ሚኪያስ ፈይሣ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ግጥም
ወግ
ሀሳቦች
ልቦለዶች
🤝 @mika145

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ሁሉም ውሸት ነው
ተረት ተረት
ልበ ደካሞች ድነው ቢያልፉም
ሀኪማን ሆዬ ቆዳን እንጂ
የተቀደደ ፡ ልብ አይሰፉም!

@mikiyas_feyisa


ተታግለናል እጣ ፈንታን
አብሮ የመሆን ተስፋ እንዳለው፥
እንዳይቆጭሽ ስንለያይ፡
ሞክረሻል
ሞክሪያለው!።

@mikiyas_feyisa

813 0 12 4 54

"እግዚአብሄር ይመስገን"
ሁሉም ሰውን የሚሰማው ቃል
ደህንነትህን ሲጠይቁህ
የትኞቹ ቀናት ናቸው
 ፈገግታህን የነጠቁህ?

ሁልጊዜ ሳቅ  ሁሌ ደስታ
ለምለም ሆኗል ልብህ ጫካው
ከአመት አመት ደህና መምሰል
ምንም ነገር እንዳልነካው

ሰርክ እንዳዲስ ሲያበጥርህ
ኑሮ እንክርዳድ እንደ ብቃይ
ገላህ ደክሞ ፊትህ ደህና
እንዳላየህ አንዲት ስቃይ
ዝምተኛ አንገት ደፊ
ባህሪህን ሀገር ያውቃል
ሰገነት ላይ ስትዘምር
ያየህ ሁሉ ይጠይቃል
የነገሩኝ ይህ አይደለ?
የሆነውስ እንዲህ አይደል?
ትሰማለህ ስለሙሉህ
ትሸሻለህ ያለ በደል
ተሰባብሮ ተከስክሶ
የልብህ ላይ መስታውቱ
ውዳሴውን ልትደግም
ተሽቀዳድመህ ወደቤቱ
እግዜር ይክበር ዘውትር ቃልህ
አየዋለው ነገን በእርሱ
አንተም እምነት አግዞሃል
እስቲ በለኝ ስለነሱ

እናቴ ያልካት የምትወድህ
ያኖረችህ ተንከባክባ
አይንህ ደክሞ ስታጤነው
ምን ሆና ይሆን ያቺ አበባ
አይተኸዋል አንጀት ልቧን
አይተኸዋል ያንን መልኳን
ላንሳፈፈህ ድውይ ቀርቶ
ይለወጣል ለሳል እንኳን
የአስራ አምስቱን
 ስቃይ ድካም
ሲበላባት ክፉ ሰርዶ
እንዴት ቆማ አለፈችው
ያንን ሁከት ያንን መርዶ?

አላወጣች ክፉ ቃላት
አላሰማች ወየው ወየው
እስቲፋኖስ ተንበርክካ
ምንድን ነበር ምትፀልየው?

"አትውሰደው እዚው ይቆይ
 ብቻዬን ነኝ ለማን ጥቅም
ለኔ አድርገው እሱ አይችልም
ልጅ እኮ ነው የለው አቅም
ብቻዬን ነኝ አልነግርህም
ታውቀዋለህ ቤቴ ልኩን
የኔን በእጥፍ ልስጥህና
መልስልኝ የፃን መልኩን

መድሃኒአለም የማትከዳኝ
ስለት ገባው ይኸው እጄን
ላንተው ዲያቆን ይሁንልህ
አቆይልኝብቻ ብቻ ልጄን"

ብላ ነበር ምትፀልየው?

 ፊትህ ጠቁሮ ከስቶ ስታይ
ተኮራምተህ ከአንዲት አልጋ
ነጠላዋን አገላድማ
 ሰርክ ማልዳ መሃሪውጋ?

ንገረኛ  የሆነችውን

ታለቅሳለች  እቅፍ አርጋህ
የሀዘኗን የጭንቀቷን
ወይስ ላንተ ጠንካራ ነች
አታሳይም የእምባ ፊቷን

ንገረኛ እያስታወስክ
ሁሉን ችላ ትስቃለች
ዘጠኝ አመት ተሸፋፍና
እህ ማለት እንዴት ቻለች?
የልቧ ላይ ተስፋ ብርሃን
በጽልመቱ ቢበለጥም
ሰርክ ደጁ ትወድቃለች
በአምላኳ ላይ ተስፋ አትቆርጥም?

ንገረኛ ወንድም አለም

በወንድምህ ልትለኩስ ነው
የጠፋውን ተስፋ ፋኖስ
ከናትህ እቅፍ እንዳየኸው
ቀድመህ ያልከው እስጢፋኖስ?
ሰው እንድትወድ  በልጅነት
በአምላክ ፍቅር የተነካህ
ትተህ ስትሄድ  አንተን ለምደን
እንዳይከፋን ሌላ ተካህ?

ሚያሳዝኑት ጓደኞችህ
 ደብሩ ውስጥ የሚያለቅሱ
ሚያሳዝኑት ደግ እናትህ
እምባቸውን የጨረሱ
ላንተማኮ አንድ አይነት ነው
እዚም የርሱ  እዛም የርሱ

በአጭር አይተን
ሳንጠግብህ 
ብትቆረጥ እንደ እንጥል
ለእስጢፋኖስ እኛው አለን
ዝማሬህን እዛው ቀጥል!።


@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa


Hi mike endt nh pls  1 nger techgrlign ye senbt temhert bet agelgay yenbre lij Nber  yohannes yibala 15 year nw  be cancer 9 year noral before 2 years indian hedo surgery tesrto dena hono nber yemtw keza last year betme tamo bed ly almost 3 years tegnto nber grade 8 alfo ahun 9 nber migbaw yenberw estifanous betme nber miwdw deacon lemhon mengd ly nber ke church kerto aykm all day church nber migegnw andm day amognal ayilm fetrin nber miyamsgnw 😢 enatu betme leftaltalch dekmgn atlm nber esum ke esu & ehetu wechi hazenun ayingerm tikur anbssa hospital bezu gize temlalsul keza yemigerm be 17 be estifanous day ya kalkidanu tabout weto eyle tsebl setugn ale betsbu fera mnm saykoy nefsu telye arfe tolo belw ngrochn chersw ye kalkidanu tabot sigba askrenun abrw azgbut bet mekdsun zorut senbt tamriwoch mezmer aktachw hulum malks 😢 jemer enatoch alchalum..... pls be 24 7 day metsbiya awde mehrtu ly yizgajal le esu mihon poem getmi tebye nw ene gn Mariamn aktgn mn bey type marg endlbgn alkm pls erdgn..


Video is unavailable for watching
Show in Telegram




.. ለአንድ ቃል

ስንቱን ውርደት ታግሰን ኖርን
ስንቱን አሽሙር ተውን ንቀን
ስንት በደል ውጠን ሳቅን
እምባ እና ሳግ ፡ እያነቀን።

ስንት ንቀት አይተን አለፍን
ስንት ቅጥፈት ቆመን ሰማን
ስንት ስድብ ችለን ሄድን
ውስጣችንን እያደማን
ስንት ፈሪ ቀለደብን
ስንት አጎብዳጅ አስረገጠን
እርጥብ ላንቃ ፍቆ ሚወርድ
ፍርፋሪ ለሚሰጠን

ስንቱ ደጁ ወስዶ አሰጣን
እንዳረጀ የአበባ ገል
ስንቱ ለማኝ አርጎ አበላን
ህሊናውን ለመታገል

ስንት ጊዜ ሙግት ገባን
ላጉል ተስፋ ሞትን አጨን
ስንት ጊዜ ለማመስገን
እግዜሩ ላይ እምባ ረጨን?

ስንት ጊዜ ስም ተሰጠን
ተፈረጅን በመደዳ
ስንት ጊዜ አንገት ደፋን
ሰንዝሮ እንኳን ለማይጎዳ

ስንት ጊዜ ተቋቋምን
ያልተሰማ ያልታየ ግፍ
ስንት ችግር አቅፈን ኖርን
ዘለላ እምባ ሳናረግፍ

ስንቱን ቻልነው አንጀት ቋጥረን
"ቃል" ይመስል የስኬት ባል
ስንት ሲዖል ዋኝተን ወጣን
"ኮራውብህ" እስክንባል?

@mikiyas_feyisa


...

"ነገ" ከትላንት ፡ ቢጎብዝም
ሲያድር ቢሆንም ፡ ሁሉ መልካም፤
የሄደ ሁሉ ፡ እንዳልነበር
በሚመጣ ሰው ፡ አይተካም።
እርግጥ ነው ቃሉን ፡ አልክደውም
ተረት አይደለም ፡ መጫወቻ፤
ግን ሰዎች አሉ ፡ የተለዩ
ከአዕላፍ መሃል ፡"አንድ"ብቻ።

@mikiyas_feyisa


"ትላንት" ግን
ምናባቱ?
እስከ "ዛሬ" መቆየቱ፤
"ነገስ" እሺ
መብቱ አለው?
በ"ዛሬ" ላይ
ፊጥ የሚለው?

@mikiyas_feyisa


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ጥፋተኛ ነበርሽ አትዋሺ
እርሱ ብቻ አይደለም የበደለሽ
እውነቱን አጥርተሽ እንዳታዪ
ጭፍን መውደድሽ ነው የከለለሽ
ውስጡ ለቄስ ሆኖ ቡቡ ሆድሽ
ጥንቁቅ ትመስያለሽ ስትታዪ
እንደ ሽሮ አስጥተሽ እሜዳ ላይ
ልቤን ተዘረፍኩኝ አትበዪ

አውቃለው ጥሩ ሰው መስሎሽ ነበር
አውቃለው ውስጥሽን ተረድቶሻል
አውቃለው ልዩ ሰው እንደነበር
አውቃለው ላይተውሽ ምሎልሻል

አውቃለው ታሪክ አትደጋግሚ
እንዳልተረዳውሽ ፊት አትንሺኝ
ያለፈው ተጫውቶብሽ ሳይሄድ
እሱንም እንዲያ ነበር ያልሺኝ

ችግሩ ትዝ አይልሽም አንቺ
ካለፈው ትምህርት አትቀስሚም
አትቸኩይ ቀስበይ የሚሉሽን
ምቀኞች ብለሽ አትሰሚም
እርሱ ነው ይበልጥ የሚጎዳሽ
እንደ ምንጭ እምባሽን ሚያፈሰው
መውረጃ ቦታውን ያውቀዋል
እምባሽን የጠረገልሽ ሰው

ውስጥሽን ገልጠሽ ያጫወትሽው
ከህመም እንድትሽሪ የረዳሽ
ዛሬ ላይ ባየው ድክመትሽ ነው
ነገ ላይ ዞሮ የሚጎዳሽ

ስሜትሽ ፅዋ አይደል ጸበል ጻዲቅ
ለሰው ሚያካፍሉት ለአፍ ሚጥም
ልብ ክብር አለው እንደ ፅላት
ለመጣ ሰው ሁሉ አይሰጥም
ይኸውልሽ
የልቤን እኔ ብዬሻለው
ተግባርሽ ያውጣሽ ከዛ ውጪ
ከማይሆን ሰው ጋር አብረሽ ስቀሽ
ልታለቅሺብኝ እንዳትመጪ።

@mikiyas_feyisa


አባት  መከታዬ
ምናምንቴ አልልም
ጥሩ ሰው እንደነበር
እስከዛሬ አልጠፋም
በልጅነት ገርፎ  ያወጣብኝ ሰንበር

ዳዲ ቅብርጥሴ
ምናምንቴ ተረት
ዲስኩር አልለቃቅም
ለዚያ ቆዳ ጫማ
ቅያሪ የሚሆን ሶል
ገዝቶልኝ አያውቅም

በእርግጥ ችጋራም ነው
በወጣትነቱ
ነግዶ እንዳያተርፍ
ትምህርት ያታለለው
ከቤቱ በስተቀር
ለስም ማስታወሻ
አንድ ቅርስ የሌለው

በርእግጥ ድሃ አደግ ነው
የተዝረከረከ መደብ ላይ ተኝቶ
ህልሙን የቀመረ
በአባቱ ማሳ ላይ
በናቱ ቀጭን ሊጥ የተመራመረ

በእርግጥ ድሃ አደግ ነው
በአንድ ጉንጪ ወተት
በአንድ ጉንጩ ቅቤ
በአንድ ጉንጩ ጎረድ
በአንድ ጉንጩ አይቤ
በልቶ ያላደገ ምቾት ያልተቃጣው
አንዴ እረኝነት
አንዴ ዘበኝነት
ጠጉሩን ያነጣው

በእርግጥ የዋህ ሰው ነው
ለዘመድ ለባዳ ልሳለምህ ብሎ
ቤቱ ለሚመጣው
የጓዳው እንጀራ ካለተዳረሰለት
ሀፍረት የሚቀጣው

በእርግጥ ንፁህ ሰው ነው
በላቡ የመጣ የደመወዝ ፍሬው
ግንባሩን ያፈካው
ከሳቁ ጀምሮ ምናምንቴው እንኳን
የሰው ሀቅ ያልነካው

በእርግጥ ታማኝ ሰው ነው
ችግሩ ቢቆለል
ተዝቆ ተዝቆ ቢያስንቅም ተራራ
ያልደከመበትን መንካት የሚፈራ

በእርግጥ ንፁህ ሰው ነው
ግና እኔ አውቃለው
እንደልጅነቴ  ያባቴን ክፋቱን
ምንም አልደብቅም
ሀቅ ከተባለ  ልናገር እውነቱን

ጠብቆ ባቆየው
ፍፁም በክብሩ ላይ አይደራደርም
ስሙን የሚያስነቅፍ
ነውር ከተገኘ እንኳን ባዳ ቀርቶ
ልጁንም አይምርም
የሚበላ አጥተን
አንጀታችን ደርቆ በጠኔ ብናልቅም
ደም ይተፋል እንጂ
ዘመድ ዘጋ ብሎ ገንዘብ አይጠይቅም

እንደዚህ ነው እሱ
ዝቅ ብሎ መስራት  እህ ብሎ መድከም
ቀና ብሎ መኖር   እየኮራ ማከም

እንደዚህ ነው እሱ
አመስግኖ ማደር
እርዳኝ ብሎ መውጣት
እያነቡ ማግኘት እየሳቁ ማውጣት

እንደዚህ ነው እሱ

በሚያውቀው ግብረገብ
ልጆቹን አንፆ ኮትኩቱ ሚያሳድግ
ክቡር ኩሩ ደሃ
ለሀብታም ምፅዋት የማያደገደግ

ጨዋ ጭምት ሰው ነው
ለራቀው ቆምጣጣ ለቀረበው ፍቅር
ስሙን ባናስጠራም
በአብራኩ ክፋዮች የማያቀረቅር

ተመሳሳይ ሰው ነው
እንኳን ቴክኖሎጂ
የማይገዛው ጥቅም
መቼውም ቢዘምን
ልጆቹን በፍፁም አያጨማልቅም!


@mikiyas_feyisa


ፍቺ በቃ ህይወት እመቤቴን
አከሰልሽው አይደል ሰውነቴን
በቃ ተዪኝ ህይወት አልሰማሽም
የ'ስካሁን ገተታው አልበቃሽም?

ይመራል ኪዲዬን እዘኚልኝ

እኔም ልቅመስ እንጂ
ከውበቱ
እኔም ልኑር እንጂ
ከድሎቱ
አግቺኝ ማርሽን
ባናት ባናት
አቱኚብኝ እንጂ
የእንጀራ እናት

አይደብርሽም ግን ላንቺ እራሱ
ቀን በቀን ፈተና መነስነሱ
ተዪው ጅራፍሽን ወዲያ ጣዪው
አንጃግራንጃ ነው አርቲቡርቲ
እኔም እንደሰዎ ተመችቶኝ
እግዚአብሄር ይመስገን ልበል እስቲ

አቦ ተመቺኛ የኔ ቅመም
ስህተት ሰራህ ብለሽ አታኩርፊ
ልበ ቢስነቴን እያስታወስሽ
ጥቂት ጥፋቶቼን በሼ እለፊ

እመቤቴን ህይወት
ተረጋጊ
በአመት አንዴ እንኳን
እረፍት አርጊ
የት ሄድብሻለው
ካንቺ ጉያ
እረገጥሺኝ እኮ
እንደ አህያ

እመቤቴን ህይወት ከፋኝ በጣም
አመቤቴን ህይወት ተሳቀኩኝ
ከመኖር በስተቀር ዝቅ ብዬ
ሌላ ክፉ ነገር ምን አረኩኝ

እንዴ...

ፍቺ በቃ ወደዛ አድቢልኝ
እንዳይኮረኩመኝ እጅሽ ታኮ
ብቻዬን አንጋለሽ አትደልቂኝ
እኔም ይከፋኛል ሰው ነኝ እኮ

እንዴ..

ተስፋ እንኳን አድዪኝ ምናለበት
ለመኖር ልጓጓ ብማረርም
እንደ ተልባ አትውቀጭ ሙከራዬን
ትዝብት ነው ትርፉ ሞት አይቀርም!


ፍቺኝ በቃ ህይወት!

@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa


በማስመጥ ልምድሽ እየደለልሽው
ልቤን ምንጭ ውሃ የምታደርጊው
አትሽኮርመሚ ባይሆን ላግዝሽ
ምን አይነት ባል ነው የምትፈልጊው?

እንደኔው አይነት?
ግን ደግሞ ሀብታም
አባካኝ ይሁን ወይስ ስስታም ?
አለባበሱስ
መልኩስ
ቁመቱስ
እንደኔው ይሁን ቁርጥ እራሴን
ሱሪዬን ወስዶ ይቀይር ኪሴን?

እሺ ፀባዩስ?
አሁንም የኔው ተጫዋች ፍቅር
ሁሉንም ይውረስ? የትኛው ይቅር?
አንዳንዱ ማለት መሳቅ ማበዴ
ተዛዝሎ መሮጥ የደሃ ቀልዴ?

አዪዪዪዪ ..
አትማይ
አልፈርድብሽም ትተሽ ስለሄድሽ
ስልጣን ገንዘቡ ስለማረከሽ
ቅንጡ ቤቱ ድር ሲያደራበት
በእኔ ኪራይ ቤት ምን አሳከከሽ

ሚሉሽን ተዪ
ከመውደድ በላይ ምቾት ይበልጣል
ኑሮ ካማረ ፍቅር እራሱ
ሲያድር ይመጣል

ጥሩ ነው ያረግሽው
ምን አንጓተተሽ መጥቶ ላይጠቅም
መያዝ ነው እንጂ
ጊዜያዊ ስሜት አያዛልቅም።

ይኸውልሽ ውዴ
ወንድ ባዳ ነው አስር ይወዳል
ብትወጂው እንኳን
ያለፈለት ለት ትቶሽ ይሄዳል።
ወጣት አትመኝ
ወርቅ ልብሽን የትም አታስጪ
ቦርኮ አይጠቅምሽም
ለልጅሽ ስትይ ያለው ምረጪ

ትተሺኝ ሂጂ
አምነሽ ቁረጪ ልብሽ ቢፈራም
እስከምታረጅ
ፍቅር ህልም እንጂ ጎጆ አይሰራም።

የኔ ውብ አለም
የኔ ተወዳጅ
ልቤን ዶግ አመድ የምታደርጊው
አንቺ አትልፊ እኔው ልዳርሽ
ምን አይነት ባል ነው የምትፈልጊው?

@mikiyas_feyisa


የእባዋን ጎርፍ አሳነሱት
መፀፀቷን አራከሱት
ገልጠው ሰው ፊት አነበቡ
የተዘጋው ምዕራፏን
ተንቀልቅላ ቤቱ ሄደች
እያነባች ይዛ አፏን
ሰውነቷን ተጠየፈች
የፀፀቷ ጅራፍ በዛ
ከጌታ ጋር አልተዋትም
እዛው ልቧን እንድትገዛ

የወገብ ላይ ውጋት ሆኑ
እንዳትቆም አሳቀቋት
በመጠየፍ አይን እያዩ
ቅን እምነቷን መነጠቋት
ውለው አድረውም
እንዲያው ናቸው
ሁሌ ግራ የሚሄዱት
ጥፋቷን ሰርክ እያነሱ
ንስሀዋን አከበዱት

አዎን ብዙ በድላለች
ሀጥዕ ሆና ጋለሞታ
ማንም ጣቱን እንዳይጠቁም
ከመጣች ግን ወደጌታ
ወርቅ ምንጣፍ ይዘርጋላት
ወደ ቤቱ እስክትገባ
ከግብዞች ፀሎት በላይ
ጌታ ይሰማል ንፁህ እምባ
ታሪክ ገጿ ምንም ይሁን
የትላንቷ ምንም ያክል
ማነው ሸክሟ በዝቷል ብሎ
እንዳትገባ ሚከለክል ?
.
አወሩባት ብዙ ነገር
.
አይን አውጣ ነች የማታፍር
አይተናታል ከዚህ ቦታ
ከጀርባዋ ይዘልፏታል
ታለቅሳለች በዝምታ
እንዲህ ሴት ነች
እንዲያ ሴት ነች
ክፉ ግብሯን ዘረዘሩት
ምንም ጥፋት እንዳልሰሩ
አሽሟጠጡ የተቀሩት

ምናለበት ሰው አይደለች?
ምናለበት ሰው አይደለች?

የልብሳቸው ጨርቃ ቢወልቅ
ቀሽም ቀሊል የሚሆኑ
ሱባኤዋን እስክትጨርስ
ገመናዋን ቢሸፍኑ
ባይፈርዱባት ምናለበት
በአደባባይ ለህዝበ አገር
የሀዲስ ኪዳን ሀጥያተኛ
በቃላት ነው የሚወገር?

ይበቃታል ህሊናዋ
ሰርክ አስታውሶ የሚቀጣት
ይበቃታል ህሊናዋ
በሀሳብ ማዕበል የሚንጣት
ይበቃታል ሰውነቷ
የሚቀፋት እንደ ሩቅ ሰው
ይበቃታል ይህ ጭንቀቷ
ውስጧን በልቶ የጨረሰው

አታድክሟት ደካማዋን
አትጨምሩት መከራዋን
አንድም የለም ከኛ መሃል
ችሎ ችሎ የማይደክም
እስቲ ተዋት ከአምላኳ ጋር
የሷን ህመም እሷው ታክም!

@mikiyas_feyisa

1.9k 0 14 11 52

አስጠነቆልኩባት


ዱር ገደል ወርጄ
ጠንቋይ ዘንዳ ሄጄ
መስተፋቅር ብቻ
ለሚጠነቁሉ.. ለታወቁ አባት
ጠጉሯን ይዤ ሄጄ.. አስጠነቆልኩባት

የታባቷንና
ለምን እኔ ብቻ ከርሷ መሄድ ማልተው
ለምን እኔ ብቻ ሳያት ምደሰተው
ለምን እኔ ብቻ በፍቅሯ ምቃጠል
ለምን እኔ ብቻ
ጡት እንዳየ ህፃን ላዩዋ ምንጠለጠል
ለምን እኔ ብቻ የ'ርሷም ዕጣ ይድረስ
የካበችው ገላ ከእግሬ ስር ይፍረስ
ለምን እኔ ብቻ
ለእርሷ ምንገበገብ በናፍቆት ምቀጣ
እርሷም በተራዋ ተንቀልቅላ ትምጣ

የታባቷን
በምዕናቤ እየሳልኩ
በፍቅሬ ተቃጥላ
ወደኔ ስትከንፍ ወደኔ ስትበር
እንደ ነብይ ቃል እጠብቃት ጀመር
ብጠብቅ .. ብጠብቅ
ብጠብቅም በጣም
ናፍቆቷ ነው እንጂ አካሏ አልመጣም
ጠንቋዩን አምኜ
ጠብቂያት
ጠብቂያት
በመጠበቅ ብዛት ጉልበቴ ቀለለ
ከመቅረቷ ይልቅ
በጠንቋዩ ስራ ቆሽቴ ድብን አለ

ወደ ጠንቋዩ ቤት
መብረር እየቃጣው እግሬ ተራመደ
እቅጩን ልነግረው
የርሱ ጥንቁልና ቁብ እንዳልፈየደ
ልጣላው ወስኜ
ከቤቱ ደርሼ አንኳኳው የምሬን
አልመልስም ካለ
"መስተፋቅር" ብሎ የበላኝን ብሬን

አልከፈት ብሎኝ
በርግጄ ስገባ ..ትግስቴ ተሟጦ
ጠንቋዩን አስተዋልኩ
ቆርጬ ያመጣሁት ፀጉሯ ላይ አፍጦ

አይ አለመታደል
ይህ ታታሪ ጠንቋይ
ስራን ከምንም ላይ ተነስቶ የፈጠረ
ፀጉሯ ጦስ ሆኖበት
ጥንቁልና ትቶ ከምንም ላይ ቀረ

"ፍቅሯ አደንዝዞት
እሷን አገኝ ብሎ
ጠንቁሎ ጠንቁሎ ..ከመጠንቆል ብዛት
መጠንቆያው ሲኒ..የሲኒ ጨብጥ ያዛት"
አያለ ይታማል

እኔ ግን እኔ ግን
የርሷ አለመምጣት
የብሬ መበላት ..ቅንጣቱን ሳይከፋኝ
እርሱን ማባበሉ ..በጣሙን አለፋኝ


ፍቅሯ ተምታቶበት
ፍቅሯ አጃጅሎት
በእርሷ ዘንዳ ሚኖር ሲሆን ቋሚ በድን
አማራጭ ስላጣን
ሌላ ጠንቋይ ጋራ ለማስጠንቆል ሄድን

*------------------*
@mikiyas_feyisa
(11-09-2015)
የቆየ ነው ደሞ😁🫡

2.2k 0 37 23 63

እንደ ተበዳይ አታልቅሺ
ለበደል ነበር አመጣጥሽ
ፀባይ አመልሽን ማጣፈጥሽ
እስስት ውስጥሽን መለወጥሽ

እንደ ንፁህ ሰው "እሪ" አትበይ
ባገር በሰፈር አታሳጂኝ
የሳልሽው ብረት በላሽ እንጂ
እቅድሽ ነበር ልትጎጂኝ

የዋህ አልነበርሽም እንዳሰብኩሽ
ጅል አልነበርኩም እንዳሰብሺኝ
አባዝተሽ ከኔ ለመውሰድ ነው
ሽሙንሙን ፍቅር የሰጠሺኝ

ፍቅርሽን ይዤ ዝም ብልሽ
ከእብድ አየሺኝ ከወንበዴ
ክፉ ሰው ሆንኩኝ ልትሄጂ ስል
ቀድሜሽ እኔ በመሄዴ

እሰይ ደግ አረኩ
የኔ አስመሳይ
ብትቀበሪም ፡ አላምንሽም
እምባሽ ላይ ሳቅሽ ይታየኛል
ውሸት አትፈሪም እየማልሽም
ድራማሽ ይብቃ ተነቃቃን
ከበቀል ጠጪ ከእልሁም
መለየት መርሳት እችላለው
እንደ ወንዶችሽ አይደለሁም!

እንዲያ ነው ብለሽ አውጂልኝ
ይሄ ጥቅስ አለ ከኔ ዘንዳ
"ደግ ነው በዳይ የሚያስለቅስ
ብፁዕ ነው ክፉ የሚጎዳ!"

እሰይ ..
እንኳን ጎዳሁሽ
@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa


..
ለገላዋ እራፊ ፡ ብጣሽ አልገዛሁም፤
እረዥም ታሪኳን ፡ ቁጭ ብዬ አልሰማሁም
ምኞት ፍላጎቷን ፡ ለይቼ አላወኩም
የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤
አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤
ያመቃትን ስቃይ ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው

ከድርብርብ ውጥረት
አስሮ ከደበቃት፤
ሽሮ ለመላቀቅ ፡ ቀልዴ ለሚበቃት
ማድያት ሽፍታ ፡
ሲያጨላልም መልኳን፤
ተራራ ሆኖብኝ ፥
"ምነው?" ማለት እንኳን
ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤
የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም
ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ
ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡
"ወዳታለው" ብቻ።


ይቅርታ.. እማ።

@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa


...ለምን?
ስለማምን?

ሁሉም
የሚጥለኝ ፤
ድንበር ፡ ስለሌለኝ?

@mikiyas_feyisa

20 last posts shown.