ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ቀን 100 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,950 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ (100) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 53 ወንድ እና 47 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 98 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ ሰው የብሩንዲ ዜጋ ነው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ (34 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው እና 60 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ) ፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ያሉ) እንዲሁም 3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (1 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለውና 2 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 3
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 35
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 62
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላንትናው ዕለት አስር (10) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 191 ደርሰዋል።
@midu_14 @midu_14