማችን በችግር የተሞላች ነች፣ ወረድ ስንል አህጉራችን ውስጥ የችግር መዓት አለ፣ ከዛም ወረድ ስንል ሀገራችን ውስጥ ብዙ ያልተፈቱ እንቆቅልሾች አሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከምታየውና ከምትሰማው ችግርና ክፍተት ውስጥ ለአንተ የትኛው ጎልቶ ይታይሃል? የትኛውን ለመቅረፍ የቀረብክ ይመስልሃል? በየትኛው ላይ ብትሰማራ ነፍስህ የምትረካ ይመስልሃል? ትንሽ ጊዜ አስብ፣ ለተወሰነ ጊዜ አቅድ፣ በቀጣይ ግን ቀጥታ ትግበራውን ጀምር። ብዙ ሰው የማያየውን ነገር ማየት ስትችል ብቻ ከሰዎች የተለየ አዲስ ነገር ማከናወን ትችላለህ። ህይወትን በዓላማ መኖር ውስጥ እይታ፣ ዝግጁነት፣ ቆራጥነትና የተግባር ሰው መሆን በጣም አስፈላጊዎች  ጥበቦች ናቸው። እይታህ የምትሔድበትን አቅጣጫ ያጠራልሃል፣ ዝገጁነት በማንኛው ሰዓት ወደ ተግባር እንድትገባ ያደርግሃል፣ ቆራጥነት ከሃሳብ በላይ ተግባር ላይ እንድታተኩር ያደርግሃል፣ የተግባር ሰው መሆን ደግሞ በውድቀትና በስህተት ውስጥ አያሳለፍና እያስተማረ ለላቀው ውጤት ያበቃሃል። ቀላል፣ የተረጋጋና ትርጉም ያለው ህይወት ለመኖር እንቅስቃሴዎችህን ሁሉ ትግል አታድርገው። የዓለምን ክፍተት ፈልግ፣ ከፍላጎትህ ጋር አቆራኘው፣ እርሱን ለመሙላትም እንቅስቃሴህን ጀምር።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪




አትበገርም!
፨፨፨///፨፨፨
አትበገርም፤ ተስፋ አትቆርጥም፤ ወደኋላ አትመለስም፤ ብርታት አታጣም፤ እራስህን አትወቅስም፤ በእራስህ አታዝንም። የያዘ ይዞህ እንጂ የዛሬ ስፍራህ አይመጥንህም ነበር። በውስጥህ ያለው እምቅ ሃይል ሰበብ በማብዛት አያምንም፤ ምክንያት መደርደርን አይቀበልም። ማድረግ የሚፈልገውን ማድረግ እንደሚችል ያውቀዋል፤ ማን እንደሚያስፈልገው፤ ማንን መጠጋት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለ እራስህ መረዳት የሚገባህን በሙሉ ተረዳ፤ ማወቅ ያለብህን እወቅ፤ የሚጠቅምህን ተማርበት፤ ከሚያስደስትህ ተግባር ማትረፉን እወቅበት። ማንም እንደማይመጣ ታውቃለህ፤ ማድረግ የምትችለውን ተረድተሃል። በውስጥህ ያለውን የአዎንታዊና አሉታዊ ሃሳብ ፍትጊያ ፋታ ስጠው። ድምፁ ቢያንስም የአትራፊውን አዎንታዊ ሃሳብ ድምፅ አዳምጥ። ብዙ የሚታዩ፣ የሚጨበጡ፣ የሚዳሰሱ አሉታዊና ምቾት የማይሰጡ ሁኔታዎች ይኖራሉ። እነርሱን ማዳበጥ፣ እነርሱን መመልከት ስታቆም ህይወት ወደ ከፍታ ትመራሃለች፤ እድገትን ታጎናፅፍሃለች።

አዎ! ጀግናዬ..! አትበገርም! የመጣው ይመጣል እንደ አመጣጡም ትመልሰዋለህ፤ የሚሆነው ይሆናል የሆነውንም ትቀበለዋለህ። በአንድም በሌላም የሚሰብርህ ነገር አታጣም፤ አንገት የሚያስደፋህ፣ የሚያሳፍርህ ሁኔታ ይገጥምሃል። ነገር ግን ዳግም ማነሰራራት ትችላለህ። አንድ ሰሞን ወድቀህ ይሆናል፣ የሆነ ጊዜ ተዋረደህ አድማጭ አተህ፣ አጋዥ አበርታች ርቆህ ይሆናል፣ በአንድ አጋጣሚ የማትፈልገው የህይወት አዙሪት ውስጥ ተገኝተህ ይሆናል። ተስፋ የተባለ ትልቅ የህይወት ስንቅ ግን አለህ። መቀየር የምትፈልገው ነገር ይቀየራል፤ ማሻሻል የሚኖርብህ ነገር በአንተው ብርታትና ጥንካሬ፣ በአምላክ ድጋፍና እገዛ ይሻሻላል፤ ይስተካከላል። ትልቁ ህልምህ የመሻሻልህ ምክንያት ነው፤ አላማህ ለነገሮች መስተካከል መንስዔ ነው።

አዎ! ወድቀህ አትቀርም፤ እንዲ እንደ ቀላል እንደተናክ፣ ከሰው በታች እንደሆንክ አትቀጥልም። ቀና ትላልህ፤ ታገግማለህ፤ ትድናለህ፤ ትታደሳለህ። ለምንም ለማንም እንደማትበገር ታሳያለህ፤ ለምንም አንገትህን እንደማትደፋ፣ ወደኋላ እንደማታፈገፍግ፣ ለማንም የአሸናፊነት ፅዋህን አሳልፈህ እንደማትሰጥ ታስመሰክራለህ። የመኖር ምክንያትህ አንተ ነህ፤ አምላክ የፈጠረህ እራስህን እንድትችል፣ ለእራስህ አለኝታ እንድትሆን፣ እራስህን እንድትደግፍና ለብዙዎች ድጋፍ ትሆን ዘንድ ነው። ከእራስህ ሸክም በላይ የሌሎችንም መሸከም እንደምትችል አስታውስ። ፈጣሪ ልፍስፍስ አድርጎ አልፈጠረህም፤ ተስፋ ቢስ፣ የማይረባ ተራ አድርጎ ወደ ምድር አላመጣህም። እራስህን ሆነህ ተዓምር መፍጠር ትችላለህ። ምንም ሊፈጠርብህ ይችላል በፍፁም ለሽንፈት እጅህን እንዳትሰጥ፤ ተስፋ መቁረጥን አትመልከት፣ ወድቆ መቅረትን እርሳው። በርታ! እንዳትበገር።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪


ለአላማህ ታመም!
፨፨፨//////////፨፨፨
ብዙ አይነት ህመም ታመህ ይሆናል። የአካል፣ የስነ-ልቦና ወይም የነፍስ ህመም ታመህ ሊሆን ይችላል። ህመሙ ግን የመጨረሻህም የመጀመሪያህም እንደማይሆን አስተውል። በህይወት እስካለህ በተለያዩ ህመሞች ውስጥ ማለፍህ አይቀሬ ነው። አካልህ ደህና ቢሆን አዕምሮህን የሚያውክህ ነገር ይኖራል፤ አዕምሮህ ቢረጋጋ ነፍስህ እረፍት የምታጣበት ወቅት ይኖራል። ነገር ግን ምንም ስቃይና መከራው ቢበዛብህ በምትኖርለት የህይወት አላማና ህልም ምክንያት የመጣ ከሆነ ያለምንም ማንገራገር ተቀበለው። እራሱን ለማብቃት፣ ለመቀየርና ለማደግ ለሚፍጨረጨር ሰው ህመም አዲሱ አይደለም፤ ውድቀት፣ ስህተት፣ መከራ፣ መከዳት፣ መገፋት፣ ተስፋ የመቁረጥ አጣብቂኝ ብርቁ አይደለም። ሲኖርበት ነበር፣ አሁንም እየኖረበት ነው፣ ወደፊትም እየኖረበት ይቀጥላል።

አዎ! ጀግናዬ..! ለአላማህ ታመም! ለህልምህ ስትል ተሰቃይ፤ ለራዕይህ ብለህ መከራን ተጋፈጥ። አደጋውን ስለፈራህ፣ በሰዎች ንግግር ስለተሸማቀክ፣ ለስህተትህ እጅ ስለሰጠህ፣ በውድቀትህ ስለተደናገጥክ የሚቀየር ነገር የለም። ትልቁ የህይወትህ አላማ ቢያሳምምህና ቢያሰቃይህ እንኳን ውጤቱ ከዛ በላይ ለሆነ ድል ያበቃሃልና ተስፋ እንዳትቆርጥ። እንቅልፍ ያጣህባቸው ምሺቶች በእርግጥም ይከፍሉሃል፤ ተስፋ በማጣት መሃል የፈሰሱት እንባዎችህ ዋጋቸውን ይመልሳሉ፤ ከእራስህ ጋር የተሟገትክበት ጉዳይ ፍሬውን በሚገባ ያሳይሃል፤ ያለምክንያት አልተሰቃየህም፤ እንዲሁ አልታመምክም። ከህመምህ ጀርባ ትልቅ የአዕምሮ፣ የስጋና የነፍስ ፈውስ አለ። ከፀፀት ነፃ የሚያወጣህ፣ እራስህ ለእራስህ ብቁ እንደሆንክ የሚያሳይህ፣ ማንነትህ ከጊዜያዊ ህመም በላይ እንደሆነ የሚያስገነዝብህ እውነተኛ ፈውስ።

አዎ! ህመምህ ጊዜያዊ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተነግሮህ ይሆናል፣ የሚሰጥህ ጥንካሬ፣ የሚያጎናፅፍህ የተለየ ማንነት ግን ሁሌም አብሮህ ይቆያል። ህመምህን ብትረሳው እንኳን በእርሱ ምክንያት ያገኘሀው ድልና ብርቱ ማንነት ሊዘነጋህ አይችልም። የስቃይህን ምክንያት ጠንቅቀህ እወቀው። በመካከለኝነት ህይወት፣ በተመሳሳዩ የአዙሪት አለም፣ አላማ በሌለው፣ ህልም በማይታወቅበት፣ በልቶ በማደርና ወጥቶ በመግባት በተሞላ የተለመደ ህይወት መከራም ይሁን ስቃይ ሊኖር አይችልም። መርጠህ የምትሰቃየው ትልቅ የህይወት አላማ ሲኖርህ ብቻ ነው። አንድ ነገር አስታወስ፤ ሰቃይህ ከፍረሃትህ የመነጨ ከሆነ ሁሌም ተመሳሳይ እድገት አልባ በምሬትና በሰቆቃ በተሞላ ህይወት ውስጥ እንደመኖር የሚያስፈራ ነገር ሊኖር አይችልም። ትናንት፣ ዛሬ እንዲሁም ነገ አንድ ቦታ እንደመገኘት የሚያሳምምና የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም። ትርጉም አልባ ህመምና ፍረሃት መሆኑ ደግሞ ይባስ ያሳምማል። መታመምህ፣ መሰቃየትህ ካልቀረ የህይወት አላማህን ለማግኘትና ለመኖር ታመም፤ ፍረሃትህ ካልቀረ ህልምህን ለመኖርና ለማሳካት ፍራ። በፍሬ አልባ እስር እራስህን አታሰቃይ።
ግሩም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪




ሳታጡት ተጠቀሙት!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
አባባሉ እንዲህ ይላል፦ "በእጅ ላይ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል።" ብዙዎቻችን አሁን እጃችን ላይ ምን እንዳለ አናውቅም። በሰዓቱ እኛ ጋር ስላሉ ብቻ ቀላልና ዋጋ ቢስ እንደሆኑ እናስባለን። ነገር ግን የምንም ነገር የሚጨምረውም የሚቀንሰውም እንደባለቤቱ አጠቃቀም። አሁን በእጃችሁ ላይ ምን አለ? እውቀት? ተሰጥዖ? ገንዘብ? የሚያግዛችሁ ሰው? ልምድ? ወይስ ሌላ? ዛሬ ያላችሁን ነገር መጠቀም ካልቻላችሁ አንድ ቀን ሳታስቡት እንደምታጡት አትጠራጠሩ። ነገሮችን ጅብ ካለፈ ውሻ ጮሀ አታድርጉት። ምንም ነገር ዋጋ የሚኖረው በሰዓቱ ጥቅም ላይ ሲውል ብቻ ነው። ጊዜ ካለፈ አለፈ ነው። የሆነ ጊዜ ገዢ የነበሩ ሰዎች በስልጣናቸው ዘመን በጎ ባይሰሩ ሌላው ገዢ ሆኖ ሲመጣ ምናልባትም ተከሳሽ ሆነው የሚቀርቡበት እድል ከፍተኛ ነው። የሰው ልጅ ሁሉ በእኩልነት የተሰጠው ረቂቅ አዕምሮ አለው። ግማሹ ተጠቅሞበት ለዓለም ይተርፋል፣ ግማሹ ሳይጠቀምበት እንዲሁ እያባከነ እራሱንም ይጎዳበታል። የሰው ልጅ የአዕምሮ ንቃትና የማስተዋል አቅም በእድሜ ደረጃው ይለያያል።

አዎ! ንቁ፣ ሳታጡት ተጠቀሙት! ፈጣሪ የሰጣችሁ አዕምሮ አለ። የእናንተም የሌሎችም አንድ ነው። አጠቃቀሙን ካወቃችሁ ህይወታችሁ የብዙዎች ምኞት ይሆናል፣ ሳትጠቀሙት ቀርታችሁ በዋዛፈዛዛ ብታሳልፉት ግን የውድቀትና የስንፍና ምሳሌ ሆናችሁ ትነሳላችሁ። አምበሳ ሲያረጅ የዝምብ መጫወቻ ይሆናል? ለምን? እርጅና ግርማሞገሱን ይቀማዋል፣ እድሜ ብርታቱን ያሳጣዋል፣ ጊዜ ያደክመዋል። ምንም እንኳን የአንበሳነት ባህሪውን ባያጣም ወኔውና ብርታቱ ግን እያደር እየወረደና እያነሰ ይመጣል። በብርታቱ ጊዜ ያድናል፣ በወጣትነቱ ወቅት የሚፈልገውን ያደርጋል፣ በጫካው ንግስናውን ያውጃል። ጊዜውን ስለተጠቀመው የሚፈልገውን ነገር በጊዜው ያገኘዋል። እጃችሁ ላይ ባለ ውድ ነገር ውድ ነገር እያመጣችሁ ስለመሆኑ እርግጠኛ ሁኑ። የጉብዝናችሁ ወራት የት እያሳለፋችሁት ነው? የብርታታችሁን ወቅት እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? በብርታታችሁ ወቅት ለሽንፈት እጅ ሰጥታችኋልን? በጉብዝናችሁ ጊዜ ተስፋቢስ ሆናችኋልን? በጥንካሬያችሁ ጊዜ ሰዎችን እየለመናችሁ ነውን? ጊዜያችሁን አታባክኑ። ነቅታችሁ ስጦታችሁን ተጠቀሙ፣ ያላችሁ ነገር እያያችሁት እንዲያመልጣችሁ አትፍቀዱ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰዓቱ እየቆጠረ ነው፣ እድሜ እየሔደ ነው፣ ህይወት ከመቅፅበት እየተቀየረች ነው፣ ሰዎች በፍጥነት እየተረሳሳሱ ከአዳዲስ ሰዎች ጋር እየተዋወቁ ነው። አንተስ የት ነህ? ምን እያደረክ ነው? ህይወት እስክትገባህ አትጠብቅ የገባህን ያክል ከልብህ ኑራት፣ የተረዳሃትን ያክል በተግባር ግለጣት። ህይወት በአጠቃላይ የጥሩ ውሳኔዎችህ ግልባጭ ነች። ዛሬ ወስነህ ብዙ ነገርህን ማስተካከል ትችላለህ፣ ዛሬ ከልብህ ተማክረሀው ውጤታማ ህይወት መኖር ትችላለህ። ምኞትህ ሁሉ ምድር ላይ እንዲወርድ ከፈለክ ያለህን ነገር እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ማወቅ ይኖርብሃል። በህይወት እስካለህ ድረስ ካጣሀው ነገር ያለህ ነገር በብዙ እጥፍ ይበልጣል። ጉድለትን መቁጠር አቁም፣ ድክመትህን መተንተን አቁም፣ ስላጣሀው ነገር ደጋግመህ ማውራት አቁም። "ይሔ ቢኖረኝ፣ ያ ቢሰጠኝ፣ እንትና ቢያግዘኝ" እያልክ ጊዜህን ከምታጠፋ እጄ ከምን? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለህን ትንሽዬ ጠጠር ተጠቀም፣ የምትፈልገውን ትልቅ ህንፃም ዛሬውኑ መገንባት ጀምር።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪

3k 0 25 1 36

ምርጫ የለኝም!
፨፨፨///////፨፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "እያስጠላኝም አደርገዋለሁ፣ ውስጤ ሳይፈቅድልኝም አከናውነዋለሁ፣ ስሜቴ ሳይስተካከልም እፈፅመዋለሁ፣ ለጊዜው ፍላጎት ባይኖረኝም አደርገዋለሁ። ምርጫዬ አንድና አንድ ነው ማድረግ ያለብኝን አድርጌ እራሴን ነፃ ማውጣት፣ የሚጠበቅብኝን ሃላፊነት ተወጥቼ ውስጤን ማሳረፍ። ለዘመናት በቁጪት መሰቃየት በቅቶኛል፣ ለዓመታት እራሴን መውቀስ ሰልችቶኛል፣ በየቀኑ እራሴን ማታለል አንገሽግሾኛል። ስለራሴ ከእኔ በላይ ማንም አያውቅም፣ ማንም እንዲያውቅም አልፈልግም። ስለራሴ የማውቀውን ያህል የመልፋት ግዴታ አለብኝ። ከዚህ በላይ ድክመቴን እየተንከባከቡ፣ ጥንካሬዬን ችላ እያልኩ መኖር አልችልም። ከጊዜያዊ ምቾቴ በላይ ቆይቶ የሚያሰቃየኝ ቁጪትና ፀፀት ይበልጥ አስጨናቂ እንደሆነ ገብቶኛል። ብዙ አስቤያለሁ፣ ብዙ አውጥቼያለሁ ብዙ አውርጄያለሁ፣ ሰው አማክሬያለሁ፣ ችግሬን፣ ድክመቴን፣ ክፍተቴን በየቦታው ተንትኜያለሁ ነገር ግን አንዳቸውም ችግሬን ሊቀርፉልኝ አልቻሉም፣ ሃሳብ ከመስጠት በቀር አንዳቸውም አብረውኝ አልተፋለሙም፣ መንገድ ከመጠቆም በቀር አንዳቸውም አብረውኝ አልተጓዙም። ጉዳዩ የእኔ እስከሆነ ድረስ ሙሉ ሃላፊነቱም የእኔ የእራሴ ብቻ ነው።

አዎ! እራሴን ከማዳን ውጪ ምንም ምርጫ የለኝም፤ ለእራሴ ከመድረስ፣ ለእራሴ ከመቆምና ለእራሴ ከመታገል በቀር ምንም አይነት የተሻለ አማራጭ የለኝም። ህይወት እንድታዳላልኝ ብዙ ጠብቄያለሁ፣ ሰዎች እንዲረዱኝ፣ ሀሳቤ እንዲገባቸው፣ ህልሜን እንድኖር እንዲያግዙኝም ብዙ ተስፋ አድርጌያለሁ። ነገር ግን ቢዘገይም የገባኝ ይሔ ነው። "እኔ እራሴን መረዳትና መርዳት ካልቻልኩ ማንም መጥቶ ሊረዳኝ አይችልም።" ክብደቱ በደምብ ይገባኛል፣ ስቃይ እንዳለው በሚገባ እረዳለሁ፣ ብዙ እረፍት አልባ ምሺቶች እንደሚጠብቁኝ አውቃለሁ ነገር ግን ብቸኛው እራሴን ለማዳን የምጓዝበት መንገድ ይሔና ይሔ ብቻ ነው። ያልሞከርኩት አቋራጭ መንገድ የለም፣ ያልሰራሁበት የሰዎች አካሔድ የለም፣ ያልደከምኩበት የሰዎች System የለም። ሁሉም ጊዜና አቅሜን ከመጨረሳቸውም በላይ የሰጡኝ እውቀትና ልምድ ይበልጥብኛል። ከሰው በላይ ለእራሴ የሚሰራ፣ በብዙ የተፈተነና በብዙ ውጣውረድ የተቃኘ የእራሴ መንገድ እንደሚያስፈልገኝ አውቄበታለሁ። ደክሞኛል ብዬ ብቆም ቦሃላ ምን እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ፣ ደብሮኛል ብዬ ሳልሰራ ብቀር ቦላ አዕምሮዬ እረፍት እንደማይሰጠኝ አውቃለሁ። ስለዚህ እያየሁ ስቃይ ውስጥ እገባለሁ፣ እያወቅኩ ዋጋ ለመክፈል እዘጋጃለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! ለእራስህ ብዙ ምርጫ አትስጥ። ብቸኛ ምርጫህ ሊሆን የሚገባው እያሰቃየና እየፈተነም ቢሆን ዋጋህን የሚጨምር፣ እያስጨነቀና ፋታ እያሳጣም ቢሆን ለድል የሚያበቃህ መሆን አለበት። ቀላል ምርጫ ቀላል ሰው ይወልዳል፣ አቋራጭ መንገድ የልምድ ውሱንነትን ይፈጥራል። ብዙዎች የሚመኙት ጥንካሬ ከመሬት ተነስቶ የሚሰጥ አይደለም፣ ብዙዎች የሚፈልጉት አሸናፊነት ሳይፈተኑ የሚሰጥ አይደለም። ውስጥህን አሳምን። ስቃይ የሌለው ህይወት ከመካከለኝነት የዘለለ ህይወት አይሰጥህም። የግል ህመም፣ ስቃይ፣ መከራ፣ ፈተና የማንም ምርጫ አይደሉም ነገር ግን እንቁውን የህይወት መዓድን ለማግኘት በእርሱ ጋር መጓዝ የግድ ከሆነ ልትመርጣቸው ይገባል። ደፋርና ፈሪ የሚኖረው ህይወት ልክ እንደ ጫካው ንጉስ አንበሳና በሰፈር ላይ ህፃናት እንደሚያባርሩት ውሻ ልዩነት አለው። ፈሪው በትንሹም በትልቁም ይደነግጣል፣ የተወራው ሁሉ ልቡን ያቆመዋል፣ በተቃራኒው ደፋሩ አላማው አደን ከሆን ምንም ቢፈጠርበት ወደኋላ አይመለስም፣ ቆርጦ የወጣው ረዕይውን ሊያሳካ ከሆነ የትኛውም ፈተና አይበግረውም። ምርጫህን ገድበው፣ ውጣውረዱን ፈርተህ ለወረደ ህይወት እራስህን አሳልፈህ አትስጥ።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel 😊 💪

3k 0 17 6 37
20 last posts shown.