ግራ የሚገባ ነገር እኮ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሀገር እያመሰ፡ ከተማ እያተራመሰ፡ እየዘረፈና እየገደለ የጋራ ግብረሃይል የሚባለው ቡድን ትንፋሹም አይሰማም። 500ኪሎሜትር በርቀት በሰፈሩ በሰላም የተቀመጠውን ፋኖ ካላጠፋሁ ብሎ ሰራዊት ያዘመታል። እንዴት ያለ ጥልቅ አደጋ ውስጥ ነን ጎበዝ? ድንዛዜው እጅግ ያስፈራል። ምን ዓይነት አዚም፡ መተት በሉት የጥንቆላ ትብታብ በተለይ መሀል ሀገርን እንዲህ ያደነዘዘው ምንድን ነው?
መንግስት ሁለት ጃኬት አለው። አንዱ የቤተመንግስቱ ጃኬት ነው። ሁለተኛውን ያጠልቅና ''ሸኔ'' በሚል የብዕር ስም ሀገር ያተራምሳል። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር የማፊያ ተግባር ያከናውናል። ኮሽ አለ ብሎ የመግለጫ ጋጋታ፡ የማስፈራርያ ክምር የሚቆልለው የጋራ ግብረሃይል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግስጋሴን 'የእኛው ልጆች ናቸው' በሚል ሂሳብ ጉዳዬም አላላቸውም። እነዚህኞቹ ባለአንደኛው ጃኬቶች ህገመንግስት የሚንዱ አይደሉም። ህገመንግስታዊ ስርዓቱን የሚገለብጡም አይደሉም። የቤት ልጅ ናቸው። የስለት ልጅ። እንዳሻቸው ይፈንጩ። ይዝረፉ። ህዝብ ያስለቅሱ። የሚገድሉትን ሰዎች 'ህጋዊ ሟቾች'' የሚል ስም ለጥፎላቸው መግለጫ የሚሰጥ ሌላኛውን ጃኬት ያጠለቀ የመንግስት ባለስልጣን ይመጣል።
ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። በወንበዴ፡ ወረበላ፡ ዘረኛ፡ዘራፊ፡ ቀጣፊ፡ መንደርተኛ፡ አቅመ ቢስ፡ ደካማ፡ ልፍስፍስ፡ ጠባብ ቡድን እጅ ላይ ወደቃለች። ሸኔ እየገደለ እየዘረፈ ይሸለማል። ፋኖ ሀገር እያዳነ ይታደናል። ፋኖ የእንጀራ ልጅ ነውና። ዓለም ቲያትር ናት ያለው ማን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ አሰቃቂና ዘግናኝ ትራጄዲ ሆናለች።
https://t.me/mesaymekonnenet